2 months ago
ማንቸስተር ሲቲ ከ ቦርንመዝ እና ኒውካስል ከ ሊቨርፑል - የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች
**********************
ቀን 10:00 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንመዝን የሚገጥም ሲሆን፣ ምሽት 12:30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ በሴንት ጄምስ ፓርክ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል።
ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ከቦርንመዝ ጋር ባደረጋቸው ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ እና 34 ግቦችን በማስቆጠር ፍጹም የበላይነት አለው።
አዲሱ የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ ቡድኑ ባለፉት 15 የውድድር ዓመታት ውስጥ በ14ቱ የመክፈቻ ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።
ሮድሪን ለባርሴሎና አሳልፎ የሰጠው ማንቸስተር ሲቲ ፣ በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የጄረሚ ዶኩን ግልጋሎት እንደማያገኙ ታውቋል።
በነሐሴ ወር ባደረጋቸው 14 ጨዋታዎች 22 ግቦችን ያስቆጠረው የሊጉ ኪከብ ግብ አስቆጣሪ ኤርሊንግ ሃላንድ በዛሬው ጨዋታ ላይም ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ማርኮ ሮዝ የሚመራው ቦርንመዝ፣ ካለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የያዘውን የ18 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ለማስቀጠል ወደ ኢትሃድ ያመራል። በተመሳሳይ ሰዓት ብራይተን በአሜክስ ስታዲየም ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል፡፡
በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ካለፉት 19 የሊግ ግንኙነቶቹ አንድም ጊዜ ያላሸነፈውን ሊቨርፑልን ይገጥማል።
ሁለቱም ክለቦች በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሊቨርፑል ባለፉት 13 ዓመታት፣ ኒውካስል ደግሞ ባለፉት አራት ዓመታት በመክፈቻ ጨዋታ ተሸንፈው አያውቁም።
ይህ ጨዋታ በሁለቱም ክለብ በአዳዲስ አሰልጣኞችና የቡድን ስብስብ የሚደረግ በመሆኑ ልዩ ትኩረትን ስቧል። ኒውካስል ዩናይትድ በዚህ ክረምት እንደ አንቶኒ ጎርደን፣ ሳንድሮ ቶናሊ እና ብሩኖ ጊማሬሽ ያሉ ኮከቦቹን ከ200 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በሆነ ዋጋ የሸጠ ሲሆን፣ አዲሱ አሰልጣኝ ማትያስ ያይስለ ቡድኑን መልሶ የመገንባት ከባድ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል።
እስካሁን በሁለቱ ቡድኖች ግንኙነት 198 ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን፣ ዛሬ በጨዋታው ሁለት ግቦች ከተቆጠሩ በሊጉ ታሪክ 200 ግቦች የተመዘገቡበት ሦስተኛው መርሐ-ግብር ይሆናል።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#premierleague #epl #manchestercityfc #liverpool #newcastle #bournemouth #matchday #football #ebcdotstream

6 months ago
አርሰናል በኢምሬትስ ተደናቀፈ!
#ethiopia | መድፈኞቹ በገዛ ሜዳቸው ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግደዋል። በ32ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ-ግብር ቦርንማውዝን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ወጥቷል።
የጨዋታው ድምቀቶች
ክሩፒ እና አሌክስ ስኮት የቼሪዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።
አዲሱ አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬሽ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ቢያሳርፍም፣ ቡድኑን ከሽንፈት ሊታደገው አልቻለም።
ይህ ሽንፈት አርሰናል ለዋንጫ በሚያደርገው ትንቅንቅ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ሲሆን፣ ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ስህተት የመስራት ዕድሉን አጥብቦበታል።
መድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት ያላቸው ተስፋ አደጋ ላይ ይወድቅ ይሆን?
አስተያያታችሁን አጋሩን
#getu #arsenal #premierleague #afc #bournemouth #footballnews #emiratesstadium #gyokeres #sportsupdate #addisababa #አርሰናል #እንግሊዝፕሪሚየርሊግ #ስፖርት #ጌጡተመስገን #getutemesgen
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሮቤ ከተማ አስተዳደር በጤና ባለሙያው ከዲር ዋቆ ላይ የድብደባ ወንጀል ፈጽሞ የተሰወረው ተጠርጣሪ እና ግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሮቤ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው በሐሰት "የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል" በማለት፤ ጓደኞቹን በማስተባበር ግለሰቡን ያስደበደበ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ትክክለኛ አስመስሎ ለማቅረብ የተጎጂውን ምስል በካሜራ ሲቀዳ እንደነበር ተገልጿል።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለ'ኦቢኤን ሳይበር ሚዲያ' እንደገለጹት፣ በሕግ አካላት በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ድብደባውን የፈፀሙ ግብረ-አበሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ኮማንደር ገመዳ አክለውም፣ የወንጀል ድርጊትን የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የፍትህ አካላት ሆኖ ሳለ፣ በቡድን ተደራጅቶ ሰውን መደብደብ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
#ethiopia #security #police

