20 hours ago
#tecno_spark_50
አዲሱ የቴክኖ ስፓርክ 50 ቀኑን ሙሉ ሲሰሩበት ቢውሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ቢጠቀሙበት፣ ስልክ ቢያወሩበት እንዲሁ ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ቢሰሩበት ከጠዋት እስከ ማታ ንቅንቅ አይልም ለምን? እጅግ ከፍተኛ የሆነ 6700 ሚሊ አምፒር ባትሪውን ይዞ ስለመጣ ነው፡፡ አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 50 ለስራዎት ያስፈልጎታል!!
#spark50 #spark50series #tecnoai #tecnoet
tecno_et

22 hours ago
ፍልሰታ በበአታ
“ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት፤
ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ “ማቴ 26፡40
የበአታ ገዳም መልዕክት
ይህን ታላቅ ጾም በታላቋ ገዳም በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካነገሥት በአታ ለማርያም በደብረመንክራት
ሥዕልቤት ኪዳነምህረት ገዳም ፡፡
ይህ ጾመ ማርያም (ጾመ ፍልሰታ) ከ7ቱ ታላላቅ አጽዋማት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል ይህን ጾም ከሌላው
ለየት የሚያደርገው አባቶቻችን ሐዋርያት ለትምህርተ ወንጌል ከተሰማሩበት ተሰባስበው የእመቤታችንን
ትንሳኤዋንና ዕርገቷን ለማየት ሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን ፈጣሪያቸውን በጸሎትና በምህላ ጠይቀው
ትንሳኤዋን እና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል፡፡እኛም የእነሱን መንገድ ተከትለን በቤተ እግዚአብሔር በጸሎት
በቅዳሴ በሰዓታት በምህላ ለሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን በየዓመቱ ሱባኤ ይዘን እንጸልያለን፡፡ ይህ ጾመ ሱባኤ
በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም በስዕል ቤት ኪዳነምህረት ገዳም በልዩ ሁኔታ ይከናወናል፡፡ ሆኖም አሁን
ባለው ሁኔታ በገዳማችን አካባቢ የሚገኙ ምእመናን በመልሶ ማልማት ምክንያት ከስፍራው ርቀው ይገኛሉ ፡፡
ስለሆነም ይህ የጥሪ መልእክት የደረሳችሁ ምእመናን እና ምእመናት በሙሉ በገዳማችን መጥታችሁ ይህን
ታላቅ የሱባኤ ጾም እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡
በሱባኤ ጊዜ በገዳማችን የሚከናወኑ መንፈሳዊ የሱባኤ አገልግሎቶች
1ኛ. ከምሽቱ 4ሰዓት እስከ ጠዋት 12፡30 የሰዓታት ቁመት ኪዳንን ጨምሮ ይከናወናል፡፡
2ኛ የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጉም ከ3፡30 እስከ 6፡00ሰዓት የካሄዳል፡፡
3ኛ ከ6፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት የቅዳሴ አገልግሎት በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል፡፡
4ኛ በገዳማችን ብቻ በተለየ መልኩ የሚጸለይ የሠርክ ጸሎት (የምህላ) አገልግሎት መሐረነአብ ተብሎ
እግዚኦ መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ በእንተማርያም መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ እየተባለ ከ9፡30 እስከ 11፡00
ሰዓት ይደረሳል ፡፡
5ኛ ከ11፡00 እስከ 12፡30 የትምህርተ ወንጌል መርሀ ግብር ይፈፀማል፡፡
ይህንን ጾመሱባኤ በእመቤታችን በበአታማርያም ደጅ መጥታችሁ በታላላቅአበው መነኮሳት እጅ
እየተባረካችሁ በመጨረሻም ነሐሴ16 ቀን በዚሁ ገዳም የኪዳነምህረት በአለንግሧን አንግሣችሁ በረከት
እንድታገኙ ጥሪያችንን በእግዚአብሔርስም እያስተላለፍን በበአታ ገዳማችን ተገኝታችሁ እንድትጸልዩ
ተጋብዛችኋል ፡፡
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን።

1 day ago
በእንግሊዝ ቻናል ውስጥ እሳት ከተነሳበት ጀልባ ከ150 በላይ ሰዎች ተረፉ
#ethiopia | ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ሲሞክር የነበረ ትንሽ ጀልባ በእንግሊዝ ቻናል ውስጥ በሞተሩ ላይ እሳት ከተነሳ በኋላ 157 ስደተኞች በሕይወት ታድነዋል።
አደጋው ማክሰኞ ጠዋት በፈረንሳይ የፍለጋና የማዳን ቀጠና ውስጥ ተከስቷል።
በማዳን ዘመቻው የፈረንሳይ የባህር ጠባቂዎች፣ የብሪታንያ የድንበር ጥበቃ ጀልባዎች፣ የባህር ሕይወት አድን ቡድኖች (RNLI) እና ሄሊኮፕተሮች ተሳትፈዋል።
ከተረፉት መካከል 103 ሰዎች በፈረንሳይ መርከቦች ሲድኑ፣ 54 ደግሞ በብሪታንያ ኃይሎች ተወስደዋል።
ባለሥልጣናት እስካሁን የሞት ወይም ከባድ ጉዳት መኖሩን አላረጋገጡም። ሁሉም የተረፉት ወደ ሰሜን ፈረንሳይ የሚገኘው ቡሎኝ-ሱር-መር ወደብ ተወስደው የሕክምና ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
ይህ ክስተት በእንግሊዝ ቻናል ላይ በትንንሽ ጀልባዎች የሚደረጉ አደገኛ ስደተኞች ጉዞዎች አሁንም ከፍተኛ አደጋ እንዳላቸው በድጋሚ አሳይቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

2 days ago
የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ መጽሐፍ
“ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ይመረቃል
#ethiopia | የጋዜጠኛ፣ ደራሲና መምህር ዐቢይ ይልማ አምስተኛ መጽሐፍ የሆነው “ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል።
መጽሐፉ በዘመናችን በብዙ ሰዎች የሚስተዋሉ እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የባዶነት ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ሱሰኝነት፣ የገንዘብ ችግርና ሌሎች የሕይወት ፈተናዎች ዙሪያ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ እይታዎችን በማቀናጀት ለአንባቢያን ተስፋና መነሳሳት ለመስጠት ያለመ ሥራ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
ደራሲው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ያጋጠሙትን ለ12 ዓመታት የዘለቀ ከባድ የጤናና የሕይወት ፈተና በድል ካለፉ በኋላ ያገኙትን ልምድና እውቀት በዚህ መጽሐፍ አካፍለዋል።
አዘጋጅ ኮሚቴው በዕለቱ የሚካሄደውን የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት እንዲታደሙ የደራሲውን ወዳጆች፣ የሥነ ጽሑፍ አፍቃሪዎችና መላውን ሕዝብ በክብር ጋብዟል።
ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም.
ጠዋት 4፡00 ሰዓት
ቦሌ ዓለም ሲኒማ
እንኳን ወደ መጽሐፉ ምረቃ በደህና መጡ!

Sponsored by
Surafel
4 days ago
#tecno_spark_50
አዲሱ የቴክኖ ስፓርክ 50 ቀኑን ሙሉ ሲሰሩበት ቢውሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ቢጠቀሙበት፣ ስልክ ቢያወሩበት እንዲሁ ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ቢሰሩበት ከጠዋት እስከ ማታ ንቅንቅ አይልም ለምን? እጅግ ከፍተኛ የሆነ 6700 ሚሊ አምፒር ባትሩን ይዞ ስለመጣ ነው፡፡ አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 50 ለስራዎት ያስፈልጎታል፡፡
#spark50 #spark50series #tecnoai #tecnoet
tecno_et
አዲሱ የቴክኖ ስፓርክ 50 ቀኑን ሙሉ ሲሰሩበት ቢውሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ቢጠቀሙበት፣ ስልክ ቢያወሩበት እንዲሁ ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ቢሰሩበት ከጠዋት እስከ ማታ ንቅንቅ አይልም ለምን? እጅግ ከፍተኛ የሆነ 6700 ሚሊ አምፒር ባትሩን ይዞ ስለመጣ ነው፡፡ አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 50 ለስራዎት ያስፈልጎታል፡፡
#spark50 #spark50series #tecnoai #tecnoet
tecno_et
5 days ago
የጥቃቱ መነሻ‼️
👉 የጥቃቱ መነሻና ቦታ፡ አካባቢውን በኃይል ለመቆጣጠር በማሰብ፣ በሱዳን በኩል የተደራጁ የ'ሳምሪ' ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከፍተዋል። ታጣቂዎቹ ጦርነቱን የጀመሩት በሱዳን ድንበር በኩል በ'ሸረሪና' እና በወልቃይት ጠገዴ ዞን፣ ቃብትያ ሁመራ ወረዳ ስር በምትተዳደረው የበረከት ከተማ አቅጣጫ ድንበር ጥሰው በመግባት ነው።
👉 የሜዳ ላይ ውጊያ ሁኔታ፡ በበረከት ከተማ እና በሸረሪና አቅጣጫ ጥቃቱን የጀመሩት ከሱዳን ሰርጎ የገቡት ታጣቂዎች ('አርሚ 70' ላይ) በቀላል መሳሪያዎች ትንኮሳ የከፈቱ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መጠነ ሰፊ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።
👉 በድሮንና በመድፍ የታገዘ አፀፋ፡ አሁን ላይ ከሁመራ ወደ በረከት ከተማ እና ሸረሪና አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ድብደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በሰማይ ላይም የድሮን እንቅስቃሴ በግልፅ እየታየ ነው። የከባድ መሳሪያው (መድፍ) ተኩስ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ርቀት ላይ በምትገኘው ሁመራ ከተማ ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እያነዘረ እንደሚገኝ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
👉 የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ፡ በበረከት እና ሸረሪና አቅጣጫ የተጀመረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረት ያንዣበበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከፈተበትን ይህንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ለመመከት እና ለመደምሰስ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል።
👉በድምፅ አልባ መሳሪያ (መሬት ላይ ሲደርስ ብቻ የሚፈነዳ መሳሪያ) በርካታ የአርሚ 70 ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል።
👉ታጣቂዎቹ ዛሬ ሁመራን ለመያዝ እቅድ እንደሰጣቸው ገልፀዋል።
👉ህወሓት በበኩሉ የፌደራል መንግስቱ ከበባ ሲፈፅም ከርሞ ዛሬ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በምዕራብ ትግራይ ተኩስ ከፍቶብናል ሲል መግለጫ አውጥቷል።
Seledadotio

