6 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) በኢትዮጵያ የሄማቶሎጂ እና ኦንኮሎጂ ማህበር (ESHO) ስድስተኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ... የስብሰባው አዳራሽ ድባብ ቅጽበታዊ በሆነ ስሜት ተውጦ ነበር። ሳይንሳዊ ቀመሮች፣ የፖሊሲ ሰነዶች እና ደረቅ ስታቲስቲካዊ መረጃዎች ብቻ ይንሸራሸሩበት የነበረው ይህ መድረክ፤ በኮሚሽነር ለሊሴ ዱጋ ህያው ድምጽ አዲስ መንፈስ ዘራ። ኮሚሽነሯ ወደ መድረኩ ብቅ ብለው በራሳቸው የህይወት መስታወት ውስጥ ያዩትን የካንሰር ፈተና እና የትግል ጉዞ ማውሳት ሲጀምሩ... አዳራሹ በረቀቀና ጥልቅ በሆነ ጸጥታ ተዋጠ።
ያቺ ቅጽበት የፖለቲካ ንግግር የምትደመጥበት አልነበረችም፤ የህክምና ሳይንስ ማብራሪያም አልተሰጠባትም። ይልቁንም፣ ከእውነተኛ የህይወት ጓዳ የተቀዳች፣ የጀግንነት፣ የመንፈስ ፅናት፣ የጥርጣሬ፣ የፍርሃት እና የብርሃናማ ተስፋ ውህድ የሆነች ጥልቅ የሰው ልጅ ታሪክ ነበረች። በጉባኤው የታደሙት የህክምና ባለሙያዎችም ሆኑ እንግዶች፣ በእያንዳንዱ የኮሚሽነሯ የቃላት ትንፋሽ ውስጥ የካንሰር ታማሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው በየዕለቱ የሚያልፉበትን የሰቆቃ እና የተስፋ ትግል አዩበት። እያንዳንዱ የካንሰር ምርመራ ውጤት ከህክምና ወረቀት እና ከቁጥር ባለፈ፣ ደምና አጥንት ያለውን ሰው፣ አንድን ሙሉ ቤተሰብ፣ እና ለዘላለም የሚቀየርን የህይወት ምዕራፍ አዝሎ እንደሚመጣ በጉልህ ታየ።
የኢትዮጵያ የሄማቶሎጂ እና ኦንኮሎጂ ማህበር በጽኑ እንደሚያምነው፣ በካንሰር ህክምና ዘርፍ ውስጥ እውነተኛ እና ትርጉም ያለው ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የህክምና ሳይንስ፣ የጤና ፖሊሲ እና የታማሚዎች የህይወት ተሞክሮ በአንድነት ሲገመዱ ብቻ ነው። የኮሚሽነር ለሊሴ ድምጽ ደግሞ ለዚህ ታላቅ ውህደት ወሳኝ ማገር ሆኗል። ኮሚሽነሯ ባሳዩት ወደር የለሽ ግልጽነት እና ባደረጉት የማያወላውል ጥብቅና (Advocacy)፣ የካንሰርን ትግል ከሆስፒታል ጠባብ ክፍሎች እና ከዝግ የስብሰባ አዳራሾች በማውጣት፣ የህዝብ የውይይት መድረክ እና የጋራ አጀንዳ እንዲሆን አድርገውታል።
አንዳንዶች ለበጎ አላማ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፤ ጥቂቶች ደግሞ ታላቅ የለውጥ ንቅናቄን ይፈጥራሉ። ኮሚሽነር ለሊሴ ዱጋ በእርግጥም በኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና ታሪክ ውስጥ ብሩህ ለውጥን እያመጡ ካሉ እና የማይፋቅ አሻራቸውን እያኖሩ ካሉ ታላላቅ የለውጥ አርበኞች ተርታ በክብር ትሰለፋለች። ለነበራት የልብ ወኔ፣ ለማያቋርጥ ጥብቅናዋ እና አነቃቂ ለሆነው የለውጥ ድምጿ፣ ማህበረሰቡ እና የህክምናው ዘርፍ ልባዊ አክብሮቱን እና ጥልቅ ምስጋናውን ያቀርባል።

2 months ago
የ “ዝክረ-ፊደል” መርሐግብር አርብ ይደረጋል
የ”ዝክረ-ፊደል” መድረክ ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ አርብ ሚያዚያ 16/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
መድረኩን በተከታታይ ዓመታት እያዘጋጀ የቀጠለው የኢትዮጵያ ማኅበራዊ አጋርነት አበረታች (Ethiopia Social Partnership Advocacy) ሀገር በቀል ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዘካሪያስ አምደብርሃን እንደገለፁት ዝግጅቱ የኢትዮጵያ ፊደልን ሁለገብ አበርክቶ በመዳሰስ፤ ከማኅበረሰባዊ መገለጫነቱ አኳያ ዓይነተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