9 months ago
🔴 "ቀይ ለበሶቹ ማሸነፍ አቅቷቸዋል፤ ለ5 ተከታታይ ጨዋታዎች ከድል ርቀዋል!"
#ethiopia | በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ወደ ቪታሊቲ ስታዲየም ያቀናው ሊቨርፑል፤ እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በቦርንማውዝ 3-2 ተሸንፏል።
የጨዋታው ድራማ:
ሊቨርፑል በቨርጂል ቫን ዳይክ እና በዶሚኒክ ሶቦዝላይ ግቦች አማካኝነት ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም፤ ቦርንማውዞች በኢቫኒልሰን እና አሌክስ ጂሚኔዝ ከመመራታቸው በተጨማሪ፤ በባከነ ሰዓት በአድሊ አማካኝነት የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆጠር 3 ነጥቡን ጠቅልለው ወስደዋል።
የሊቨርፑል ቀውስ:
📉 በውድድር ዓመቱ ለ7ኛ ጊዜ ተሸንፈዋል።
📉 በሊጉ ብቻ ለ5 ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ተስኗቸዋል።
የሊቨርፑል ችግር መከላከሉ ላይ ነው ወይስ አሰልጣኙ ጋር? ሀሳባችሁን ስጡን!
#liverpoolfc #bournemouth #premierleague #epl #lfc #football #ethiopia #sportsnews

አንቶይን ሴሜንዮ ወደ ኢቲሃድ ሊያቀና ይችላል
#ethiopia | የእንግሊዙ ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ የበርንማውዙን ኮከብ አንቶይን ሴሜንዮን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ።
ዝውውሩ አሁን ላይ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ተጫዋቹ ዛሬ የህክምና ምርመራውን እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል።
💰 የዝውውር ዝርዝሮች
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን ለማስፈረም የተጠቀመው ስልት በውል ማፍረሻ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ ከበርንማውዝ ጋር በቀጥታ በመደራደር የተደረገ ልዩ ስምምነት ነው።
* የዝውውር ዋጋ፦ 62.5 ሚልዮን ፓውንድ።
* ተጨማሪ ክፍያ (Add-ons)፦ 1.5 ሚልዮን ፓውንድ።
* የወደፊት ሽያጭ፦ በርንማውዝ ተጫዋቹ ለሌላ ክለብ በሚሸጥበት ወቅት የ10% ክፍያ እንዲያገኝ ተስማምቷል።
✍️ የኮንትራት ሁኔታ
የ26 ዓመቱ ጋናዊ ኢንተርናሽናል በኢቲሃድ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ውል የሚፈርም ይሆናል። ሴሜንዮ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በበርንማውዝ ቤት እያሳየ ያለው ድንቅ ብቃት የፔፕ ጋርዲዮላን አይን ለመሳብ እንዳበቃው ይነገራል።
የሴሜንዮ መምጣት ለማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨማሪ ፍጥነትና ጉልበት እንደሚሰጥ የተጠበቀ ሲሆን፣ ዝውውሩ በይፋ ሲጠናቀቅ ለቡድኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ማንችስተርሲቲ #አንቶይንሴሜንዮ #የዝውውርዜና #እግርኳስ #mancity #antoinesemenyo #transfernews #premierleague #bournemouth

Comments