6 days ago
#ከመልዕክቶቻችሁ "ሰላም ዘ-ሐበሻ፣ ይሄ የአከራይ ተከራይ የሚሉት ነገር እያጉላላን ነው። መንግስት የአከራይ ተከራይ ውል በየሁለት ዓመቱ አድሱ በማለቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 14 አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እንገኛለን። ሆኖም ትንሽዬ ጉዳይ ለማስፈጸም ጠዋት የተቀመጥን ከምሳ በኋላም እየጠበቅን ነው። ሁለት ሰራተኛ ያውም የሚያለግሙ አስቀምጠው ይህንን ሁሉ ሰው ማስተናገድ ተስኗቸዋል። ወረዳ 13ም ሕዝቡ በተመሳሳይ እያማረረ ነው። ይህ ቀርፋፋ አሰራር እንዲስተካከል ለሚመለከተው ድምጻችንን አሰሙልን"
ስሜኝ ደብቁልኝ ከገርጂ
ስሜኝ ደብቁልኝ ከገርጂ
6 days ago
"ደህና ነኝ!" ሊመረቅ ነው!
የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ “ደህና ነኝ - እግዚአብሔር ይመስገን” የተሰኘ መንፈ-ሳይንሳዊ መፅሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2/2018 ዓም ፣ ቅዳሜ ጠዋት 4፡00 ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ አሁን በትውልዱም ፣ በሐገራችንም የገባውን የጭንቀት ፣ የፍርሃት ፣ የባዶነት ስሜት ፣ የተስፋ መቁረጥ ፣ የካንሰር ፣ የስኳር ፣ ስትሮክና መሰል በሽታዎች ጥቃትን በዕውቀት ያክማል፡፡ በራስ ኩነኔ ፣ በሱሰኝነት ፣ በገንዘብ እጦት ወዘተ (ብቻ) ሕይወትም ኑሮም ለከበዳት ነፍስ አስገራሚ ምስጢራትን ይበታትናል፡፡ ፀሐፊው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ፣ በመኖርና መሞት መካከል ከተፋለመባቸው የ12 ዓመታት የሕይወት ጦርነት አሸናፊነት ውስጥ “ደህና ነኝ ፤ እግዚአብሔር ይመስገን!” መጽሐፍ ተወልዳለች።
በምረቃው ዕለት ታላላቅ እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን መርሀ ግብሩንም የሚያዋዙ የጥበብ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የኒውካስሉ ተወዳጅ የቀድሞ አሰልጣኝ ኬቨን ኪጋን ካረፉ ገና አስር ቀናት ብቻ ቢቆጠሩም፣ ክለቡ ሌላ ያልተጠበቀ መርዶ አስተናግዷል፦ የኪጋንን ህልም እውን በማድረግ ክለቡን ለክብር ያበቁት አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል።
ከእጅግ አስከፊው የ2025-26 የውድድር ዘመን በኋላ በኃላፊነታቸው ለመቀጠል እና ክለቡን መልሰው ለመገንባት ቃል ገብተው የነበሩት ኤዲ ሃው፣ አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሊጀመር ሶስት ሳምንታት ብቻ ሲቀሩት ውሳኔያቸውን ቀልብሰዋል።
ማክሰኞ ምሽት በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ኒውካስል ከብሪስቶል ሲቲ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 4-1 በሆነ አሳፋሪ ውጤት መሸነፉ ብዙ ነገሮችን የቀየረ ይመስላል። ከሜዳቸው ውጪ ስታዲየሙን ሞልተው የነበሩት የኒውካስል ደጋፊዎች ያሰሙት የተቃውሞ እና የቁጣ ድምፅ፣ ይህ "ትርጉም አልባ" የሚመስል የወዳጅነት ጨዋታ ትልቅ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ አመላካች ነበር።
በማግስቱ ረቡዕ ጠዋት እንደተሰማው ኤዲ ሃው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ወስነዋል። የቅርብ ምንጮች እንደሚያሳዩት ይህ ውሳኔ የቅጽበት የብስጭት ውሳኔ ሳይሆን፣ ከከባዱ የውድድር ዘመን መገባደጃ አንስቶ አሰልጣኙ በውስጣቸው ሲያብሰለስሉት የቆዩት እና ሊሸከሙት ያልቻሉት ከባድ ሸክም ውጤት ነው።
ለኤዲ ሃው፣ ይህ ስንብት እጅግ አስደናቂ ለነበረው የኒውካስል ቆይታቸው የማይመጥን አሳዛኝ ማብቂያ ነው። ከ30 ዓመታት በፊት ኬቨን ኪጋን እጅግ ተቃርበውት የነበረውን፣ ደጋፊውም ለ70 ዓመታት ሲናፍቀው የነበረውን ትልቅ ዋንጫ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ ያመጡት እርሳቸው ነበሩ።
እ.ኤ.አ በ2021 ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ መውረድ አፋፍ በደረሰበት ወቅት ኃላፊነቱን የተረከቡት ሃው፣ ኒውካስልን በሊጉ ማቆየት ብቻ ሳይሆን በሚቀጥለው ዓመት ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ መድረክ መልሰውታል። በ2024-25 ደግሞ በካራባኦ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የሊጉን ሻምፒዮን ሊቨርፑልን በዌምብሌይ አሸንፈው ታሪካዊ ዋንጫ በማንሳት ስማቸውን በኒውካስል ታሪክ በወርቅ ቀለም አጽፈው ነበር።
ይህ የዋንጫ ድል የሳዑዲው የኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው እና የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለሚያልመው ኒውካስል እንደ ትልቅ መነሻ መታየት ነበረበት። ሆኖም፣ የ2025ቱ ክረምት የሁሉንም ነገር አቅጣጫ ቀየረው።
በተለይም አሌክሳንደር ኢሳክን በክለቡ ለማቆየት የተደረገው ተስፋ አስቆራጭ እና መራር ትግል፣ በመጨረሻም ስዊድናዊው አጥቂ በብሪታንያ የዝውውር ሪከርድ በዝውውር መስኮቱ መዘጋጃ ዕለት ወደ ሊቨርፑል ማምራቱ ክለቡን ክፉኛ ጎድቶታል። ኒውካስል የኢሳክን ክፍተት ሊተካ የሚችል ተጫዋች ማምጣት አልቻለም። እንደ ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ቤንጃሚን ሴስኮ እና ጆአዎ ፔድሮ ያሉ ታላላቅ ኢላማዎቹን ለተቀናቃኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሳልፎ ሰጠ።
በምትኩ ክለቡ እና ኤዲ ሃው በጋራ ያመጧቸው ኒክ ዎልቴማዴ፣ ዮአን ዊሳ እና አንቶኒ ኤላንጋ አጠቃላይ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ($243m) ቢወጣባቸውም፣ ያሳዩት አቋም እና የገጠማቸው የጉዳት ችግር የተከፈለባቸውን ዋጋ ፈጽሞ ሊያጸድቅ አልቻለም። የኤላንጋ እና ዎልቴማዴ ብቃት ሲዋዥቅ፣ አጥቂው ዊሳ በሙሉ የውድድር ዘመኑ በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ብቻ ነበር። በ43 ሚሊዮን ፓውንድ የመጣው ጃኮብ ራምሴይም በቁርጭምጭሚት ጉዳት ሲሰቃይ ጊዜውን አሳልፏል።
የዝውውር ውድቀቱ በሜዳ ላይ ውጤት ቢሸፈን ኖሮ የኤዲ ሃው ጫና ያን ያህል አይከፋም ነበር። ሆኖም የ2025-26 የውድድር ዘመን ለኒውካስል እውነተኛ ቅዠት ሆኖ አለፈ።
በዓመቱ መጀመሪያ ጥሩ አጀማመር ያሳየው ክለቡ፣ ከአዲሱ ዓመት በኋላ ግን የመውረድ ስጋት ወዳለባቸው ቡድኖች ወረደ። ከጥር መጨረሻ አንስቶ እስከ የውድድር ዘመኑ ማብቂያ ድረስ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በ10ሩ በመሸነፉ፣ ከ6ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ደረጃ በማሽቆልቆል ደጋፊውን በሀዘን እና በቁጣ ሞላው።
ይባስ ብሎ በኤፍኤ ካፕ እና በካራባኦ ካፕ በማንችስተር ሲቲ በቀላሉ ሲሰናበት፣ በቻምፒዮንስ ሊጉ ደግሞ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8-3 በሆነ አሳፋሪ የጎል ናዳ አዋርዶ ከውድድሩ አስወጣው።
የኤዲ ሃው የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ የገባው ገና በጊዜ ነበር። በሚያዝያ ወር ኒውካስል በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ በቦርንማውዝ ከተሸነፈ በኋላ፣ የክለቡ ታሪካዊ ሌጀንድ አላን ሺረር እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለኤዲ ምን ያህል ከባድ ጊዜ እንደሆነ ባውቅም፣ የወደፊት እጣ ፈንታው ምን እንደሚሆን አላውቅም። ዳግም የመዋጋት እና ክለቡን የማንሳት አቅሙ ያለው አይመስለኝም። በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ኤዲ ሃው ኒውካስልን ያሰለጥናል ብዬ አላስብም።"
ሺረር እንዳለውም ሆነ ኤዲ ሃው ኒውካስልን ወደ ቀደመ ክብሩ የመመለስ ትልቅ ታሪክ ሰርተው፣ ነገር ግን በኋለኛው አመታቸው በዝውውር ውድቀት እና በሜዳ ላይ አስከፊ ውጤቶች ታጅበው የሴንት ጀምስ ፓርኩን በር ዘግተው ወጥተዋል።

