1 month ago
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች ከሁለት አሥርታት በኋላ በሐዋሳ ከተማ ዳግም ተሰባሰቡ
#ethiopia | "አንለያይም" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የቀድሞ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ዳግም የመገናኘት መርሃ ግብር በሐዋሳ ከተማ ለሦስት ቀናት እየተካሄደ ይገኛል።
ለዚህ ታሪካዊ ሁነት ከ200 በላይ ተመራቂዎች ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎችና ከሀገር ውስጥ ከተሞች ወደ ስፍራው ያመሩ ሲሆን በውጭ ሀገር የሚገኙ ተሳታፊዎች ደግሞ በዩቲዩብ ቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብሩን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
የቀድሞ ተማሪዎቹ ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ ከተማዋ በመመለስ ትዝታቸውን በማደስ ላይ ናቸው።
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ኢትዮጵያዊነት በጋራ ራዕይና ኃላፊነት የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ታደሰ አክለውም ከተማዋ በደማቅ እንግዳ ተቀባይነት ስሜትና በተከናወኑ የልማት ሥራዎች አምራ ተመራቂዎችን የተቀበለች መሆኑን በመግለጽ የከተማዋን ውበት በአካል እንዲያጣጥሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ተመራቂዎቹ በሦስት ቀናት ቆይታቸው የተለያዩ መርሃ ግብሮችን የሚያከናውኑ ሲሆን በዕለቱ አመሻሽ ከሳውዝ ስፕሪንግ ጀምሮ የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶችንና ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በእግር ጉዞ ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም የ1998/1999 ዓ.ም ተመራቂዎችን የዩኒቨርሲቲ ቆይታ የሚያስታውስ አንለያይም የተሰኘ መጽሐፍ ለምረቃ ይበቃል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የሀገር መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ተመራማሪዎችና ባለሀብቶች ተገኝተው ልዩ ቆይታ እያደረጉ ይገኛሉ።
#hawassa #hawassauniversity #alumni #ethiopiannews #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

3 months ago
የጅማ ዩኒቨርሲቲው ምሩቅ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ለዩኒቨርሲቲው የ10 ሚሊዮን ብር ፋብሪካ በነጻ ሊተክል ነው
#ethiopia | የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪና የ“ቤጃይ ኢንዱስትሪያል ኤንድ ኢንጂነሪንግ ሶሉሽንስ” መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ለተማረበት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በነጻ ሊተክል መሆኑ ተሰማ።
ዩኒቨርሲቲው “ስኬታማና ጀግና ልጅ” ሲል የገለጸው ኢንጂነር ቢጃይ በራሱ ድርጅቱ የሚመረተውን ይህንን ዘመናዊ ፋብሪካ ለተቋም በስጦታ ከመስጠቱም ባሻገር በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎችንም እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁ ተቋም በኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላ በትምህርቱ በመግፋት የማስተርስ ዲግሪውን የሠራው ኢንጂነር ቢጃይ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ 24 ንዑስ ተቋራጮችን ያሳደገና የ10 ሚሊዮን ብር የኢኮኖሚ ሽልማት ያሸነፈ ስኬታማ የኢንዱስትሪ መሪ ነው።
በአሁኑ ወቅት በቡርኪናፋሶ ዘመናዊ የሳተላይት ማምረቻ ተቋም ለመገንባት ታላቅ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ኢ/ር ቢጃይ ለዩኒቨርሲቲው ካደረገው ሰፊ ድጋፍ ጎን ለጎን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች (Alumni) በሙሉ በይፋ ተመዝግበው ከተቋሙ ጋር እንዲገናኙ ጥሪ አቅርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

6 months ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁንን የአመቱ ምርጥ ሲል ሰየመ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ7ኛው የምርምር ጉባዔው በተለያየ ዘርፍ የአውቅና ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ኮሌጁ የዓመቱ ምርጥ የቀድሞ ተመራቂ (Alumni) ሆኖ የተመረጡት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን ናቸው፡፡
ዶ/ር ዮሀንስ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና (Doctor of Medicine) ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፣ በትምህርትና በተግባር ዘርፎች ከፍተኛ ብቃት አሳይተዋል።
በኢንተርንሺፕ የተግባር ልምምድ ግዜአቸው በተለያዩ ሙያዊ ክፍሎች ሰፊ የክሊኒካል ልምድ በማግኘት፣ በታካሚዎች እንክብካቤ እና በሕክምና ውሳኔ ሂደት ንቁ ተሳትፎ አድርጎዋል።
ከሁሉ በላይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያደረጉት አገልግሎት በኒራቅ ጤና ጣቢያ እንደ አጠቃላይ ሐኪም፣ ከመደበኛ ሕክምና ተግባራቸው በተጨማሪ ዝቅተኛ ወጪ ያለው የሚጠቅም ፈጠራ አቀረበዋል፤ ይህም ተጣጣፊ የሆነ በግድግዳ ላይ ተለጣፊ የህጻናት የድንገተኛ አልጋ እና ከርሱ ጋር የተያያዘ የአስተማሚ መቀመጫ፣ ከተቀናጀ መደገፊያ እና የሚነቀል አነስተኛ የሂደት መሳሪያ ትሬይ ጋር የተያያዘ፣ ኮሎስቶሚ አፕሊያንስና የተሻሻለ እስፓይካ ቴብል ነው።
ይህ የፈጠራ ስራ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽና እንዲሻሻል አስተዋጻኦ አድርገዋል። ከሕክምና አገልግሎታቸው በተጨማሪ፣ በ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመታገዝ በማህበረሰቡ ውስጥ ትምህርትንና ፈጠራን ለማበረታታት “መቅድም ቤተ መፃህፍት እና የፈጠራ ማዕከል” መመስረት ችለዋል።
በሙያቸውና በፈጠራ ስራቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን የዓመቱ ምርጥ አልሙናይ (የቀድሞ ተመራቂ) እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

