Logo
FastMereja
ኢቭ ሳኒተሪ "ጸደይ ሞዴስ" የሴቶች ንፅህና መጠበቂያን አስተዋወቀ

​#fastmereja I ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከ10 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ከ50 በላይ ተማሪዎች የአንድ ዓመት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በፍሬንድሺፕ ፓርክ አካሂዷል።

ዛሬ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የድርጅቱ አዲስ ምርት የሆነው "ፀደይ ሞዴስ" ያስተዋወቀ ሲሆን ​"አንድም ተማሪ በንፅህና መጠበቂያ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ መቅረት የለባትም" በሚል ሃሳብ በሴት ተማሪዎች ላይ የሚታየውን የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደምም በከተማዋ ለሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ የድጋፍ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።

​ላለፉት 20 ዓመታት በሴቶችና ህፃናት የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ኢንዱስትሪ ሲንቀሳቀስ የቆየው ኢቭ ሳኒተሪ ፕሮዳክቶች ማኑፋክቸሪንግ፤ በዕለቱ በተካሄደው የጠዋት መርሃ-ግብር የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ታዳጊ ሴቶች በወር አበባ ዑደት፣ በንፅህና መጠበቂያ ምርቶች አጠቃቀም፣ በሴቶች ጤና እና ማብቃት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እና ውድድሮችን በማካሄድ የተለያየ የገንዘብ ሽልማት በመስጠት አጠናቋል።

28 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.