8 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የ9 ዓመቷን ሜሊና ፍራቶሊንን ገድሎ አስከሬኗን ደብቋል ተብሎ የተከሰሰው ኢትዮ-ጣሊያናዊ ካናዳዊው የሉቺያኖ ፍራቶሊን የፍርድ ሂደት ማክሰኞ ዕለት ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ የሟች እናት የሆነችውን ካሊ ጋላኒስን ጨምሮ በርካታ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል። ችሎቱ የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት በሀዘን ድባብ ታጅቦ ውሏል።
ካሊ ጋላኒስ ስለ ልጇ ሞት በአደባባይ ስትናገር ማክሰኞ የፍርድ ቤት ውሎ የመጀመሪያዋ ነበር። ፍርድ ቤት ቀርባ ቃል ስትሰጥ፣ ከተከሳሹ ሉቺያኖ ጋር ስለነበራት የ10 ዓመታት ግንኙነት ተናግራለች። ጋላኒስ እና ሉቺያኖ እ.ኤ.አ. በ2009 በኢትዮጵያ ውስጥ እንደተገናኙ እና የርቀት ፍቅር እንደነበራቸው ገልጻለች። ሜሊና በ2016 የተወለደች ሲሆን፣ ጋላኒስ የልጇ ብቸኛ አሳዳጊ እንደነበረች መስክራለች።
ሉቺያኖ በሀምሌ 2025 ሜሊናን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ይዟት ለመሄድ ፍላጎት እንዳለው አሳውቆ እንደነበር ጋላኒስ መስክራለች። ነገር ግን፣ "ተከሳሹ ለሜሊና የነገራትን አንዳንድ አሳሳቢ ነገሮች በመስማቴ ምቾት አልተሰማኝም" ስትል ለፍርድ ቤቱ አስረድታለች። በዚህም ምክንያት የጉዞ መዳረሻቸውን ወደ ኒውዮርክ ለመቀየር መስማማታቸውን ተናግራለች። ሉቺያኖ እና ሜሊና ሀምሌ 11 ቀን 2025 ወደ ኒውዮርክ ያቀኑ ሲሆን፣ ሀምሌ 19 ከምሽቱ 12 ሰዓት ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። በዚያች ምሽት ሲዘገዩ በተደጋጋሚ ስልክ እንደደወለች እና አጭር የጽሁፍ መልእክት እንደላከች፣ እንዲሁም ልጇን ማናገር እንደምትፈልግ ስትጠይቀው "ተኝታለች" የሚል ምላሽ እንደሰጣት እናትየው በምስክርነቷ ገልጻለች።
ጋላኒስ ስለ ሁኔታው ያወቀችው በማግስቱ ሀምሌ 20 ቀን 2025፣ ሌሊት 7፡30 አካባቢ የሞንትሪያል ፖሊሶች ቤቷ መጥተው "ስለ ልጅሽ ሁኔታ የሰማሽው ነገር አለ?" ብለው እስኪጠይቋት ድረስ ምንም እንደማታውቅ ተናግራለች። ለ12 ሰዓታት ያህል ከፖሊሶች ጋር በቆይታ ጥያቄዎችን ስትመልስ ካሳለፈች በኋላ፣ በማግስቱ ቀትር ላይ የልጇ አስከሬን መገኘቱን ሲነግሯት እጅግ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባቷን አስረድታለች።
በእለቱ ከሟች እናት በተጨማሪ አራት ሌሎች ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል። መርማሪ ዲጄ ሞሸር፣ የኤሴክስ ካውንቲ አስከሬን መርማሪ ኬሊ ቫለንታይን፣ የአስከሬን ምርመራ ያደረጉት የፎረንሲክ ፓቶሎጂስት ዶ/ር ማይክል ሲኪሪካ፣ እንዲሁም ፍለጋውን የመሩት የደን ጠባቂ ሎጋን ኩዊን ይገኙበታል። ኩዊን በሰጡት ምስክርነት፣ 14 የደን ጠባቂዎች እና ከ50 በላይ የህግ አስከባሪዎች በተሳተፉበት ፍለጋ፣ አስከሬኗን ሾርት ስዊንግ ትሬይል በተባለ ስፍራ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ማክሰኞ በዋለው ችሎት በርካታ ማስረጃዎች ቀርበዋል። የመጀመሪያው ሉቺያኖ ከመርማሪ ሞሸር ጋር በነበረው የ10 ሰዓታት ቆይታ የተወሰደ የቪዲዮ ማስረጃ ነው። በቪዲዮው ላይ ሉቺያኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲናገር እና ሲያለቅስ፣ እንዲሁም "የት እንዳለች አላውቅም" ሲል ታይቷል። ሁለተኛው ማስረጃ ደግሞ ሜሊና ከመጥፋቷ በፊት ሀምሌ 19 ቀን በመኪና ጀርባ ተቀምጣ ለእናቷ የላከቻት ፎቶግራፍ ሲሆን፣ ይህ ፎቶ በኋላ ላይ ልጇን ለመፈለግ በወጣው የማንቂያ መልእክት ላይ ጥቅም ላይ ውሏል። በተጨማሪም የሟች አስከሬን ፎቶዎች፣ የሞት የምስክር ወረቀት እና የአስከሬን ምርመራ ውጤቶች ለዳኞች ቀርበዋል።
የአስከሬን ምርመራውን ያደረጉት ዶ/ር ሲኪሪካ፣ ሜሊና የሞተችው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መተንፈስ በማቃቷ መሆኑን አረጋግጠው፣ አሟሟቷም ግድያ መሆኑን የሚያሳዩ "አሳማኝ ማስረጃዎች" መገኘታቸውን ገልጸዋል። የሞተችበት ትክክለኛ ሰዓት በሪፖርቱ ላይ ባይሰፍርም፣ የመጨረሻ ምግብ ከተመገበች ከ4 እስከ 6 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደተገደለች ዶክተሩ ገምተዋል። መርማሪዎች እንዳረጋገጡት ሜሊና የመጨረሻ ምግቧን የበላችው ሀምሌ 19 ቀን ከቀኑ 11፡30 ላይ በሳራቶጋ ስፕሪንግስ በሚገኝ ማክዶናልድስ ውስጥ ነበር።
ሉቺያኖ በሁለተኛ ደረጃ ግድያ እና የሰው አስከሬን በመደበቅ ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብሎ የካደ ሲሆን፣ የፍርድ ሂደቱ እስከ ሶስት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ዳኛ ታቲያና ኮፊንገር ጠቁመዋል። ችሎቱም ዛሬ ረቡዕ ጠዋት ይቀጥላል።

