Logo
SeledaPost
ተጠንቀቁ

ያስደነግጣል ስልኩ ላይ ለረጅም ሰዓታት አቀርቅሮ በማሳለፉ ፓራላይዝ የሆነው የ19 ዓመት ወጣት

ቻይናዊው የ19 ዓመቱ ሻዮ ዶንግ ለረጅም ሰዓታት ስልኩ ላይ አቀርቅሮ በማሳለፉ የተነሳ በከፊል ፓራላይዝ ሆኗል።

ስልኩ ላይ ማኀበራዊ ሚዲያዎችን በመከታተል ሙሉ ጊዜውን በሚባል ደረጃ ላይ የሚያሳልፈው ወጣቱ  ከጊዜ በኋላ በአንገቱ፣ በእጆቹ እና በእግሮቹ ላይ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማው ጀመር።
ነገሮችም እየተባባሱ ሄደው አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እግሩ መንቀሳቀስ አቅቶት እንደነበር ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ዶክተሮችም በፍጥነት ወደ ቀዶ ጥገና ወስደውት በአከርካሪው ላይ ከፍተኛ የደም መርጋት መኖሩ አረጋገጡ።
ወጣቱ ያለማቋረጥ ስልኩ ላይ አቀርቅሮ ማሳለፉ በአከርካሪው ውስጥ ያለውን የደም ቧንቧ ተሰብሯል። ይህም ደም በውስጡ እንዲረጋ እና በከፊል ሽባ እንዲሆን አድርጓል ብለዋል ዶክተሮቹ።

እንደ ዕድል ሆኖ ግን፣ ሻዮ ዶንግ አሁን ላይ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴን እያደረገ ሲሆን፤ ዶክተሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚድን ያምናሉ።
አንገትን ለረጅም ጊዜ አቀርቅሮ ስልክ ላይ ማሳለፍ የደም ዝውውርን በመዝጋት ራስ ምታትን፣ ማዞርን፣ ድካምን እና መደንዘዝን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
ሁኔታዎች እየከፉ ሲሄዱ ደግሞ ወደ ስትሮክ ወይም ፓራላይዝ እስከመሆን ሊዳርግም ይችላል ይላሉ

#ቤት_እየዋለ_ወይም / ስልክ #ለሚያበዛ ጓደኛቹ ላኩለት

Seledadotio
Seledadotio
28 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.