5 months ago
መድፈኞቹ ፉልሀምን በመርታት የነጥብ ብልጫቸውን አሳደጉ
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል በለንደን ደርቢ ፉልሀምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ ቪክቶር ዮኬሬስ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን አንድ ግብ አክሏል።
ዮኬሬስ በዚህ ውጤት ከአሌክሲስ ሳንቼዝ በኋላ በክለቡ በመጀመሪያው የውድድር ዓመት 20 እና ከዚያ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች መሆን ችሏል።
ቡካዮ ሳካ ከ11 ጨዋታዎች በኋላ በኤምሬትስ ስታዲየም ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ለሌላ ግብ የሚሆን ኳስም አመቻችቶ አቀብሏል።
ይህን ተከታታይ ድል ያስመዘገበው አርሰናል ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች ካሉት ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት አስፍቷል።
በተጨማሪም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአንድ የውድድር ጨዋታዎችን በማሸነፍ የአርሰን ቬንገርን የ39 ጨዋታዎች ክብረ ወሰን ማሻሻል ችለዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስል ብራይተንን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ብሬንትፎርድ ዌስትሃምን 3 ለ 0 ረትቷል።
ዎልቭስ ከሰንደርላንድ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
#arsenal #premierleague #football #victory #emiratesstadium #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
አርሰናል በኢምሬትስ ተደናቀፈ!
#ethiopia | መድፈኞቹ በገዛ ሜዳቸው ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግደዋል። በ32ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ-ግብር ቦርንማውዝን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ወጥቷል።
የጨዋታው ድምቀቶች
ክሩፒ እና አሌክስ ስኮት የቼሪዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።
አዲሱ አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬሽ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ቢያሳርፍም፣ ቡድኑን ከሽንፈት ሊታደገው አልቻለም።
ይህ ሽንፈት አርሰናል ለዋንጫ በሚያደርገው ትንቅንቅ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ሲሆን፣ ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ስህተት የመስራት ዕድሉን አጥብቦበታል።
መድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት ያላቸው ተስፋ አደጋ ላይ ይወድቅ ይሆን?
አስተያያታችሁን አጋሩን
#getu #arsenal #premierleague #afc #bournemouth #footballnews #emiratesstadium #gyokeres #sportsupdate #addisababa #አርሰናል #እንግሊዝፕሪሚየርሊግ #ስፖርት #ጌጡተመስገን #getutemesgen
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሮቤ ከተማ አስተዳደር በጤና ባለሙያው ከዲር ዋቆ ላይ የድብደባ ወንጀል ፈጽሞ የተሰወረው ተጠርጣሪ እና ግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሮቤ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው በሐሰት "የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል" በማለት፤ ጓደኞቹን በማስተባበር ግለሰቡን ያስደበደበ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ትክክለኛ አስመስሎ ለማቅረብ የተጎጂውን ምስል በካሜራ ሲቀዳ እንደነበር ተገልጿል።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለ'ኦቢኤን ሳይበር ሚዲያ' እንደገለጹት፣ በሕግ አካላት በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ድብደባውን የፈፀሙ ግብረ-አበሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ኮማንደር ገመዳ አክለውም፣ የወንጀል ድርጊትን የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የፍትህ አካላት ሆኖ ሳለ፣ በቡድን ተደራጅቶ ሰውን መደብደብ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
#ethiopia #security #police

8 months ago
አርቴታ የደህንነት ስጋት አለብኝ አሉ
#ethiopia | የአርሰናሉ አለቃ ሚኬል አርቴታ ሜዳ ላይ ጨዋታን በመምራት ረገድ ብቁ ቢሆንም፣ ከሜዳ ውጭ ግን በመኪናው ውስጥ እያለ የሚገጥሙት ሁኔታዎች እረፍት ነስተውታል።
አሰልጣኙ ከደጋፊዎች ጋር መገናኘትና አክብሮት ማሳየት የሥራው አካል እንደሆነ ቢያምንም፣ የደህንነት ወሰኖች መታለፍ ግን አሳስቦታል።
የዊጋኑ ክስተት ምን ነበር?
ባለፈው እሁድ አርሰናል በኤፍኤ ካፕ ዊጋንን ድል ካደረገ በኋላ፣ በኤምሬትስ ስታዲየም አቅራቢያ አንድ አስገራሚ ክስተት ተፈጥሯል። አርቴታ እና ባለቤቱ በትራፊክ ውስጥ እያሉ፦
* አንድ ግለሰብ የአርቴታን መኪና በእግሩ ይከተል ነበር።
* ለልጁ ማሊያ እንዲፈርምለት በተደጋጋሚ ይማጸን ነበር።
* አርቴታ ግን በደህንነት ስጋት ምክንያት የመኪናውን መስኮት ለመክፈት ፈቃደኛ አልሆነም።
"ወሰኖች መከበር አለባቸው"
አሰልጣኙ ስለ ሁኔታው ሲናገር ለደጋፊዎቹ ያለውን አክብሮት ገልጾ፣ ነገር ግን ነገሮች መስመር ሲያልፉ ያለውን ስሜት እንዲህ ብሏል፦
"ሁልጊዜም አክብሮት ለማሳየት እሞክራለሁ። ፊርማ መፈረምም ሆነ ፎቶ መነሳት የሥራችን አካል ነው። ነገር ግን መከበር ያለባቸው የደህንነት ወሰኖች አሉ። በተለይ አንዳንዶች ይህንን የሚያደርጉት ለትክክለኛ ዓላማ እንዳልሆነ ሲሰማኝ ምቾት አይሰማኝም።"
በተጨማሪም ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ባለቤቱን አስመለክቶ "በሴልፊ ምክንያት ተበሳጭታለች" ተብሎ የተሰራጨው ዘገባ "የተሳሳተ እና ፍትሃዊ ያልሆነ" መሆኑን አርቴታ በግልጽ አስተባብሏል።
የክለቡ ጥብቅ መመሪያ
አርሰናል ለተጫዋቾቹ እና ለአሰልጣኞቹ ግልጽ የሆነ የደህንነት መመሪያ ሰጥቷል።
በዚህም መሠረት፦
* በስታዲየም አካባቢ መኪና በሚያሽከረክሩበት ወቅት የመኪና መስኮት መክፈት የተከለከለ ነው።
* ይህ መመሪያ የወጣው ደጋፊዎች በብዛት ተሰባስበው አደጋ እንዳይፈጥሩ ለመከላከል ነው።
አርቴታ ለእውነተኛ ደጋፊዎቹ ያለውን ፍቅር ቢገልጽም፣ የራሱና የቤተሰቡ ደህንነት ግን ቀዳሚ መሆኑን አስምሮበታል። "እውነተኛ ፍቅር ኖሯቸው ለሚመጡ ደጋፊዎች ትልቅ ክብር አለኝ፤ ነገር ግን ጥበቃ የሚያስፈልገን ጊዜ አለ" በማለት መልዕክቱን ቋጭቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #mikelarteta #arsenal #gunners #premierleague #footballsafety #emiratesstadium #ethiopia