በሆነ በዘመን የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም!
የአህመድ ተሸመ (ዲንቢ) “ጊዜ አይሄድም”!
ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሰር)
#ethiopia | መቸም የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ድንቅ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ለራሱ የሠራቸውን ዘግየት እናድርግና ለሌሎች የሙያ አጋሮቹ ሠርቶላቸው በብዙኋን አድማጮች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኙትን የዜማ ድርሰቶቹን እንዘርዝር ብንል ጊዜም ሥፍራም አይበቃንም፡፡
እንደው ከግምታችን በላይ ስለሆነው ስለዲንቢ የላቀ የዜማ ደራሲነት ሰብዕና መሠረታዊ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ቢችል ግን ጥቂቱን ብቻ ከዚህ እንደሚከተለው እዘረዝርላችኋለሁ፡—
ለአሊ ቢራና ሄለን በርሄ - “ሲያዴ”፤ ለፀሀዬ ዮሐንስ - “ማን ልበልሽ”፤ ለማዲንጎ አፈወርቅ - “ላላተርፍ”፤ ለብዙአየሁ ደምሴ - “የህልሜ ንግስት”፤ ለዘቢባ ግርማ - “ገራገር”፤ ለኢሳያስ ታምራት - “እያዳነ ያማል”፤ ለታረቀኝ ሙሉ - “ስሚያቸው”፤ ለሚኪያስ ቸርነት - “ግርማ ሞገሴ”፤ ለሃይማኖት ግርማ - “ከዚራ ቁ-2”፤ ለግርማ ተፈራ - “ልዩ”፤ ለሀመልማል አባተ - “ሀሴት”፤ እና የመሳሰሉቱን የአህመድ ዲንቢን የዜማ ፈጠራዎች ከብዙ በጥቂቱ ማስታወስ ይቻላል፡፡
አንዳንድ ሙዚቃዎች ለጆሮ ብቻ አይሰሩም፤ ለስሜት ይደርሳሉ፤ ዛሬ ተሰርተው ግን ትዝታችንን ይመልሱልናል፡፡
አንዳንድ ዜማዎች፣ በውስጣችን የተከረቸሙ የጊዜ በሮችን ያንኳኳሉ፤ ይከፍታሉምም፡፡ በሮቹ ሲከፈቱ ደግሞ የተዘነጉ ፊቶች፣ የተለየናቸው ጓደኞች፣ የተራመድንባቸውን ጎዳናዎች… ብቻ ምኑ ቅጡ ትላንታችንን እንደ መጽሀፍ ይገልጡልናል፡፡ በሆነ ዘመን የቀረውን ማንነታችንን እንደገና ይመልሱልናል።
አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ከ14 ዓመታት በኋላ በአዲስ አልበሙ ሲመለስ፣ እኔ የሰማሁት የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብን አይደለም። አንድ በሆነ ዘመን የነበረ የዜማ ሰዋሰውና በዚሁ ዜማ ምክንያት የተሰፋ፣ የምናፍቀውን ዘመን የመለሰልኝ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡
ያ የኔ ዘመን የምለው “ዘጠናዎቹ”ን ነው፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. ነው። አይ፣ ተማሪነት! እንዴት ያለ ጣፋጭ፣ እንዴት ያለ የማይደገም ዘመን ነበር! ያ ዘመን ለእኔ የወጣትነት ወርቃማ ጠዋት ነበር። ዓለምን እንደ አዲስ ማየት የጀመርኩበት፤ ከተማዋን፣ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ሐሳብንና ነፃነትን ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ልብ ያጣጣምኩበት ዘመን ነበር።
ያ ዘመን ከጓደኞቸ ጋር እንደፈለግን የኖርንበት ዘመን ነበር። በአደባባይ የተከራከርንበት፣ አለምን የጠየቅንበት፣ መንግሥትን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃወምንበት፣ ነፃነትን ያየንበት፣ ዜማን ያጣጣምንበት ወቅት ነበር። ያ ዘመን “ዘጠናዎቹ” ነበር፡፡
ያንን ዘመን ሁሌም እናፍቀዋለሁ፤ ምናልባትም የምናፍቀው ዘመኑን ራሱን አይደለም፤ በዚያ ዘመን ውስጥ የነበርነውን እሱን፣ እሷን፣እኔን፣እኛን ነው። እንደገና እንዲመጣም እመኛለሁ።
ማርሴል ፕሩስት የተባለ ፈረንሳያዊ የልብ ወለድ ጸሀፊና ሀያሲ ጥልቅ የሆነን ትዝታ አስበን ለማስታወስ በምናደርገው ጥረት አይመለስም፤ ነገር ግን የስሜት ሕዋሳችን በሚነካ አንድ ድንገተኛ ልምድ ሊቀሰቀስ ይችላል ይላል፡፡ ሙዚቃም ከእነዚህ የትዝታ ቀስቃሾች መካከል እጅግ ኃይለኛው ሳይሆን አይቀርም።
በዚህ ረገድ እንደ አህመድ ተሾመ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ ዜማ የተረሳ ግን ተደበቀ ስሜትን ይቀሰቅሳል፤ የጠፋ የሚመስለውን የዜማ ስልተ ምት ይመልሳል፤ በዘመን ጥላ ሥር ተደብቆ የኖረ ማንነት እንደገና ያነቃቃል።
በ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የራሱ የሆነ የዜማ ሰዋሰው፣ ቀለምና የአወራረድ ለዛ ነበረው። ያ ዘመን ለእኔ ሙዚቃን ከመስማት ወደ ማዳመጥ የተሸጋገርኩበት ጊዜ ነው። ስለዚህ የዚያ ዘመን ዜማዎች በጆሮዬ ብቻ ተደምጠው አልቀሩም፤ በማንነቴ ውስጥ ህያው ናቸው።
እኔ የሙዚቃ ባለሙያ አይደለሁም፤ ሙዚቃን ግን በልቤ አዳምጠዋለሁ። በእኔ የዜማ አረዳድ፣ የዚያ ዘመን የዜማ አሠራሮች በቀላሉ የሚደገሙ አይደሉም። ምክንያቱም ዜማው የተፈጠረው በድምፅ ብቻ ሳይሆን፣ በዘመኑ መንፈስም ጭምር ነው። ከዚያ በኋላ የመጡት ዘመናት የራሳቸውን የሙዚቃ ቋንቋ ፈጥረዋል።
ያው ዘመን ሲለወጥ የዜማ ሰዋሰውም የሚለወጥ ይመስለኛል፡፡ ይህም የሥነ ጥበብ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፤ ዋናው ጉዳይ ግን በ1990ዎቹና ከዚያ በኋላ በመጡት ዜማዎች መካከል የተቋረጠ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ መቆራረጡ ለሙዚቃ ባለሙያዎች ትልቅ የጥናት ርዕስ የሚሆንም ነው፡፡
ታዲያ የአህመድ ተሾመ አዲስ አልበም፣ የ1990ዎቹን የዜማ መንፈስ አገኘሁበት፤ የቀድሞውን በቀጥታ ሳይደግም፣ ያንን ለዛ በአዲስ ስልተ ምት የቀነበበ ዜማ ሆኖ አዳመጥኩት። ጉዳዩን ሳይንቲፊካሊ መግለጽ ባልችልም ልቤ ግን አልበሙ በዚያን ጊዜና በዛሬው የሙዚቃ ዘመን መካከል የተዘረጋ የዜማ ድልድይ እንደሆነ ይነግረኛል።
በአጠቃላይ ለእኔ፣ የአህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ጊዜ አይሄድም አዲስ አልበም የአዳዲስ ዜማዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ካለፈ ጊዜና ትዝታ ጋር የተደረገ ውይይት ነው፤ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያስታረቀ የዜማ ድልድይ ነው፤ በዘጠናዎቹ የቀረውን እኔን የመለሰ አልበም ነው። ይመችሽ ዲንቢ!!
ካላመናችሁኝ ደግሞ ከአዲስ አልበሙ መካከል "ጊዜ አይሄድም"፣"አይሽና"፣ "ይረፍዳል" እና "ህልም ነው" አድመጣችሁ ፍረዱኝ፤ ካጠፋሁ እኔ ሳልሆን ዲንቢ ይቀጣል፡፡

ማስተዋል መልሰው አጥናፉ ትባላለች በቅፅል ስሟ ሚሚ ፤ ትንሽ የአ ዕምሮ ህመ ም አለባት ፤ በቀን 14- 11- 2018 ዓ.ም ጠዋት ብዙ ጊዜ ሄዳ ወደምትመጣበት ወደ አራብሳ አቡዬ ቤተክርስቲያን ለመሳለም እንደወጣች አልተመለሰችም።
ሌላ የምታውቀው እና የምትሄድበትም የለም። በእለቱ ለብሳ የወጣችው ሙሉ ነጭ ቀሚስ ነጠላ እና ነጭ ሲሊፐር ጫማ ነው።
የጠፋችበት አካባቢ አራብሳ ነው
ነገር ግን በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ የሀገራችን ልጆች እባካችሁ ካያችኋት ተባበሩን እና ከታች በለጠፍነው ስልክ ቁጥር ደውሉልን።
0935164242 - ሜሮን መልሰው (እህት )
0920427395 - ሸዊት ( እህት)
0913282943 - አቶ መልሰው አጥናፉ ( አባት)

