(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ የጀርባ አጥንት የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ መቆጣጠር እንዳለባት አስታወቁ። ይህ የተሰማው አሜሪካ እና ኢራን በቁልፍ የውሃ መስመሩ ላይ እያደረጉት ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ እጅግ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት ነው።
ትራምፕ ዛሬ ሰኞ ከ'Fox & Friends' ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ "ሰርጡን እንጠብቀዋለን፤ ምናልባትም እኛ እናስተዳድረዋለን። የሰርጡ 'ጠባቂ መልአክ' እንሆናለን" ብለዋል። አሜሪካ ይህንን ጥበቃ በማድረጓ ከሌሎች ሀገራት ወጪዋ ሊተካላት (ካሳ ሊከፈላት) እንደሚገባም አክለዋል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካ በኢራን ላይ የባህር ላይ እገዳ ዳግም መጣሏን ያወጁት ፕሬዝዳንቱ፣ በሰርጡ ለሚያልፉ የጭነት መርከቦች ለደህንነት ጥበቃ ወጪ የሚውል የ20 በመቶ ታክስ እንደሚጣል አስታውቀዋል።
የሀገራቱ ፍጥጫ የነዳጅ ዋጋን ሰኞ ጠዋት ከ3 በመቶ በላይ አሻቅቦታል። ዓለም አቀፍ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፈው ሳምንት ከነበረበት 71.99 ዶላር በአንድ በርሜል ወደ 80 ዶላር ተጠግቷል። ምንም እንኳን ዋጋው በሚያዝያ ወር ጦርነቱ አይሎ በነበረበት ወቅት ከተመዘገበው የ126 ዶላር ከፍተኛ ጣሪያ አሁንም ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ስጋት "እጅግ አደገኛ" ደረጃ ላይ መድረሱ በዓለም ገበያ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ፈጥሯል። በአውሮፓ፣ በእስያ እና በዎል ስትሪት የአክሲዮን ገበያዎችም ማሽቆልቆል ታይቷል።
የአሜሪካ ጦር ቅዳሜ ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ የኢራን ኃይሎች በቆጵሮስ ባንዲራ በምትጓዝ የንግድ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በኢራን ላይ "የዚህን ሳምንት ሶስተኛ ዙር ጥቃት" መሰንዘሩን አስታውቋል። እሁድ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ቴህራን በኦማን የባህር ዳርቻ ሌላ መርከብ ከጥቅም ውጪ ማድረጓን ተከትሎ፣ የኢራንን የማጥቃት አቅም ለማዳከም አሜሪካ ተጨማሪ ጥቃቶችን አድርሳለች።
ኢራን በበኩሏ በባህሬን፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ እና ኦማን በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት አድርሳለች። የአሜሪካ ባህር ኃይል 5ኛ እዝ በሚገኝባት ባህሬን እና በዮርዳኖስ፣ ከኢራን የተተኮሱ በርካታ ሚሳኤሎችን በአየር ላይ ማክሸፍ መቻሉ ተዘግቧል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ፣ ኢራን የሰላም ስምምነቱን በመጣስ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነች ተከራክረዋል።
ቴህራን በሳምንቱ መጨረሻ የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋቷን ያሳወቀች ሲሆን፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የውሃ መስመሩ ዳግም ሙሉ በሙሉ ሊከፈት የሚችለው "የአሜሪካ ጦር ጠብ አጫሪ ጣልቃ ገብነት ሲያበቃ ብቻ ነው" ብሏል። ትራምፕ በበኩላቸው ሰርጡ ክፍት ነው ብለው ቢከራከሩም፣ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ግን በእጅጉ ቀንሷል። 'Kpler' የተባለው የመርከቦች ክትትል መረጃ እንደሚያሳየው፣ ከጦርነቱ በፊት በቀን 138 መርከቦች ያልፉበት ከነበረው መስመር፣ እሁድ ዕለት ያለፉት 6 መርከቦች ብቻ ናቸው።
ባለፈው ሰኔ 17 አሜሪካ እና ኢራን ለ60 ቀናት የሚቆይ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት (MoU) ተፈራርመው የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ስምምነት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የፈረሰ ይመስላል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስከ ነሐሴ አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በኔቶ ጉባኤ ላይ ስምምነቱ "አብቅቷል" ማለታቸውን ተከትሎ የሰላም ድርድሩ ተስፋ ጨልሟል።

3 months ago