(ዘ-ሐበሻ ዜና) በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሞዴሊንግ ውድድር (Mister Classy Model International) ላይ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው ሞዴል ዘላለም ተድላ መስፍን በቅጽል ስሙ ሞዴል ዞላ አሸናፊ በመሆን የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጓል።
ወጣቱ ሞዴል በዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አምስት የተለያዩ ዘርፎችን በበላይነት አጠናቋል። ባሸነፈባቸው ዘርፎችም የዓመቱ ሞዴል አሸናፊ፣ የምርጥ አረማመድ አሸናፊ፣ የእጅግ አስተዋይ ተወዳዳሪ አሸናፊ፣ የምርጥ መደበኛ አለባበስ አሸናፊ እንዲሁም የውድድሩ የሶስተኛ ደረጃ (3rd Runner Up) አሸናፊ በመሆን ዋንጫዎችን ጠቅልሏል። የውድድሩን ርዕሶች እና አጠራሮች ሙሉ በሙሉ ወደ አማርኛ ለመመለስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሞዴሉ በሁሉም የውድድሩ መመዘኛዎች ብልጫ ወስዷል።
1. CLASSY MODEL EARTH WINNER
2. BEST CATWALK WINNER
3. MOST INTELLIGENT WINNER
4. BEST IN FORMAL WEAR WINNER
5. 3RD RUNNER UP
ይህ ተደጋጋሚ ድል ለወጣቱ ሞዴል የመጀመሪያው አይደለም። ከአንድ ወር በፊት በኢንዶኔዥያ ጃካርታ በተካሄደው ሌላ ዓለም አቀፍ የባህል ሞዴሊንግ ውድድር ላይ ተሳትፎ በተመሳሳይ አራት የተለያዩ ሽልማቶችን ይዞ መመለሱ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በተከታታይ እና በተደራራቢ ውጤት በማስመዝገብ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ወንድ ሞዴል ለመሆን በቅቷል። ይህን ታላቅ ድል ያስመዘገበው ሞዴል ዘላለም ተድላ፣ የፊታችን አርብ ጠዋት 2፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል።

3 months ago