12 days ago
የአፋልጉኝ ተማጽኖ – እባካችሁ ተባበሩን
#ethiopia | ማስተዋል መልሰው አጥናፉ (በቅጽል ስሟ ሚሚ) ትባላለች። ትንሽ የአዕምሮ ሕመም አለባት።
በ2018 ዓ.ም. ሐምሌ 14 ጠዋት እንደተለመደው በአራብሳ የሚገኘውን አቡዬ ቤተክርስቲያን ለመሳለም ከቤቷ ወጥታ ከዚያ በኋላ አልተመለሰችም።
በዕለቱ የለበሰችው፦
- ሙሉ ነጭ ቀሚስ
- ነጭ ነጠላ
- ነጭ ሲሊፐር ጫማ
የጠፋችበት አካባቢ አራብሳ ቢሆንም፣ በየትኛውም አካባቢ ካያችኋት እባካችሁ በፍጥነት ለቤተሰቧ ያሳውቁ። የእናንተ አንድ መረጃ ቤተሰቧን ከከባድ ጭንቀት ሊያድን ይችላል።
የመገናኛ ስልክ ቁጥሮች
- 📞 0935 164242 – ሜሮን መልሰው (እህት)
- 📞 0920 427395 – ሸዊት (እህት)
- 📞 0913 282943 – አቶ መልሰው አጥናፉ (አባት)
እባካችሁ ይህን መረጃ በማጋራት ተባበሩ። አንድ ሼር ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ ሊሆን ይችላል። 🙏

13 days ago
ተጀመረ! ተጀመረ! ተጀመረ!
የባማኮን ሪል እስቴት የሽያጭ ኤክስፖ በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ!
በቃላችን መሰረት የአመቱ ታላቅ ቅናሽ አስጀምረናል!!!
በርካታ ጎብኚዎች በተገኙበት በመጀመሪያው ቀን እስከ 3 ሚሊየን ብር እውነተኛ ቅናሽ እያደረግን ነው።
እርሶስ??
በዝግጅቱ ላይ የሚጠብቁዎት አስገራሚ ነገሮች፡
• 1. ታላቅ የዋጋ ቅናሽ እና ምቹ የክፍያ ሁኔታዎች( እስከ 3 ሚሊዮን ብር ቅናሽ)
2. ለኑሮ ምቹ ለኢንቨስትመንት አዋጭነት ያላቸው አማራጮች
• 3. ጥራታቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የተሟሉ መገልገያዎች
በካዛንቺስ እምብርት በባማኮን ሪል ስቴት ከሐምሌ 24–26 ከጠዋት 2:00 ሰዓት እስከ 12:00 ሰዓት እርስዎም በመገኘት የዚህ ልዩ መድረክ ተጠቃሚ ይሁኑ!
ለ3 ቀናት ብቻ የሚቆይ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ፤ ኑ፣ ይጎብኙ፣ በቁፋሮ ዋጋ ያለቀ ቤት በባማኮን ሪልእስቴት! አዲሱ ስፖርት ፓርክ ፊት ለፊት በሚገኘው ህንጻችን ውስጥ በጉጉት እንጠብቆታለን።
ነገዎን ዛሬ ይግዙ!
ለበለጠ መረጃ
በአጭር የስልክ መስመር 8770 ወይም 0905 400004 ይደውሉልን። በተጨማሪም የባማኮንን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይወዳጁ።
ባማኮን በከፍታ ላይ የተገነባ!

ጄነራል ታደሰ ወረደ ወዴት ተሰወሩ?
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅና በጥበቃ ተሽከርካሪዎች የተከበበ የነበረ ቢሆንም፣ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ግን አብረዋቸው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል።
ጄነራሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌደራል መንግሥት ዳግም በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሚታወስ ነው። ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊትም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር።
በአሁኑ ወቅት በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት በጨመረበት ሁኔታ፣ የጄነራሉ ከአካባቢው መሰወር በትግራይ ክልል አዲስ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል።

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) በሆሊውድ ዝነኛ የብሎክባስተር ፊልሞች "Godzilla vs. Kong" እና "Godzilla x Kong: The New Empire" ላይ “ጂያ” የተሰኘውን ቁልፍ ገጸ-ባህሪ በመወከል የምትታወቀው የ18 ዓመቷ መስማት የተሳናት ወጣት ተዋናይት ኬይሊ ሆትል ማክሰኞ ጠዋት በደረሰባት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቷ ማለፉን ፎክስ ኒውስ ዲጂታል አረጋግጧል።
የተዋናይቷ አባት ጆሹዋ ሆትል በሜሪላንድ ግዛት ውስጥ ስለደረሰው አደጋ በሰጠውና በፌስቡክ በኩል ባስተላለፈው የ23 ደቂቃ የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ (ASL) ቀጥታ ስርጭት መግለጫ፣ ልጁ ወደ ሆስፒታል በመጓዝ ላይ እያለች ልቧ መቆሙን በለቅሶ አስታውቋል። ከተከታታይ መስማት የተሳናቸው ትውልዶች በተገኘችውና የቨርጂኒያ ተወላጅ በሆነችው ኬይሊ ሆትል ሞት ሳቢያ መላው የሆሊውድ የኪነ-ጥበብ ማኅበረሰብ በከባድ ሐዘን ውስጥ ወድቋል።
ይህንን ልብ ሰባሪ ክስተት እና የተዋናይቷን አጭር የሕይወት ጉዞ በጥልቀት ስንመለከተው ኬይሊ በሆሊውድ ውስጥ በገንዘብና በጥቅም ብቻ በሚመራው የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ መስማት ለተሳናቸው አካላት እውነተኛና ተጨባጭ የውክልና መድረክ የፈጠረች ስልታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኗን ያሳያል። በ2021 ዓ.ም. “ጎድዚላ ቨርሰስ ኮንግ” በተሰኘው ታላቅ ፊልም ላይ ከግዙፉ “ኮንግ” ጋር ልዩ የልብ ትስስር ያላትን የጂያን ገጸ-ባህሪ ወክላ ስትወጣ፣ በሆሊውድ ታሪክ ውስጥ መስማት የተሳናቸው ተዋናዮች በትልልቅ የሳይንስ ልብወለድ ፊልሞች ላይ የመሪነት ሚና መጫወት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየች ድንቅ ተሰጥኦ ነበረች።
በ2024 ዓ.ም. በወጣው ሁለተኛው ፊልም ላይም የምልክት ቋንቋን በፊልሙ ውስጥ በስፋት በማስተዋወቅ የራሷን ደማቅ አሻራ አኑራለች።
በተጨማሪም፣ ኬይሊ ሆትል ወደ ትልቁ የፊልም ዓለም ከመግባቷ በፊትም ቢሆን በተለያዩ የንግድ ማስታወቂያዎችና የጥበቃ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ መስማት ለተሳናቸው ማኅበረሰቦች እኩል ዕድል እንዲሰጥ ስትሟገት የቆየች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጭምር ነበረች። ምንም እንኳን ገና በለጋ ዕድሜዋ መክሰሟ እና በሲኒማው ዓለም የጀመረችው ደማቅ ጉዞ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ በአጭር የተቀጨ ቢሆንም፣ በሆሊውድ ውስጥ ያሉ መስማት የተሳናቸው ወጣት ተዋናዮች የወደፊት ዕድል እንዲቀየርና ማግለል እንዲቆም ያደረገችው ተጋድሎ ግን ዘላቂ ውርስ ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን የፊልም ኢንዱስትሪ ተንታኞች በጥብቅ ያመለክታሉ።

20 days ago
ለአእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ለመፍጠር የፊታችን ቅዳሜ ጁላይ 18 2026 ጠዋት በሚኒሶታ ፌለን ፓርክ የእግር ጉዞ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል #mentalhealthmatters #mentalhealthwalk #minnesota #nami
22 days ago
መቐለ ገቡ‼️
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር አርቪን ሆሴ ማሲንጋ የተመራ ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት መቐለ ከተማ ገብቷል።
ልዑኩ በመቐለ ቆይታው በፌደራል መንግስቱና ህውሃት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ለመፍታት እንደሚሞክርና ግጭት በቀጠናው እንዳይከሰት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
አሜሪካ በቅርቡ በህውሃት አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏ ይታወሳል።

23 days ago
አሽከርካሪዎች #እንድታውቁት
ነገ ሀምሌ 08/2018 ዓ.ም ታሪካዊ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ይጀመራል፡፡ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ወደ ከተማችን ገብተዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች በሲኤምሲ መስመር የተባበሩት አደባባይ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር ጠዋትና ማታ ሲገቡና ሲወጡ የሚጓዙባቸው መስመሮች ማለትም ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በሳህሊተ ምህረት አንዲሁም ከኢትዮ ቻይና መስመር በሳህሊተ ምህረት እስከ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር የትራፊክ መጨናነቅ ያጋጥማል፡፡
በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ጉባኤው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በመስመሮቹ የምትጓዙ አሽከርካሪዎች አስቀድማችሁ አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በመዲናዋ አዲስ አበባ በተለይም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሰሚት፣ ገርጂ እና አካባቢው ከመቼውም ጊዜ በላይ የተበራከተው የማጅራት መምታት እና የንጥቂያ ወንጀል የነዋሪውን ደህንነት ክፉኛ እየፈተነ ይገኛል። የወንጀሉ ገጽታ እና የጸጥታ አካላት እየወሰዱት ያለው እርምጃ ነዋሪዎችን እና የፖሊስ ኃላፊዎችን እያወዛገበ ሲሆን፣ የህዝቡን ስጋት እና የፖሊስን ምላሽ እንደሚከተለው አጠናቅረነዋል።
እንደ ነዋሪዎች እና ስማቸው እንዳይጠቀስ ከፈለጉ የውስጥ ፖሊስ አባላት ዘ-ሐበሻ ባገኘው መረጃ፣ የዘረፋው ወንጀል መልኩን ቀይሮ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ለወትሮው በምሽት ይፈጸም የነበረው ማጅራት መምታት፣ አሁን የክረምቱን መግባት እና የጠዋቱን ጨለማ እንደ ሽፋን በመጠቀም ወደ ማለዳ ተሸጋግሯል።
የዚህ አዲስ የማለዳ ላይ ጥቃት ዋነኛ ሰለባ እየሆኑ ያሉት ደግሞ፣ ጠዋት በጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የሚያመሩ አረጋውያን እናቶች ናቸው። ይህ በየዕለቱ እየተፈጸመ ያለ አስነዋሪ ድርጊት ቢሆንም፣ የፖሊስ የበላይ ኃላፊዎች ችግሩን ለመፍታት ከማሰብ ይልቅ ጉዳዩን አድበስብሶ ማለፍን መርጠዋል የሚል ጠንካራ ወቀሳ ከውስጥ ምንጮች ቀርቧል። "የህዝቡ ስቃይ ዝም ተብሎ ስለታለፈ እና ኃላፊዎች እርምጃ ባለመውሰዳቸው መረጃውን ለሚዲያ አድርሰናል" ያሉት የውስጥ ምንጮች፣ ተቋማዊ ቸልተኝነት መኖሩን በጽኑ ተችተዋል።
በተነሳው የ"ቸልተኝነት እና የዝምታ" ክስ ላይ ምላሽ የሰጡን የፖሊስ ኃላፊዎች፣ ተቋሙ በምንም መልኩ ዝምታን እንዳልመረጠ አስታውቀዋል። ኃላፊው ለቀረበባቸው ወቀሳ በሰጡት ምላሽ፣ ፖሊስ ወንጀለኞች በስፋት ይንቀሳቀሱባቸዋል የተባሉትን ሰሚት፣ ገርጂ እና 'ጥላሁን' የተባሉ አካባቢዎችን ለይቶ ሰፊ የጸጥታ ማስከበር አሰሳ እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ወንጀለኞች የሚሰባሰቡባቸውን ህገ-ወጥ የሺሻ ቤቶችን የማፍረስ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ በአንድ ቀን በተደረገ ኦፕሬሽን ብቻ 80 ያህል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ማስመለስ መቻሉን ፖሊስ በምላሹ አስረድቷል። ከቀን 12 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 1 ሰዓት ድረስ የዘለቀ ጥብቅ አሰሳ በየቀኑ እየተካሄደ መሆኑንም አክለዋል።
ከዚህ ቀደም የነበሩ አመራሮች የጸጥታ ስራዎችን ለሚዲያ ፍጆታ ይጠቀሙበት እንደነበር የወቀሱት ኃላፊው፣ "አሁን ያለው የጸጥታ መዋቅር ማወናበድ ሳይሆን በተጨባጭ ወንጀልን ከስረ-መሰረቱ ለማጥፋት ትልቅ ኦፕሬሽን እየሰራ ስለሆነ ነው እንጂ የተኛንበት ጊዜ የለም" ሲሉ ተከራክረዋል።
በፖሊስ ኃላፊው ምላሽ ውስጥ ጎልቶ የወጣው ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ በነዚህ አካባቢዎች ያለው የውጭ ዜጎች ወንጀል ተሳትፎ ነው። ከዩጋንዳ፣ ናይጄሪያ እና ሌሎችም ሀገራት የመጡ፣ እንዲሁም ህጋዊ የጉዞ ሰነድ የሌላቸው በርካታ ስደተኞች በአካባቢው ተሰባስበው ይገኛሉ። እነዚህ የውጭ ዜጎች በስርቆት፣ በዝሙት አዳሪነት እና በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውንና ፖሊስም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደባቸው መሆኑ ተጠቁሟል።
የህዝቡን የዕለት ተዕለት ስቃይ እና የፖሊስን ሪፖርት ጎን ለጎን ስንመዝነው፣ አንድ ትልቅ የአሰራር እና የትኩረት ክፍተት ይታያል። በአንድ በኩል ህዝቡ እና አረጋውያን እናቶች ጥቃት እየደረሰባቸው ያለው በማለዳው (ጠዋት) የጨለማ ሰዓት መሆኑን እያማረሩ ነው። በሌላ በኩል ግን ፖሊስ ትልቅ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ብሎ ያቀረበው ማስረጃ "ከቀን 12 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 1 ሰዓት" የሚያደርገውን አሰሳ ነው። ይህ የሚያሳየው ወንጀለኞቹ የፖሊስን የጥበቃ ሰዓት ክፍተት አጥንተው የዘረፋ ሰዓታቸውን ወደ ጠዋት ማለዳ ሲያሸጋግሩ፣ ፖሊስ ግን አሁንም ትኩረቱን ምሽት ላይ ብቻ ማድረጉን ነው።
ፖሊስ "ለሚዲያ ፍጆታ ሳይሆን በተግባር እየሰራሁ ነው" ማለቱ የሚበረታታ ቢሆንም ስኬቱ ሊለካ የሚገባው በተያዙ ስልኮች ብዛት ብቻ ሳይሆን በማለዳ ወደ ቤተክርስቲያን እና ወደ ስራ የሚወጣው ነዋሪ በሚያገኘው የደህንነት ዋስትና ነው። በመሆኑም የጸጥታ አካላት የኦፕሬሽን ስልታቸውን እና የሰዓት ስምሪታቸውን ነዋሪው እየተጠቃበት ካለው የማለዳ ሰዓት ጋር ሊያስተካክሉ ይገባል። ፖሊስ አደረግኩት የሚለው ኦፕሬሽን በተግባር የህዝቡን ስጋት እስካላቀለለ ድረስ፣ "ቸልተኝነት አለ" የሚለው የህዝብ ቅሬታ መቀጠሉ አይቀርም።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ የጀርባ አጥንት የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ መቆጣጠር እንዳለባት አስታወቁ። ይህ የተሰማው አሜሪካ እና ኢራን በቁልፍ የውሃ መስመሩ ላይ እያደረጉት ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ እጅግ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት ነው።
ትራምፕ ዛሬ ሰኞ ከ'Fox & Friends' ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ "ሰርጡን እንጠብቀዋለን፤ ምናልባትም እኛ እናስተዳድረዋለን። የሰርጡ 'ጠባቂ መልአክ' እንሆናለን" ብለዋል። አሜሪካ ይህንን ጥበቃ በማድረጓ ከሌሎች ሀገራት ወጪዋ ሊተካላት (ካሳ ሊከፈላት) እንደሚገባም አክለዋል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካ በኢራን ላይ የባህር ላይ እገዳ ዳግም መጣሏን ያወጁት ፕሬዝዳንቱ፣ በሰርጡ ለሚያልፉ የጭነት መርከቦች ለደህንነት ጥበቃ ወጪ የሚውል የ20 በመቶ ታክስ እንደሚጣል አስታውቀዋል።
የሀገራቱ ፍጥጫ የነዳጅ ዋጋን ሰኞ ጠዋት ከ3 በመቶ በላይ አሻቅቦታል። ዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፈው ሳምንት ከነበረበት 71.99 ዶላር በአንድ በርሜል ወደ 80 ዶላር ተጠግቷል። ምንም እንኳን ዋጋው በሚያዝያ ወር ጦርነቱ አይሎ በነበረበት ወቅት ከተመዘገበው የ126 ዶላር ከፍተኛ ጣሪያ አሁንም ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ስጋት "እጅግ አደገኛ" ደረጃ ላይ መድረሱ በዓለም ገበያ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ፈጥሯል። በአውሮፓ፣ በእስያ እና በዎል ስትሪት የአክሲዮን ገበያዎችም ማሽቆልቆል ታይቷል።
የአሜሪካ ጦር ቅዳሜ ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ የኢራን ኃይሎች በቆጵሮስ ባንዲራ በምትጓዝ የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በኢራን ላይ "የዚህን ሳምንት ሶስተኛ ዙር ጥቃት" መሰንዘሩን አስታውቋል። እሁድ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ቴህራን በኦማን የባህር ዳርቻ ሌላ መርከብ ከጥቅም ውጪ ማድረጓን ተከትሎ፣ የኢራንን የማጥቃት አቅም ለማዳከም አሜሪካ ተጨማሪ ጥቃቶችን አድርሳለች።
ኢራን በበኩሏ በባህሬን፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ እና ኦማን በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት አድርሳለች። የአሜሪካ ባህር ኃይል 5ኛ እዝ በሚገኝባት ባህሬን እና በዮርዳኖስ፣ ከኢራን የተተኮሱ በርካታ ሚሳኤሎችን በአየር ላይ ማክሸፍ መቻሉ ተዘግቧል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ፣ ኢራን የሰላም ስምምነቱን በመጣስ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነች ተከራክረዋል።
ቴህራን በሳምንቱ መጨረሻ የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋቷን ያሳወቀች ሲሆን፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የውሃ መስመሩ ዳግም ሙሉ በሙሉ ሊከፈት የሚችለው "የአሜሪካ ጦር ጠብ አጫሪ ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ ብቻ ነው" ብሏል። ትራምፕ በበኩላቸው ሰርጡ ክፍት ነው ብለው ቢከራከሩም፣ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ግን በእጅጉ ቀንሷል። 'Kpler' የተባለው የመርከቦች ክትትል መረጃ እንደሚያሳየው፣ ከጦርነቱ በፊት በቀን 138 መርከቦች ያልፉበት ከነበረው መስመር፣ እሁድ ዕለት ያለፉት 6 መርከቦች ብቻ ናቸው።
ባለፈው ሰኔ 17 አሜሪካ እና ኢራን ለ60 ቀናት የሚቆይ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት (MoU) ተፈራርመው የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ስምምነት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የፈረሰ ይመስላል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስከ ነሐሴ አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በኔቶ ጉባኤ ላይ ስምምነቱ "አብቅቷል" ማለታቸውን ተከትሎ የሰላም ድርድሩ ተስፋ ጨልሟል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ባለሀብቶች በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ለመጣው ውጥረት ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ሰኞ ጠዋት የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያዎች ማሽቆልቆል አሳይተዋል። የዋጋ ግሽበት ስጋትን ተከትሎ ሦስቱም ዋና ዋና የአክሲዮን ገበያ ጠቋሚዎች (Dow Jones, Nasdaq, እና S&P 500) የቀነሱ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ4 በመቶ በላይ ጭማሪ በማሳየት አንድ በርሜል 79 ዶላር አካባቢ ደርሷል።
አሜሪካ እና ኢራን በሳምንቱ መጨረሻ የጥቃት ልውውጦችን ዳግም የጀመሩ ሲሆን፣ ቴህራን ለዓለም አቀፍ ንግድ ቁልፍ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ መዝጋቷን አስታውቃለች። ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውሃ መስመሩ ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል እና በኢራን ወደቦች ላይ እገዳ ዳግም እንደሚጥሉ ተናግረዋል። ይህ እገዳ የኢራን መርከቦች ወይም ደንበኞች ወደቦቹን እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ቢሆንም፣ የ20 በመቶ የጭነት ታክስ ለሚከፍሉ የሌሎች ሀገራት መርከቦች ግን ክፍት እንደሚሆን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረው ስጋት የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ መዋዠቅ እንዲያሳይ አድርጎታል። ምንም እንኳን ዋጋው በቅርብ ጊዜ በተሰሙት ዜናዎች ምክንያት ጭማሪ ቢያሳይም፣ አሁንም ባለፈው ግንቦት ወር ከነበረበት ደረጃ በእጅጉ ያነሰ ነው።
በተጨማሪም የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያዎች የቴክኖሎጂ እና የማይክሮቺፕ አምራች ኩባንያዎች ወሩን በከባድ ፈተና መጀመራቸው ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል። ባለሀብቶች በኩባንያዎቹ የተጋነነ የዋጋ ተመን እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ያልተጨበጠ የገበያ ግለት ዙሪያ እያመነቱ ይገኛሉ። በዚህም የተነሳ የNvidia ፣ ስፔስ ኤክስ እና ኢንቴል አክሲዮኖች በጠዋቱ የግብይት ክፍለ ጊዜ ቅናሽ አሳይተዋል።