በዘንድሮ መርሐግብር ላይ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡
ፊደል ሁለንተናዊ ሉዓላዊነታችንን በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የነበረውንና ያለውን ሚና በተመለከተ በፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያስ የኢትዮጵያ ፊደል ከፀረ-ቅኝ ግዛት ተፅዕኖ የመላቀቅ ተምሳሌትነቱን በፕሮፌሰር አየለ በከሪ፤ ፊደል እንደታሪክ መዝገብነት ምን አበረከተ !የሚለውን በመምህር ዳንኤል ሰይፈ ሥላሴ፤ የኢትዮጵያውያን ፊደል በሌሎች ንፅረተ-ፊደላት ምልከታ በዶ/ር አበባየሁ መሰለ፤ በእለቱ ከሚቀርቡ ጥናታዊ ገለፃዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የፓናል ውይይትና የእውቅና መርሐግብርም ይኖራል፡፡ “በዝክረ ፊደል” በዝግጅት ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ታዳሚያን አርብ ሚያዚያ 16/2018 በወመዘክር አዳራሽ መገኘት እንደሚችሉም ተገልፆአል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም በእለቱ ተገኝተው የዘገባ ሽፋን እንዲሠጡ ጥሪ ቀርቧአል፡፡

3 months ago
የሲሲአርዲኤ (CCRDA) የ53 ዓመታት የልህቀት አሻራ
የሲአርዲኤ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ለውጥና ልማት ላይ የሚሰራ አንጋፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት (ኮንሶርትየም) ሲሆን፣ ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመናት በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ አሻራ አሳርፏል።
እ.አ.አ በ1973 በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረሃብ ወቅት፣ የእርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለማከናወን በልበ ቀናዎች የተመሰረተ ተቋም ነው።
ዛሬ ላይ የ53 ዓመታት የልህቀት እና የለውጥ ጉዞን አስቆጥሯል።
ራዕይ፦
ድህነት ተወግዶ ማየት።
ተልዕኮ፦
ማህበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ከአባላት ጋር በትጋት መስራት።
በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባላቱም በሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በሚከተሉት ዘርፎች ይሰማራሉ፦
ሰብዓዊ ድጋፍ እና ጤና
ልጆች፣ ወጣቶች እና ስነ-ፆታ
አካባቢ ጥበቃ እና የውሃ ንፅህና
ኤች አይ ቪ መከላከል
መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ
ሲሲአርዲኤ አባላቱ ተሞክሮ የሚለዋወጡባቸው መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በፖሊሲ ውትወታ (Advocacy) እና በሀብት ማሰባሰብ ረገድ የአባላቱን ተፅዕኖ የማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
𝐅𝐚𝐜𝐞𝐛𝐨𝐨𝐤: https://web.facebook.com/c...
𝐋𝐢𝐧𝐤𝐞𝐝𝐈𝐧: www.linkedin.com/in/ccrda-...
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦: https://t.me/ccrda_et
𝐘𝐨𝐮𝐓𝐮𝐛𝐞: https://www.youtube.com/@c...
