ማንቸስተር ሲቲ ከ ቦርንመዝ እና ኒውካስል ከ ሊቨርፑል - የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች
**********************
ቀን 10:00 ሰዓት ላይ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንመዝን የሚገጥም ሲሆን፣ ምሽት 12:30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ በሴንት ጄምስ ፓርክ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል።
ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ከቦርንመዝ ጋር ባደረጋቸው ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ እና 34 ግቦችን በማስቆጠር ፍጹም የበላይነት አለው።
አዲሱ የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ ቡድኑ ባለፉት 15 የውድድር ዓመታት ውስጥ በ14ቱ የመክፈቻ ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።
ሮድሪን ለባርሴሎና አሳልፎ የሰጠው ማንቸስተር ሲቲ ፣ በጉዳት ምክንያት በዛሬው ጨዋታ የጄረሚ ዶኩን ግልጋሎት እንደማያገኙ ታውቋል።
በነሐሴ ወር ባደረጋቸው 14 ጨዋታዎች 22 ግቦችን ያስቆጠረው የሊጉ ኪከብ ግብ አስቆጣሪ ኤርሊንግ ሃላንድ በዛሬው ጨዋታ ላይም ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ማርኮ ሮዝ የሚመራው ቦርንመዝ፣ ካለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የያዘውን የ18 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ለማስቀጠል ወደ ኢትሃድ ያመራል። በተመሳሳይ ሰዓት ብራይተን በአሜክስ ስታዲየም ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታል፡፡
በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ካለፉት 19 የሊግ ግንኙነቶቹ አንድም ጊዜ ያላሸነፈውን ሊቨርፑልን ይገጥማል።
ሁለቱም ክለቦች በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሊቨርፑል ባለፉት 13 ዓመታት፣ ኒውካስል ደግሞ ባለፉት አራት ዓመታት በመክፈቻ ጨዋታ ተሸንፈው አያውቁም።
ይህ ጨዋታ በሁለቱም ክለብ በአዳዲስ አሰልጣኞችና የቡድን ስብስብ የሚደረግ በመሆኑ ልዩ ትኩረትን ስቧል። ኒውካስል ዩናይትድ በዚህ ክረምት እንደ አንቶኒ ጎርደን፣ ሳንድሮ ቶናሊ እና ብሩኖ ጊማሬሽ ያሉ ኮከቦቹን ከ200 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በሆነ ዋጋ የሸጠ ሲሆን፣ አዲሱ አሰልጣኝ ማትያስ ያይስለ ቡድኑን መልሶ የመገንባት ከባድ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል።
እስካሁን በሁለቱ ቡድኖች ግንኙነት 198 ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን፣ ዛሬ በጨዋታው ሁለት ግቦች ከተቆጠሩ በሊጉ ታሪክ 200 ግቦች የተመዘገቡበት ሦስተኛው መርሐ-ግብር ይሆናል።
በዘረንቶስ ሰለሞን
#premierleague #epl #manchestercityfc #liverpool #newcastle #bournemouth #matchday #football #ebcdotstream

2 months ago