24 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢራን ላይ በቅርቡ ለተፈጸሙት የአየር ጥቃቶች በስተጀርባ ዩናይትድ ስቴትስ እጇ እንዳለበት በዋሽንግተን የሚገኙ ሚዲያዎችና የውስጥ ምንጮች እየዘገቡ ይገኛሉ። ይሁንና ይህንን መረጃ በተመለከተ የኋይት ሀውስ ሆነ የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ እስካሁን በይፋ የሰጡት ማረጋገጫ የለም።
እንደ ወጡት ሪፖርቶች ገለጻ የአሜሪካ ጥቃቶች በዋናነት ኢላማ ያደረጉት በኢራን ውስጥ የሚገኙ የአየር መከላከያ ስርአቶችን እና የሚሳኤል ማከማቻ ቦታዎችን ነው።
በሌላ በኩል፣ የኢራን ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ዙሪያ ፍጥጫው በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ጠዋት በሰጡት ቃለ ምልልስ በሆርሙዝ ሰርጥ ውስጥ መደበኛ የንግድ መርከቦች እንደልብ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን እና የውሃ መስመሩ ክፍት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የኋይት ሀውስ አስተዳደር አሁንም ቢሆን ሙሉ እምነቱን የጣለው ከኢራን ጋር በሚደረግ ስምምነት ወይም አመኔታ ላይ ሳይሆን፣ በራሱ ወታደራዊ አቅም የኢራንን ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ የመቀልበስ እና የማስፈራራት ብቃት ላይ መሆኑ ተመላክቷል።

25 days ago
#ጤናመረጃ 🍋
10 አስገራሚ የሎሚ የጤና ጥቅሞች!
ሎሚን🍋 አዘውትሮ መጠቀም ከሚያስገኛቸው
ጥቅሞች ዋና ዋናዎቹን አጠር አድርገን እንያለን።
1) በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል፤ በቪታሚን ሲ የበለፀገ በመሆኑ ከጉንፋንና ከተለያዩ ተላላፊ ቫይረሶች ይከላከላል።
2) ለምግብ መፈጨት ሥርዓት፤ ጠዋት በለጋ ውሃ መጠጣት በጉበት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድና አንጀትን ለማረጋጋት ይረዳል።
3) የቆዳን ውበት ይጠብቃል፤ የኮላጅን ምርትን በማፋጠን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፤ መልክን ያጠራል።
4) የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያለው ሲትሪክ አሲድ የካልሲየም ጠጠር እንዳይፈጠርና በሽንት እንዲወገድ ያደርጋል።
5) የደም ማነስን ይከላከላል፤ ሰውነታችን ከምግብ የሚያገኘውን የብረት (Iron) ንጥረ ነገር በቀላሉ እንዲመጥ ያግዛል።
6) ለአፍ ጠረን መፍትሔ ነው፤ በአፍ ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን በማጥፋት ጠረንን ያድሳል፤ የጥርስ ሕመምንም ያስታግሳል።
7) ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል፤ በውስጡ ያለው የፔክቲን ፋይበር የረሃብ ስሜትን የሚቀንስና ስብን ለማቃጠል የሚረዳ ነው።
8) የልብን ጤንነት ይጠብቃል፤ መጥፎ ኮሌስትሮልን በመቀነስ ለልብ ሕመም እና ለድንገተኛ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድልን ያጠባል።
9) ካንሰርን ይከላከላል፤ በውስጡ ያሉ ተፈጥሯዊ ውህዶች (Flavonoids) የካንሰር ሴሎች እንዳይፈጠሩና እንዳይስፋፉ ይረዳሉ።
10) የደም ግፊትን ያስተካክላል፤ በውስጡ የሚገኘው ፖታሲየም የደም ስሮችን በማዝናናት የደም ግፊት ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሉዊስ የቀጥታ በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴቲቷ ሀገር ሞሪሺየስ ዋና ከተማ ፖርት ሉዊስ ከነገ ጠዋት ጀምሮ የቀጥታ በረራ ማድረግ ይጀምራል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንዳሉት፤ የቀጥታ በረራው የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ለሀገራቱ ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ይዞ ይመጣል።
በቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ በባሕር ዳርጃዎቿ የምትታወቀው ሞሪሺየስ በታሪክና ባሕል ቱሪዝም ከበለፀገችው ኢትዮጵያ ጋር የቀጥታ በረራው መተሳሰር የቱሪስት ፍሰትን ያቀላጥፋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሞሪሺየስ አምባሳደር ኢንድራርጂት ባቡዋ በበኩላቸው፤ የቀጥታ በረራው በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት ነጋዴዎች በቀላሉ እንዲገናኙ፣ የንግድ ልውውጥ እንዲያፋጥኑ እና የጋራ ኢንቨስትመንት እንዲያቋቁሙ ምቹ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
የሀገራቱን የገቢና ወጪ ንግድ ለማሳደግ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና የባሕል ልውውጥን ለማጠናከር አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 145 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በ41 የአፍሪካ ሀገራት 62 መዳረሻዎችን በማስፋፋት የአህጉሪቱን ብሎም ዓለም አቀፍ ትስስርን ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሉዊስ ከተማ በሳምንት 3 ቀን በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በታምራት ደለሊ

26 days ago
💎 ወርቃማ ክረምት ለልጅዎ ከዮቶጵያ
ዮቶጵያ የሕጻናትና ታደጊዎች ሁለንተናዊ ብቃት ካምፕ፤
👫 ልጅዎን 2 ወራት ከእኛ ጋር እንዲያሳልፍ ያድርጉ፤ በትክክል የማይቆጩበት ውሳኔ ይሆናል፤
👉 በቆይታቸው፤
🧠 የአእምሮ ምህንድስና፣
🏃♂አካል ብቃትና መዝናኛ
⛪️🕌 እንደየ እምነታቸው ስነ ምግባር እና ሃይማኖታዊ እውቀት የሚያገኙበት መንፈሳዊ ትምህርትን ያገኛሉ።
🗓 በሳምንት 5 ቀናት ይቆያሉ፤
ጠዋት በትምርህት ከሰዓት በጨዋታ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ደስ ብሏቸው ያሳልፋሉ።
🏥 አስተማማኝ ጥበቃና የነርስ ባለሙያዎች ተዘጋጅተዋል፤ የልጅዎን ሳምንታዊ እድገትም መከታተል ይችላሉ።
🎁 ከ2 በላይ ልጆች ለሚያስመዘግቡ የ10% ቅናሽ ይደረግላቸዋል፣ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው ልጅዎን ቀድመው ያስመዝግቡ!።
📍የስልጠና ቦታዎች፤
ቁጥር. 1 ብስራተ ገብርኤል
ቁጥር. 2 አያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ
📲 ለምዝገባ በ0963999966 / 0963999977
ይደውሉ፤
ትክክለኛ የክረምት ምርጫ ለልጅዎ
ከዮቶጵያ የሕፃናትና ታዳጊዎች ሁለንተናዊ የብቃት ካምፕ !!!!

ኢቭ ሳኒተሪ "ጸደይ ሞዴስ" የሴቶች ንፅህና መጠበቂያን አስተዋወቀ
#fastmereja I ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ10 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ከ50 በላይ ተማሪዎች የአንድ ዓመት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በፍሬንድሺፕ ፓርክ አካሂዷል።
ዛሬ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የድርጅቱ አዲስ ምርት የሆነው "ፀደይ ሞዴስ" ያስተዋወቀ ሲሆን "አንድም ተማሪ በንፅህና መጠበቂያ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ መቅረት የለባትም" በሚል ሃሳብ በሴት ተማሪዎች ላይ የሚታየውን የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደምም በከተማዋ ለሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ የድጋፍ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።
ላለፉት 20 ዓመታት በሴቶችና ህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ኢንዱስትሪ ሲንቀሳቀስ የቆየው ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ፤ በዕለቱ በተካሄደው የጠዋት መርሃ-ግብር የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ታዳጊ ሴቶች በወር አበባ ዑደት፣ በንፅህና መጠበቂያ ምርቶች አጠቃቀም፣ በሴቶች ጤና እና ማብቃት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እና ውድድሮችን በማካሄድ የተለያየ የገንዘብ ሽልማት በመስጠት አጠናቋል።

27 days ago
ለእናቱ የገባውን ቃል ለመጠበቅ አስክሬን ቤት አስቀምጦ ለተፈተነው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት ነው::
ከሦስት ሳምንታት በፊት እናቱ ባረፉበት ዕለት የገባውን ቃል ለማክበር ሲል አስክሬን ቤት ውስጥ ትቶ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናውን በመፈተን መላውን የሀገሪቱን ሕዝብ በከፍተኛ ሐዘን ያስለቀሰውና ያስደመመው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም፣ አዲስ የመኖሪያ ቤት ሊገነባለት መሆኑ ተሰማ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር የሚኖረው ይህ የ14 ዓመት ታዳጊ፣ በወቅቱ እናቱ በጽኑ ታመው በነበሩበት ወቅት “እኔ አንድ ነገር ብሆን እንኳ ለዓመታት የለፋህበትን ፈተና እንዳታቋርጥ” በማለት ያስገቡትን ጥብቅ ቃል ለመጠበቅ የጠዋት ፈተናውን ተፈትኖ፣ ከሰዓት ደግሞ እናቱን አልቅሶና ቀብሮ በመመለስ የከሰዓት ፈተናውን ማጠናቀቁና “ቃልሽን አላጠፍኩም እማ!” ማለቱ ይታወሳል።
ዛሬ በተሰማው አዲስና ተስፋ ሰጪ መረጃ መሠረት፣ ለታዳጊውና ለታናናሽ ወንድሞቹ ቋሚ የቤት መፍትሔ ለመስጠት የሸገር ከተማ የኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለቤት ግንባታ የሚሆን መሬት በይፋ አዘጋጅቶ አስረክቧል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የመኖሪያ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለታዳጊዎቹ ለማስረከብ ቃል ገብቷል።
ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ በጅጅጋ ከተማ ሌላ ትዳር መሥርቶ በመኖሩ ምክንያት እናታቸውን አጥተው ብቻቸውን ለቀሩት ለእነዚህ ወንድማማቾች የተደረገው ይህ የመሬትና የቤት ግንባታ ድጋፍ፣ የታዳጊውን ታማኝነትና ብርታት ያከበረ እንዲሁም ማኅበራዊ አጋርነትን በተግባር ያሳየ መሆኑ ተገልጿል።

28 days ago
ተጠንቀቁ
ያስደነግጣል ስልኩ ላይ ለረጅም ሰዓታት አቀርቅሮ በማሳለፉ ፓራላይዝ የሆነው የ19 ዓመት ወጣት
ቻይናዊው የ19 ዓመቱ ሻዮ ዶንግ ለረጅም ሰዓታት ስልኩ ላይ አቀርቅሮ በማሳለፉ የተነሳ በከፊል ፓራላይዝ ሆኗል።
ስልኩ ላይ ማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመከታተል ሙሉ ጊዜውን በሚባል ደረጃ ላይ የሚያሳልፈው ወጣቱ ከጊዜ በኋላ በአንገቱ፣ በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ነገሮችም እየተባባሱ ሄደው አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እግሩ መንቀሳቀስ አቅቶት እንደነበር ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
ዶክተሮችም በፍጥነት ወደ ቀዶ ጥገና ወስደውት በአከርካሪው ላይ ከፍተኛ የደም መርጋት መኖሩ አረጋገጡ።
ወጣቱ ያለማቋረጥ ስልኩ ላይ አቀርቅሮ ማሳለፉ በአከርካሪው ውስጥ ያለውን የደም ቧንቧ ተሰብሯል። ይህም ደም በውስጡ እንዲረጋ እና በከፊል ሽባ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል ዶክተሮቹ።
እንደ ዕድል ሆኖ ግን፣ ሻዮ ዶንግ አሁን ላይ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴን እያደረገ ሲሆን፤ ዶክተሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚድን ያምናሉ።
አንገትን ለረጅም ጊዜ አቀርቅሮ ስልክ ላይ ማሳለፍ የደም ዝውውርን በመዝጋት ራስ ምታትን፣ ማዞርን፣ ድካምን እና መደንዘዝን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
ሁኔታዎች እየከፉ ሲሄዱ ደግሞ ወደ ስትሮክ ወይም ፓራላይዝ እስከመሆን ሊዳርግም ይችላል ይላሉ
#ቤት_እየዋለ_ወይም / ስልክ #ለሚያበዛ ጓደኛቹ ላኩለት

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ውድድር (Mister Classy Model International) ላይ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው ሞዴል ዘላለም ተድላ መስፍን በቅጽል ስሙ ሞዴል ዞላ አሸናፊ በመሆን የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጓል።
ወጣቱ ሞዴል በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አምስት የተለያዩ ዘርፎችን በበላይነት አጠናቋል። ባሸነፈባቸው ዘርፎችም የዓመቱ ሞዴል አሸናፊ፣ የምርጥ አረማመድ አሸናፊ፣ የእጅግ አስተዋይ ተወዳዳሪ አሸናፊ፣ የምርጥ መደበኛ አለባበስ አሸናፊ እንዲሁም የውድድሩ የሶስተኛ ደረጃ (3rd Runner Up) አሸናፊ በመሆን ዋንጫዎችን ጠቅልሏል። የውድድሩን ርዕሶች እና አጠራሮች ሙሉ በሙሉ ወደ አማርኛ ለመመለስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሞዴሉ በሁሉም የውድድሩ መመዘኛዎች ብልጫ ወስዷል።
1. CLASSY MODEL EARTH WINNER
2. BEST CATWALK WINNER
3. MOST INTELLIGENT WINNER
4. BEST IN FORMAL WEAR WINNER
5. 3RD RUNNER UP
ይህ ተደጋጋሚ ድል ለወጣቱ ሞዴል የመጀመሪያው አይደለም። ከአንድ ወር በፊት በኢንዶኔዥያ ጃካርታ በተካሄደው ሌላ ዓለም አቀፍ የባህል ሞዴሊንግ ውድድር ላይ ተሳትፎ በተመሳሳይ አራት የተለያዩ ሽልማቶችን ይዞ መመለሱ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በተከታታይ እና በተደራራቢ ውጤት በማስመዝገብ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ወንድ ሞዴል ለመሆን በቅቷል። ይህን ታላቅ ድል ያስመዘገበው ሞዴል ዘላለም ተድላ፣ የፊታችን አርብ ጠዋት 2፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል።

Comments