𝐗 (𝐓𝐰𝐢𝐭𝐭𝐞𝐫): https://x.com/CCRDA454972
𝐖𝐞𝐛𝐬𝐢𝐭𝐞: https://ccrdaeth.org/
#ccrda #ሲሲአርዲኤ #ethiopia #ngos #civilsociety #development #socialjustice #53yearsofservice #impact #humanitarianaid #policyadvocacy #communitydevelopment #ethiodevelopment

9 months ago
የግብረ ሰናዩ ላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እና ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን
#ethiopia | COVID 19 - ኮሮና ከነጠቀን ባለአበርክቶዎች ኢትዮጵያውያን የጤና ዘርፉ ሻምፒዮኖች መካከል የላየንስ ክለብ አለም አቀፍ ማህበር ዐብይ ተልዕኮ ፈፃሚው ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን አይዘነጉም።
እኔ ሳውቃቸው ትኩረት በሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች በተለይም የዓይን ማዝ (Trachoma) እና ጊኒ ዎርምን ጨምሮ በወባ መከላከል፥ቁጥጥር እና በሕክምና ከነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ ነው።
በተለይም በአማራ ክልል የትራኮማ (Trachoma) ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወባም (Malaria) እንዲሁ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ስለነበር ሁለቱን በሽታዎች ባቀናጀ በካርተር ሴንተር የሕብረተሰብ አቀፍ የጤና ቁጥጥር ፕሮጄክት (Mal-Tra)ጉልህ ድርሻ ነበራቸው።
በዚህ ረገድ ሎሬቱ ከቲ.ኤፍ. ግሎባል ሄልዝ (Taskforce for Global Health) የአፍሪካ ተጠሪ ከዶ/ር ተሾመ ገብሬ እና ከካርተር ሴንተር የኢትዮጵያ ተጠሪ ከዶ/ር ዘሪሁን ታደሰ ጋር በአጋርነት የከወኑትን አካትቼ በሰፊው እመለስበታለሁ።
ዛሬ ላይ ይህ የላየንስ ክለብ እንቅስቃሴ እንዴት ነው?
"እናገለግላለን" (We Serve) የሚል መሪ ቃልን አንግቦ ነው የተነሳው።
በሕብረተሰብ አገልግሎት ልቆ ለመገኘት ሰውን በጥልቅ የልብ ፍቅር መውደድ ይሻል።
በኢትዮጵያ ላየንስ ክለብ የግብረ ሰናይ ስራ ከጀመረ ከስድስት አስርት አመት በላይ ሆኖታል።
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ነፍስኄር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከላየንስ ክለብ ኢትዮጵያ አምስት የቻርተር አባላት አንዱ ነበሩ።
ለዓይነ ስውርነት የሚዳርጉ በሽታዎችን ለምሳሌ በዓይን ማዝ (Trachoma)፥ በዓይን ሞራ ግርዶሽ Cataract)፥ በውሃ ወለድ መዘዝ የዓይነ ስውርነት (River blindness) በሽታዎች ለሚሰቃዩ ቅድሚያ በመስጠት በሕክምና ጥበብ እይታቸው እንዲመለስና ወደ አዲስ የተሻለ ሕይወት እንዲሸጋገሩ ማድረግ የግብረሰናይ ተልዕኮው ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ ነው የቆየው።
እነኚህን በሽታዎች በዘላቂነት ለመከላከል ከእህት የላየንስ ክለቦች፥ ከካርተር ሴንተር፥ ከኢንተርናሽናል ትራኮማ ኢኒሺዪቲቭ፥ ከክሪስቶፌል ብላየንድነስ ሚሽን እና ከሌሎችም አጋሮች ጋር በመሆን የ2ኛ ደረጃ የዓይን ሕክምና አገልግሎትን በማስፋፋት የጤና ዘርፉን ሲደግፍ ቆይቷል።
በቀዶ ሕክምና ዜጎች በተለይ አቅመ ደካሞች የዓይን ብርሃንቸው ተነጥቀው እንዳይቀሩ ብሎም 2ኛ ደረጃ የዓይን ማዕከላት በባህርዳር፥ ደብረ ብርሃን፥ አርባምንጭና ጅግጅጋ መቋቋማቸውን የድርጅቱ ሰነድ ያመለክታል።
የመንግስት ሆስፒታሎችን አቅም በማሳደግ ረገድ ራስ ደስታ፥ ልዕልት ዘነበወርቅ ሆስፒታል፥ ራስ ደስታና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።
60 አመታትን ያስቆጠረው ላየንስ ክለብ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ የስኳር ሕሙማን ማዕከል እንዲቋቋምም አድርጓል።
ላየንስ ክለብ በኢትዮጵያ ሕብረተሰባዊ ምግባረ ሰናይ ተግባሩ እንዲጠናከር አባላት በማፍራት ያለበትን ውሱንነት በመቅረፍ የአባላት ማቀፍ እድሎችን ማስፋፋት እንደሚያሻ የክለቡ የኢትዮጵያ አመራሮች በአፅንኦት የሚያነሱት ነው።
ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የቆዳ ሕክምና ስፔሻሊስቶች (Dermatologists) መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የቆዳ፣ የስጋ ደዌ፣ የአባላዘር፣ የትራኮማ እና ሌሎች ችግሮች የት የሃሩራማ በሽታዎች ቁጥጥር ላይ በተለይም በአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ የሕብረተሰብ ጤና ትኩረት እንዲያገኝ ወሳኝ አካላትን በማግባባት (በ-advocacy) ሚናቸው ታላቅ እንደነበር ለዘርፉ ባለኝ ቅርበት ምስክር ነኝ።
ከሐኪምነታቸው በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌ፣ እርዳታ አስተባባሪ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል፣ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባል እና በብዙ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ጥቅምት 22 ቀን በ1941 ዓ.ም በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት፣ ሐረር ከተማ የተወለዱት ዶ/ር ጥበበ ትምህርት የተከታተሉት በአዲስ አበባ ሽመልስ ሀብቴ ት/ቤት ነው።
አባታቸው ሻለቃ የማነብርሃን ወ/ሥላሴ በጦር ሰራዊቱ መኮንን ስለነበሩና የሚታየው ዲሲፕሊንና አለባበስ ከስካውት (Scout) ዲስፕሊንና አለባበስ ጋር የሚቀራረብ ስለነበር ጥበበ በዚያ ተማርከው የስካውት ክበብ አባል ሆነዋል።
ጥበበ 8ኛ ክፍልን ሳሉ የተቸገሩ ልጆችን በት/ቤቱ አካባቢ አይተው ከጓደኞቻቸው ጋር ተማከሩና ከድርሻ የኪስ ገንዘባቸው ቀንሰው በማጠራቀም ሞከሩና፤ ኋላም ‹‹የ10 ወንድማማቾች ማኅበር›› የተባለ ማኅበር መሰረቱ።
የጦር ሰራዊት እና የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድኖችን ጋብዘው ስራዎቻቸውን ለተማሪዎች እንዲያሳዩ በማድረግ ከዚያ የሚገኘውን ገንዘብ ለችግረኛ ተማሪዎቹ እንዲሰጥ መላ ዘየዱ።
ከዝግጅቶቹ ያገኙት ገንዘብ የተማሪዎቹን የምግብና የደንብ ልብስ ወጪ ለመሸፈን አስቻላቸው።
ይህ የበጎ ፈቃደኝነት ጥረት ተጠናክሮ ከተደገፉት ተማሪዎች ውስጥ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተምረውና ትልቅ ደረጃ ደርሰው በምዕራባውያኑ ባህር ማዶ ሀገራት የሚኖሩም አሉ።
ጥበበ በልጅነታቸው ዲፕሎማት የመሆን ምኞት የነበራቸው ቢሆንም እናታቸው ታመው ሆስፒታል የገቡበት አጋጣሚ ግን የጥበበን ፍላጎትና የሕይወት መንገድ ቀየረው።
እናታቸው ታመው አሁን ጦ/ኃይሎች ሆስፒታል ከሚባለው የልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል ገቡ።
የእናታቸውን ቀዶ ሕክምና በስኬት ያከናወኑትን ኢትዮጵያውያን ዶክተሮችን (ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ ፕሮፌሰር ታዬ መኩሪያንና ሌሎች ሐኪሞችን) ሲመለከቱ ሐኪም የመሆን ምኞት አሸነፋቸውና ሃሳብ ቀየሩ።
ከዚያም የሩስያ ወዳጅነት ማኅበር የትምህርት እድል ሲሰጥ ጥበበ እድሉን አግኝተው ወደ ሩሲያ ሄደው ለ6 አመታትየሩስያ ቋንቋና የሕክምና ትምህርትን ተምረው በማዕረግ አጠናቀዋል።
በቆዳ ሕክምና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪያቸውንም አገኙ፤ የአለም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርትን ማከላቸው ለኋላው ዲፕሎማሲን ለሚሻው የጤና ልማት የማግባባት አድቮኬሲ ስራ ብዙ እንዳገዛቸው መገመት ይቻላል።
ዶ/ር ጥበበ ከ1972 እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በሉቮቭ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በአማካሪ ስፔሻሊስትነትና ተባባሪ ፕሮፌሰርነትም አገልግለዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የመላው አፍሪካ የሥጋ ደዌ ማገገሚያና ስልጠና ማዕከል (All Africa Leprosy Rehabilitation & Training Center - ALeRT) ዋና የቆዳ ሐኪምና የክፍሉም ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
የዶ/ር ጥበበ ከተሳተፉባቸው ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን (Lions Clubs International) ነው።