8 months ago
🏫 "ትምህርት ቤቴን አድሳለሁ!" — ለይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የመልሶ ግንባታ ጥሪ! 🌳✨
#ethiopia | ይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት፤ የሀገር ዋርካ የሆኑ አንቱ የተባሉ ምሁራንን፣ ሚኒስትሮችን፣ ደራሲያንንና ጋዜጠኞችን ያፈራ የዕውቀት ማዕከል ነው።
ከታላቁ ደራሲ ደበበ ሰይፉ እስከ ስፖርት ጋዜጠኝነት ፈር ቀዳጁ ገነነ ሊብሮ፣ ከዶ/ር አብርሃም ፈለቀ እስከ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ድረስ የዚህ አንጋፋ ትምህርት ቤት ፍሬዎች ናቸው።
ለምን ጥሪ ተደረገ?
በ1963 ዓ.ም ማስተማር የጀመረውና በተፈጥሮ ውበቱ የሚታወቀው ይህ ትምህርት ቤት፤ አሁን ካለንበት ዘመን ጋር በሚመጥን መልኩ ተሻሽሎ ለአዲሱ ትውልድ ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆን ታላቅ የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ተይዟል።
ጥሪው ለማን ነው?
🎓 በዚህ ትምህርት ቤት የተማራችሁ የቀድሞ ተማሪዎች (Alumni)
👨🏫 ያስተማራችሁና የምታስተምሩ መምህራን
💰 የይርጋዓለም ተወላጅ የሆናችሁ ባለሀብቶችና ወጣቶች
🌍 በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የይርጋዓለም ወዳጆች በሙሉ
የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር እምባቆም ዼጥሮስ እና የዞኑ አስተዳደር ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፤ ትምህርት ቤቱን በቋሚነት ራሱን እንዲያስተዳድርና ዘመናዊ እንዲሆን በምናደርገው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ተጋብዘዋል።
ትናንት የዕውቀት ብርሃን የፈነጠቀልንን ቤት፣ ዛሬ ተረክበን እናድሰው!
መላኩ ይርጋለም
#yirgalemsecondaryschool #educationethiopia #schoolrenovation #yirgalem #sidama #givingback #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
🎓 የነፃነት ጮራ!
ለ60 ዓመታት ትውልድ የቀረፁት መምህር ጠምቀ...
#ethiopia | ከአክሱም ማይብራዚዬ ገዳም የቤተ ክህነት እውቀት እስከ ጎንደር ዘመናዊ ትምህርት... ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በ1957 ዓ.ም በቄራ እና ጎፋ አካባቢ "የነፃነት ጮራ ትምህርት ቤትን" የመሰረቱት ታላቁ አባት!
መምህር ጠምቀ፤ ትምህርት ቤታቸው በደርግ ዘመን ቢወረስም፤ ዓላማቸውን ግን ማንም አልወረሰባቸውም።
በፅናት እና በታማኝነት መምህርነትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ ሕይወት ተልዕኮ በመቁጠር በርካታ ሀኪሞችን፣ ኢንጂነሮችን፣ ጋዜጠኞችን እና ተመራማሪዎችን አፍርተዋል።
ልዩ የክብር መርሐግብር!
እኚህን በሕይወት ያሉ ታላቅ ባለውለታ ለመዘከር እና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማክበር፤ በቀድሞ ተማሪዎቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት ልዩ ዝግጅት ተሰናድቷል።
📅 ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም
በዕለቱ ምን ይጠበቃል?
📘 የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክረው "የትምህርት ጮራ" የተሰኘ ባለ 80 ገጽ መጽሐፍ ይመረቃል።
🎙 ከትምህርት ባልደረቦቻቸው እና ከተማሪዎች ጋር የፓናል ውይይት ይደረጋል።
🎖 የትምህርት ቢሮ እና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ምስጋና ይቀርባል።
በሕይወት እያሉ ባለውለታዎቻችንን እናክብር!
የነፃነት ጮራ ፍሬዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
#netsanetchora #school #education #teachertemke #tribute #addisababa #kera #gofa #ethiopia #alumni #education #hero #teacher #netsanetchora #thankyouteacher

