(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢራን ላይ በቅርቡ ለተፈጸሙት የአየር ጥቃቶች በስተጀርባ ዩናይትድ ስቴትስ እጇ እንዳለበት በዋሽንግተን የሚገኙ ሚዲያዎችና የውስጥ ምንጮች እየዘገቡ ይገኛሉ። ይሁንና ይህንን መረጃ በተመለከተ የኋይት ሀውስ ሆነ የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ እስካሁን በይፋ የሰጡት ማረጋገጫ የለም።
እንደ ወጡት ሪፖርቶች ገለጻ የአሜሪካ ጥቃቶች በዋናነት ኢላማ ያደረጉት በኢራን ውስጥ የሚገኙ የአየር መከላከያ ስርአቶችን እና የሚሳኤል ማከማቻ ቦታዎችን ነው።
በሌላ በኩል፣ የኢራን ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ዙሪያ ፍጥጫው በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ጠዋት በሰጡት ቃለ ምልልስ በሆርሙዝ ሰርጥ ውስጥ መደበኛ የንግድ መርከቦች እንደልብ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን እና የውሃ መስመሩ ክፍት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የኋይት ሀውስ አስተዳደር አሁንም ቢሆን ሙሉ እምነቱን የጣለው ከኢራን ጋር በሚደረግ ስምምነት ወይም አመኔታ ላይ ሳይሆን፣ በራሱ ወታደራዊ አቅም የኢራንን ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ የመቀልበስ እና የማስፈራራት ብቃት ላይ መሆኑ ተመላክቷል።

26 days ago