በዚህ ክለብ ተሳትፏቸው በተለይ አፍለኛ የዓይን ማዝ ቁጥጥር (control of active trachoma) እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ (cataracts) ሕክምና እንዲሁም የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምና (trachomatus trichiasis) ላይ ሳይጠቀሱ አይታለፍም።
ትኩረት ከሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች አንዱ የጊኒ ወርም በሽታ ሲሆን ከጊኒ በመወገዱ የኢትዮጵያ ዎርም ተብሎ ስም ለውጥ እንዳይደረግ ያሰጋል።
እናም ይህን በሽታ ለማጥፋት በተያዘ ፕሮግራም የበጎ ፈቃድ አምባሳደርም ሆነው አገልግለዋል።
ሎሬት ዶክተር ጥበበ የሎሬትነት ማዕረግን ያገኙት ከሰሜን አሜሪካ ነው።
የዓለም ሎሬቱ ዶ/ር ጥበበ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል። እንደውም በአንድ የሽልማት ሁነት ላይ እንዲህ እል:-
"… ማንም ሰው የትም አገር ሄዶ ሽልማት ሊሸለም ይችላል፤ በአገሩ የተሸለመው ሽልማት ግን ታላቁ ነው ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ትልቁ ሽልማቴ በ2002 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሰጠኝ የክብር ዶክትሬት ነው"።
በዓለም የጤና ድርጅት፣ በዓለም ባንክ፣ በብሪታኒያና አሜሪካ የቆዳ ሕክምና ማህበርና አካዳሚ፣በዓለም አቀፍ የቆዳ ሕክምና ማኅበር፣ በአፍሪካ የኤድስ (AIDS) መከላከል መርሃ ግብር፣ በዊልያም ዱ ቦይስ የአፍሮ-አሜሪካ የምርምር ተቋም እንዲሁም በሌሎች ተቋማትም አገልግለዋል።
ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቩላድሚር ፑቲን ዘንድ ለሩሲያም ሆነ ለቀሪው ዓለም መልካም ተግባር ላከናወኑ ሰዎች የሚሰጠውን ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ከ39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ጋር በ-Carter Center እና ሎሬቱ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጥምረት አማካይነት ሰፊ የጤና ልማት ስራ ስለመከናወኑ በብዙ የመስክ ስራዎች ራሴም ተገኝቼ መሬት የነካ ሃቅ መሆኑን ታዝቤያለሁ።
‹‹ገና ላሳካው ፈልጌ ያልፈጸምኩት ብዙ ቀሪ ክንውኖች አሉኝ›› ሲሉ የነበሩት ሎሬት ዶ/ር ጥበበ ዓለምን ባርበደበደው ኮሮና በሽታ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በቺካጎ ከተማ የዛሬ110 አመት ገደማ ላየንስ ክለብ የተመሰረተው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን አባላትን በማቀፍ በ183 ሀገራት ውስጥ ከ43,300 ክለቦች በላይ በ714 የአገልግሎት ማስተባበሪያ አውራጃዎች ተቀናጅቶ እየተመራ ነው።
ክለቦቹ ከመደበኛ ማህበራዊ ስብስብነት በላይ አባላቱ ተልኳቸው ጊዜያቸውን፥ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን አቀናጅተው ለበጎ ምግባር በማዋል እርዳታናድጋፍ የሚሹትን የሕብረተሰብ ክፍሎች መታደግ ነው።
........
(Composed by:- Eshetu Geletu - Public health advocate & Champion of NTDs Control)

10 months ago
እኔ አዜብ አታሮ አደሬ ነኝ፣ የኢትዮጵያ ኤርትራ ልዩ ፍላጎት ማህበረሰብ—EESNC መስራች። በዚህ ዓመት፣ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ማህበረሰቦቻችን ውስጥ ያሉ በአውቲዝም እና በእድገት ችግር ለተጠቁ ልጆች፣ ወጣቶች እና አዋቂዎች ድጋፍ ለመስጠት ከ Grand African Run ጋር በመተባበር እንሰራለን።
የሚያስደስተው ነገር ይሄ ነው.፡ በእኛ ሥም ቢመዘገቡም ክፍያዎ 25%ቱ በቀጥታ ለእኛ ለEESNC ይሄዳል ለአሳዳጊዎች ስልጠና፣ ለወጣቶች እና አዋቂዎች ፕሮግራሞች፣ እና ለቤተሰቦች ጥብቅና advocacy ለመስራት።
የበለጠ ማድረግ ይፈልጋሉ? በQgiv ላይ የራስዎን Peer-to-Peer ገንዘብ ማሰባሰቢያ ገፅ ይፍጠሩ—ያካፍሉት፣ እና የበለጠ ቤተሰቦችን በፍጥነት ላድርሳቸው endichel እርዱን!
መሮጥ የመዝናኛ ቅርሳችን አካል ነው። ለEESNC ሲሮጡ፣ የመጨረሻ መስመር ላይ ብቻ አይደለም —ዋናው ግንዛቤን ወደዚህ ሕብረተሰብ ማምጣት ነው ።
10 months ago
በታክስ እና ጉምሩክ ዙርያ የሚወጡ ህጎችና አሰራሮች ፍትሀዊ፣ግልፅና የሚተነበዩ እንዲሆኑ ተጠየቀ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተቋቋመባቸው አላማዎች አንዱ የፖሊሲ አድቮኬሲ ስራዎችን በማካሄድ ለንግድና ኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ ባለፉት ጊዜያት በርካታ የምክክር መድረኮችን በማመቻቸት ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት እንዲመክሩና የተሻሉ የንግድ ህጎችና ፖሊሲዎች እንዲወጡና እንዲተገበሩ ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል፡፡
የዚህ አንድ አካል የሆነው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ በታክስና ጉምሩክ ሪፎርም ፣ ትግበራና ተግዳሮቶች ዙርያ ትኩረቱን በማድረግ ተካሂዷል፡፡
“የታክስ እና የጉምሩክ ሪፎርም አተገባበር በግሉ ዘርፍ ላይ ያለው ተጽእኖ” በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የመጀመሪያው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ አዲስ ቻምበር ከአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጲያ እና ከአለም አቀፉ የግል ኢንተርፕራይዞች ማእከል ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።
የምክክር መድረኩ የሚመለከታቸው የገንዘብ ና የገቢዎች ሚኒስቴር ሀላፊዎች ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አመራሮች ፣ የአዲስ ቻምበር እና የአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላትን በማገናኘት በግብር እና በጉምሩክ ስርአት፣ አስተዳደርና አተገባበር ዙርያ ሰፊ ሃሳቦች የተንሸራሸሩበት መድረክ ነበር፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አለምወርቅ ደረሰ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ የሪፎርምና የለውጥ ስራዎች መስራቱን ጠቅሰው መስሪያ ቤታቸው ለንግዱ ህብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት እጅግ ቀላል፣ ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።
የግሉ ዘርፍ የሚያነሳቸውን ተግዳሮቶችም በተደራጀ እና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተቀራርቦ ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ጠቁመዋል ።
የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሀፊ መሠረት ሞላ (ዶ/ር) በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የግብር እና የጉምሩክ ጉዳይ ከበርካታ አመታት ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ችግር መሆኑን ተናግረው እንዲህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት ምክር ቤታቸው ወሳኝ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ፤ የፖሊሲ ግብአቶች የሚሰበሰቡበትና አመቺ ፖሊሲዎች እንዲወጡና ተግባራዊ እንዲደረጉ ምክር ቤቱ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል መላኩ እንደተናገሩት አባል ኩባንዎቻቸውና መላው የንግዱ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ውስጥ የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በማስታወስ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ማክሮ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጤናማ፣ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ እና ሊተነበይ የሚችል የግብር እና የጉምሩክ ስርአት መኖር ወሣኝ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ለውይይት የሚሆኑ ጹሁፎች ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን እና አግሉ ዘርፍ በሚመለከታቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የቀረቡ ሲሆን ሰፋ ያሉ ሀሳቦችና ግብአቶች ቀርበውበታል፡፡
ከተነሱ ሀሳቦችና ምልከታዎች መካከል የኢትዮጵያ የታክስ ምጣኔ ከጥቅል አመታዊ ምርት ጋር ሲነጻጸር ከአመት አመት እየቀነሠ መምጣቱ፤ የታክስ እና ጉምሩክ ሪፎርሞች ከተቋማት ብቃትና ፤ከሰለጠነ የሰው ሀይል አንጻር ክፍተቶች እንዳሉበት፤ የታክስ እና ጉምሩክ አስተዳደርና አተገባበሮች ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱ አለመሆናቸው፤ የታክስ ፖሊሲ ለውጦችን በየጊዜው ከሚለዋወጠው ኢኮኖሚ ጋር በማነጻጸር ለውጥ ያለማድረግ ክፍተቶች መሆናቸውን በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ በምክክር መድረኩ ከተነሱት ሀሳቦች መካከል የቅንጅታዊ አሰራር መጓደል፤ የታክስ ከፋዮችን መብት ሊያስከብር የሚችል ነፃና ገለልተኛ ተቋም አለመኖር፤ የታክስ ግጭት አፈታት ረጅምና አሰልቺ መሆን በዋናነት ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡
በግብር ይግባኝ ችሎት በቂ የግሉ ዘርፍ ተወካይ እንዲኖርና በግብር ይግባኝ ክርክር ወቅት ቅድሚያ የሚከፈለው የ 50 በመቶ መጠን ወደ 20 በመቶ ዝቅ እንዲል እንደ ምክረ ሀሳብ ተጠይቋል ።
በአጠቃላይ “የታክስ እና የጉምሩክ ሪፎርም አሠራርና አተገባበር በግሉ ዘርፍ ላይ ያለው አንድምታ” በሚል የተካሄደው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ከንግዱ ማህበረሰብና ከሚመለከታቸው ሀላፊዎች በርካታ ምላሾችና ምክር ሀሳቦች የተዳሰሱበት ሲሆን በተለይ የኢትዮጵያ የታክስ እና ጉምሩክ አሠራር እና አተገባበር ቀልጣፋና ለንግድ አሰራር አስቻይ እንዲሆን አሁን ያለው ፖሊሲ፣ ሕግና መመሪያ ወደፊት ከሚታሰበው የግል ዘርፉ ሚና አኳያ መቃኘት እንዳለበት፤ ሪፎርሞቹን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችሉ ብቁ ተቋማት፤ ወጥ ስትራቴጂና ዝርዝር ህጎች በስራ ላይ ማዋል ፤ በታክስ አሰባሰብ ሂደት ውስጥ ቴክኖሎጂን መጠቀም፤ ፍትኃዊና ተጠያቂነት ያለበት የታክስና ጉምሩክ ስርአትን መፍጠርና ግንዛቤ እንዲያድግ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል ፡፡
በመጨረሻም በምክክር መድረኩ መፈታት አለባቸው የተባሉ ተግዳሮቶችን በማጠናቀር ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማቅረብ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ክትትል እንደሚደረግ አዲስ ቻምበር ገልጿል፡፡
አዲስ ቻምበር በቀጣይም ከአሜሪካን ንግድ ምክር ቤት በኢትዮጵያና ከአለም አቀፉ የግል ኢንተርፕራይዞች ማእከል ጋር በመተባበር በተለያዩ የፖሊሲ አድቮኬሲ ጉዳዬች ዙሪያ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች በተከታታይ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል ።
#advocacy
#addischamber

መሮጥ የመዝናኛ ቅርሳችን አካል ነው። ለEESNC ሲሮጡ፣ የመጨረሻ መስመር ላይ ብቻ አይደለም —ዋናው ግንዛቤን ወደዚህ ሕብረተሰብ ማምጣት ነው እና ምንም ቤተሰብ ብቻዋን እንደማትራመድ እያሳዩ ነው።
ስለሆነም በኩራት፣ በዓላማ፣ እና ህይወትን ለሚቀይር ጉዳይ እንሮጣለን ማለት ነው! የምትረዱት QR ኮዱን በመንካት ፣ መመዝገብ፣ ወይም መለገስ—እና አብረን ታሪክ እንፍጠር።
I am Azeb Ataro Adere, founder of the Ethiopian Eritrean Special Needs Community (EESNC) .We are proud to partner with Grand African Run.to support children, youth, and adults with autism and developmental disabilities. In our Ethiopian Eritrean community here in DMV, The exciting part is, if you want to register 25% of your fee goes directly to EESNC to fund caregivers training, youth, and adults programs and Advocacy for Families. Do you want to do even more, create your own peer to peer page on QGIV. and Share it and help us reach more families faster. Running is part of our heritage. When you run for EESNC, you are not just crossing a finish line. You are breaking stigma, raising awareness, and you are showing that no family walks alone. On October 11th, we will run with pride., with purpose and for a cause that changes lives. Use the QR code, sign up or donate and lets make history together.
Sponsored by
Surafel
11 months ago
ተሽሯል‼️
ከተቃውሞ በኋላ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።
በአገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ክርክር የፈጠረ የነበረው ድንጋጌ ከአዋጁ ማሻሻያ ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል ፡፡
ይህ ድንጋጌ አገር በቀል ድርጅቶች ለፖለቲካዊ ቅስቀሳ (political advocacy) እና ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ስራዎች ከውጭ የገንዘብ ምንጭ ገንዘብ እንዳይቀበሉ ይከለክል ነበር።
ቢቢሲ እንደዘገበው የማሻሻያ ረቂቁ አገር በቀል ድርጅቶች ከምርጫ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ስራ ለመስራት ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን "ቅድሚያ የድጋፍ ደብዳቤ ማግኘት" እንዳለባቸው ተቀምጧል።
በስራ ላይ ያለው አዋጅ ከስድስት ዓመት በፊት የጸደቀ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረውን እና "አፋኝ" በሚል የሚተቸውን አዋጅ ሙሉ ለሙሉ የሻረ ነበር። አዲሱ አዋጅ ለሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር።
Seledadotio

12 months ago
ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ የሴቶች አጀንዳዎች ትኩረት እንዲያገኙ የውትወታ ስራ እየሰሩ መሆኑን ገለፁ
ጥምረቱ የውትወታ ሥራውን ይበልጥ ለማጠናከር እና የሴቶች አጀንዳዎች ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ የባለብዙ ዘርፍ ተዋናዮች እና ከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍል የተውጣጡ ሴቶች ተወካዮች ጋር የሚገናኙበት ውይይት ዛሬ ቀን 27/10/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳሮ ማርያ ሆቴል አካሄዷል።
ይህ የውትወታ ወርክሾፕ በፖሊሲ አውጭዎች፣ በፖሊሲ ፈጻሚዎች፣ በሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ከክልሎች ከወረዳ እና ዞኖች በተውጣጡ የማኀበረሰብ ክፍል ሴቶች መካከል ውይይት እና ትብብርን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ ዓላማውም በዘርፉ ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ትግበራ እና የአድቮኬሲ ጥረቶችን ማጠናከር ነው ተብሏል።
ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ከሦስት ዓመታት በፊት ከሁሉም ክልሎች በተውጣጡ 22 በሚሆኑ በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የሴቶች ማኅበራት ጥምረት የተመሠረተ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ከ60 በላይ አባል ድርጅቶችን በመያዝ በህግራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ እና ውክልና ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል።
ጥምረቱ በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከ6 ሺህ 122 በላይ የሴት የማኅበረሰብ ተወካዮችን በመድረስ 3 ሺህ 500 በላይ አጀንዳዎችን የሰበሰበ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በጋራ ስምምነት የተደረሰባቸውን 10 አንገብጋቢ የሴቶች አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስረክቧል።
እነዚህ አጀንዳዎች የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮች እና ፍላጎቶች የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ፣ በህገራዊ የፖሊሲ አውታሮች ውስጥ የሴቶችን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጁ ናቸው። አጀንዳዎቹ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥምረቱ የተለያዩ የውትወታ (Advocacy) ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ዋና ዋና 10 የሴቶች አጀንዳዎች 1. በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጸታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መባባስ፣ 2. የሰላም እጦት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር፣ 3. ለሴት አካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ትኩረት ማነስ፣ 4. የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ሚና ማነስ፣ 5. የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የመሬት ባለቤትነት መብት ውስንነት፣ 6. ስር የሰደዱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ 7. የኑሮ ውድነት እና የሥራ አጥነት ችግር በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ጫና፣ 8. የትምህርት ተደራሽነት ለሴቶች ውስን መሆን፣ 9. የመሠረተ ልማቶች እጥረት እና ተደራሽነት ውስንነት፣ 10. ሕገ መንግሥቱ የሀገርን አንድነት እና ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ ማሻሻል የሚሉት እንዲሻሻሉ ሴቶች ጠይቀዋል።
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ፣ እነዚህ የሴቶች አጀንዳዎች እውን እንዲሆኑ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም መንግሥት፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ሚዲያ እና የግሉ ዘርፍ የየበኩላቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ በመጠየቅ የሴቶችን ድምፅ ማድመጥ እና አጀንዳዎቻቸውን ተግባራዊ ማድረግ ለሀገራዊ ሰላም፣ እድገት እና ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።

Comments