Logo
Getu Temesgen
በላሚን ያማል ላይ የተሰነዘረው አስነዋሪ የዘረኝነት ጥቃት
#ethiopia | በትላንትናው ምሽት በባርሴሎና እና በአትሌቲኮ ማድሪድ መካከል በተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ፣ የባርሴሎናው ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ኢ-ሰብአዊ ለሆነ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኗል።

በጨዋታው ወቅት በስታዲየሙ የተገኙ ደጋፊዎች ያማልን "በጣም አስቀያሚ ነህ" በማለት ሲሳደቡ የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን፣ ከዚህም ባለፈ የዘር ማንነቱን በመጥቀስ "ወደ ሞሮኮ ተመለስ" የሚሉ የጥላቻ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።

በዚህ ድርጊት ክፉኛ የተበሳጨው ወጣቱ ተጫዋች፣ ጨዋታው ሲጠናቀቅ በከፍተኛ ስሜት ውስጥ ሆኖ ሜዳውን ለቆ መውጣቱ ተስተውሏል። ላሚን ያማል ከዚህ ቀደም በስፔን ደጋፊዎች አማካኝነት በእምነት ላይ የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን በጽኑ ሲያወግዝ እንደነበር ይታወሳል።

ይህ ተደጋጋሚ እየሆነ የመጣው የዘረኝነት ድርጊት በስፔን እግር ኳስ ላይ ጥቁር ነጥብ እየጣለ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #lamineyamal #notoracism #fcbarcelona #laliga #footballnews #humanrights #stopracism #barcelona #atleticomadrid

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.