22 hours ago
የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ነገር ...
#ethiopia | በኢትዮጵያ አፋር ክልል በዳናኪል ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውና ሁልጊዜም ንቁ የሆነው የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ላቫ ሀይቅ በሳይንቲስቶችና በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ይገኛል።
ሦስቱ አህጉራዊ የመሬት ንጣፎች የሚገናኙበትና የሚራቀቁበት ይህ ስፍራ፣ አህጉራት እንዴት እንደሚከፈሉና የምድር የውስጥ ሙቀት እንዴት እንደሚገለጽ የሚያስረግጥ ህያው የተፈጥሮ ቤተ-ሙከራ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ በባሳልቲክ ድንጋይ የተገነባው እሳተ ገሞራ የማይቋረጥ የላቫ ሀይቅ የሚገኝበት ሲሆን፣ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ሙቀት፣ በጨው ሜዳዎችና በጂኦተርማል እንቅስቃሴዎች የተከበበ በመሆኑ ለአካባቢው ልዩ የተፈጥሮ ውበት ሰጥቶታል።
ስፍራው አስቸጋሪና ሞቃታማ የአየር ንብረት ያለው ቢሆንም፣ ከዳሎልና ከአሳሌ ሀይቅ ጋር በመሆን የሀገሪቱን የጂኦ-ቱሪዝም መስህብ ከፍ አድርጎታል።
በተጨማሪም በዚሁ አካባቢ የሚገኘው የስምጥ ሸለቆ ተፈጥሮአዊ ሀብት የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ተጠቅሷል።
ዩኔስኮ ለስፍራው ገና ይፋዊ እውቅና ባይሰጥም፣ ለወደፊቱ የጂኦፓርክ ልማት ተስፋ ካላቸው ቀዳሚ ቦታዎች አንዱ አድርጎ ለይቶታል።
ለዚሁ እውቅና በዕጩነት ከተያዙት የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ፣ በውብ ቀለማትና በፍልውሃ ምንጮች ያሸበረቀው ዳሎል፣ ከባህር ወለል በታች 120 ሜትር ዝቅ ብሎ የሚገኘው የዳናኪል ዝቅተኛ መሬት፣ የዘመናት የጨው ማውጣት ባህል የሚከናወንበት የአሳሌ ሀይቅ፣ የአፍደራ ሀይቅ እና የሉሲ አፅም የተገኘበት ታሪካዊው የአዋሽ ታችኛው ሸለቆ ይጠቀሳሉ።
ይህ ስፍራ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ማግኘቱ ድንቅ የሆኑ የስነ-ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ፣ ዘላቂ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተሳትፎና የሥራ ዕድል ለማሳደግ እንዲሁም ለሳይንሳዊ ምርምሮችና ለትምህርት ዘርፍ የጎላ ጥቅም ያበረክታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ertaale #afar #geopark #unesco #danakildepression #ethiopiantourism #volcano #geology #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments