ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ የሴቶች አጀንዳዎች ትኩረት እንዲያገኙ የውትወታ ስራ እየሰሩ መሆኑን ገለፁ
ጥምረቱ የውትወታ ሥራውን ይበልጥ ለማጠናከር እና የሴቶች አጀንዳዎች ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ የባለብዙ ዘርፍ ተዋናዮች እና ከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍል የተውጣጡ ሴቶች ተወካዮች ጋር የሚገናኙበት ውይይት ዛሬ ቀን 27/10/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳሮ ማርያ ሆቴል አካሄዷል።
ይህ የውትወታ ወርክሾፕ በፖሊሲ አውጭዎች፣ በፖሊሲ ፈጻሚዎች፣ በሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ከክልሎች ከወረዳ እና ዞኖች በተውጣጡ የማኀበረሰብ ክፍል ሴቶች መካከል ውይይት እና ትብብርን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ ዓላማውም በዘርፉ ሁሉን አቀፍ የፖሊሲ ትግበራ እና የአድቮኬሲ ጥረቶችን ማጠናከር ነው ተብሏል።
ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ከሦስት ዓመታት በፊት ከሁሉም ክልሎች በተውጣጡ 22 በሚሆኑ በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የሴቶች ማኅበራት ጥምረት የተመሠረተ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ከ60 በላይ አባል ድርጅቶችን በመያዝ በህግራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ እና ውክልና ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል።
ጥምረቱ በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከ6 ሺህ 122 በላይ የሴት የማኅበረሰብ ተወካዮችን በመድረስ 3 ሺህ 500 በላይ አጀንዳዎችን የሰበሰበ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በጋራ ስምምነት የተደረሰባቸውን 10 አንገብጋቢ የሴቶች አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እስረክቧል።
እነዚህ አጀንዳዎች የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮች እና ፍላጎቶች የሚያንፀባርቁ ሲሆኑ፣ በህገራዊ የፖሊሲ አውታሮች ውስጥ የሴቶችን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጁ ናቸው። አጀንዳዎቹ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥምረቱ የተለያዩ የውትወታ (Advocacy) ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ዋና ዋና 10 የሴቶች አጀንዳዎች 1. በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጸታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መባባስ፣ 2. የሰላም እጦት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር፣ 3. ለሴት አካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ትኩረት ማነስ፣ 4. የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ሚና ማነስ፣ 5. የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና የመሬት ባለቤትነት መብት ውስንነት፣ 6. ስር የሰደዱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ 7. የኑሮ ውድነት እና የሥራ አጥነት ችግር በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ጫና፣ 8. የትምህርት ተደራሽነት ለሴቶች ውስን መሆን፣ 9. የመሠረተ ልማቶች እጥረት እና ተደራሽነት ውስንነት፣ 10. ሕገ መንግሥቱ የሀገርን አንድነት እና ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ ማሻሻል የሚሉት እንዲሻሻሉ ሴቶች ጠይቀዋል።
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ፣ እነዚህ የሴቶች አጀንዳዎች እውን እንዲሆኑ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም መንግሥት፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ሚዲያ እና የግሉ ዘርፍ የየበኩላቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ በመጠየቅ የሴቶችን ድምፅ ማድመጥ እና አጀንዳዎቻቸውን ተግባራዊ ማድረግ ለሀገራዊ ሰላም፣ እድገት እና ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።

12 months ago
SeledaPost
12 months ago
Replying to FastMereja 's post
a11111111111qaz