🔴 መድፈኞቹ በኤሚሬትስ ታሪክ ሰርተዋል! አርሰናል 4 - 0 ዊጋን ⚽️🔥
#ethiopia | አርቴታ ለውጥ አምጥቷል፤ አርሰናል የኤፍ ኤ ዋንጫ 5ኛ ዙርን ተቀላቅሏል!
በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ 4ኛ ዙር ጨዋታ፣ የ14 ጊዜ ሻምፒዮኑ አርሰናል ዊጋን አትሌቲክን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
የጨዋታው ታሪካዊ ነጥቦች፦
⚡️ የመጀመርያዎቹ 30 ደቂቃዎች፦
አርሰናል በጨዋታው የመጀመርያ 30 ደቂቃዎች ውስጥ 4 ግቦችን በማስቆጠር፣ በዚህ የውድድር መድረክ ይህንን ማድረግ የቻለ የመጀመርያው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ በመሆን ታሪክ ጽፏል።
🎯 የኤዜ ድንቅ ብቃት፦
ኤቤሬቺ ኤዜ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል (2 assists)፣ ከ9 ዓመት በኋላ ይህንን ስኬት ከሄክቶር ቤለሪን በመቀጠል ያስመዘገበ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
⚽️ ግብ አስቆጣሪዎች፦
ኖኒ ማዱኬ፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ፣ ጋብርኤል ጄሱስ እና ሀንት (በራሱ ላይ) መድፈኞቹን ለድል ያበቁ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።
የአርቴታ ስልታዊ ውሳኔ፦
ከብሬንትፎርዱ ጨዋታ በኋላ በቋሚ አሰላለፉ ላይ የ8 ተጫዋቾችን ለውጥ አድርጎ የገባው ሚካኤል አርቴታ፣ ከ2019/20 የውድድር ዓመት በኋላ ክለቡን ወደ 5ኛው ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ አሸጋግሯል።
መድፈኞቹ ዘንድሮ 15ኛውን የኤፍ ኤ ዋንጫ ክብረ ወሰን ያሻሽሉ ይሆን? 🏆
#arsenal #facup #wigan #arteta #eberechieze #emiratesstadium #footballnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🔥 በ5 ጎሎች የታጀበው የኤምሬትሱ ጦርነት!
ማን ዩናይትድ 3 ነጥብ ይዞ ተመለሰ! 🔴
#ethiopia | "አርሰናል በሜዳው ተደናገጠ፤ ዩናይትድ የ23ኛው ሳምንት ኮከብ ሆነ!"
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ምሽት 1:30 ላይ በኢምሬትስ ስታዲየም የተደረገው የአርሰናል እና የማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ፤ በዩናይትድ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
⚽️ የጎል ድግስ:
የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ምቤሞ፣ ዶርጉ እና ኩንያ ከመረብ ሲያሳርፉ፤ የአርሰናልን ጎሎች ሜሪኖ እና ማርቲኔዝ (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል።
ይህ ውጤት ለዩናይትድ ትልቅ የሞራል ስንቅ ሲሆን፤ ለአርሰናል ደግሞ በሜዳው መሸነፍ ያልተጠበቀ ሆኗል።
ስለ ጨዋታው ምን ተሰማችሁ? የጨዋታው ኮከብ ማን ነበር?
#arsenal #manutd #premierleague #emiratesstadium #mbeumo #dorgu #cunha #merino #football #ethiopia

Comments