11 months ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቀረበ
#ethiopia | “ያለፈውን በማክበር የተሻለ ነገን ማለም” (Honoring Our Past Reimagining Our Future) በሚል መሪ ቃል 75ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹን (Alumni) ወደ “ቤታችሁ ኑ’ በሚል መርህ ከታህሳስ 18-24፤ 2018 ዓ.ም. ለተዘጋጀው ፕሮግራም በመላው አለም ለሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቀረበ።
75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በያዝነው ህዳር እና ታህሳስ ወር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚያከብር ዛሬ ህዳር 18፣ 2018 በዩኒቨርሲቲው ግቢ በተሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫውን የሰጡት ዶ/ር መሳይ ገ/ማርያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሉምናይ ቢሮ ዳይሬክተር፣ ወ/ሮ ሀና ደምሴ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚዲያ አማካሪ እንዲሁም ዘሪሁን ብርሃኑ (ረ/ፕ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ት/ት መምህር እና የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚዲያ አማካሪ ናቸው። 75ኛ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓሉን በተመለከተ ዛሬ እና ነገ (ህዳር 18 እና 19) ከሚደረገው የባለ ድርሻ አካላት ውይይት እንዲሁም ቅዳሜ ህዳር 20 ከሚጀምረው የዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ውድድር ጀምሮ በርካታ ፕሮግራሞች ተሰናድተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን የ75 ዓመታት ጉዞ እና ታሪክ የሚሰንድ መፅሀፍ በዩኒቨርሲቲው እውቅ ምሁንራ የሚዘጋጅ ሲሆን በዋናነት ዩኒቨርሲቲው ያለፈበትን የሰባ አምስት ዓመታት ታሪክ ይዘክራል።
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በዘመን ጉዞ ውስጥ፣ በክፍል ውስጥ ከሚደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶች ባሻገር በሀገሪቱ ተለዋዋጭ የፖለቲካ እና የታሪክ ለውጦች ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ ሚና አጉልቶ የሚያሳይ፣ አሁን የደረሰበትን የራስ ገዝነት አቋም እና ሁኔታ እንዲሁም ወደፊት ለመጓዝ የተለመውን መንገድ በሰፊው የሚያስቃኝ ዶኩመንታሪ እየተዘጋጅ ይገኛል።
ከነዚህ የታሪክ ስነዳዎች ባሻገር መነሻውን አራት ኪሎ አድርጎ እስከ ዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የሚደረግ የእግር ጉዞ የሚኖር ሲሆን ጉዞው ከቦታ ዳሰሳ ባሻገር የዩኒቨርሲቲውን ሰፊ ታሪክ የሚያይሳዩ የተለያዩ የቴአትር፣ ሙዚቃ፣ ስዕል ፣ ትረካ እና ልዩ ልዩ የጋራ የክዋኔ እንቅስቃሴዎች ይኖሩታል።
በተጨማሪም በተማሪዎች መሃል የሰባ አምስት ዓመት ልቀት በሰባ አምስት ሰኮንዶች (75 years of excellence in 75 seconds) የተሰኘ ሽልማት የሚያስገኝ የአጭር ፊልም ውድድር የሚኖር ሲሆን ተማሪዎች ውድድሩ ተርማሪዎች ስለዩኒቨርሲቲው ያላቸውን ግንዛቤ ያሰፋል፣ ሃሳባቸው ኪነጥበባዊ መንገድን በመጠቀም እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ያግዛቸዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ተማሪዎችን እና የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንዲሁም ሰፊውን ባለ ድርሻ አካላት የሚያሳትፉ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በምርምር የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ተከታታይ ፓናል እና ኮንፈረሶችም የዝግጅቱ አካላት ናቸው።
በተከታታይ በሚደረጉ የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና ፓናል ውይይቶች የሚቀርቡ ጥናቶች የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጪም ለሚገኙ ሁሉ ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ የሚቀርቡት ርዕሰ ጉዳዮችም ከአካድሚያዊ የምርምር ርዕሰ ጉዳዮች ባሻገር በሀገራዊ አንገብጋቢ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹን ዳግም ማግኘት እና መወያየት እንደሚፈልግ የገለፁት አሰናጆቹ በመላው ዓለም የሚገኙ ማንኛውም የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በ https://alumni.aau.edu.et/... ድረ ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ በመገለጫው ጥሪ ተደርጓል።
በተለይ ደግሞ ከታህሳስ 18 እስከ 24 ለአንድ ሳምንት በሚደረገው የአልሙናይ ሳምንት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደግሞ ልዩ የሆነ መመዝገብያ QR code የተዘጋጀ ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫውም ይፋ ተደርጓል።

Sponsored by
Surafel
Comments