1 month ago
#ሶፊያ #ኮንታ
#ethiopia | የኮንታ ብሔር ሴቶች በባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች አምረው በህብረት አደባባይ የሚወጡበት ደማቅ ስነ ስርዓት
የኮንታ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ሴቶች ውበታቸውንና ማንነታቸውን የሚያንጸባርቁ ባህላዊ አልባሳትን እንዲሁም ልዩ ልዩ ባህላዊ ጌጣጌጦችን በማድረግ በቡድን በመሆን በአደባባይ ደምቀው የሚታዩበትና የሚከብሩበት ልዩ ሁነት ነው።
#ሶፊያ #ኮንታ #ባህል #ጌጣጌጥ #ethiopianculture #kontazone #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የኮንታ ብሔር አዲስ ዓመት ህንግጫ
ከጳጉሜን 2 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል
#ethiopia | ከጳጉሜን መጨረሻ እስከ መስቀል በዓል ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቀው የኮንታ ብሔር የዘመን መለወጫ ህንግጫ በልምላሜና በተስፋ ታጅቦ ሊከበር ዝግጅት ተጠናቋል።
በኮንታዎች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ይህ ባህላዊ በዓል፣ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት በፍስሐ እና በደስታ የሚቀበሉበት የማንነት መገለጫ ነው።
የህንግጫ ትርጉም ያማረ፣ ያጌጠ እና የለመለመ ማለት ሲሆን፣ መስከረም ሲጠባና አደይ አበባ ምድሩን ሲሸፍነው የኮንታ ቀዬዎች ልዩ ውበት ይለብሳሉ።
በበዓሉ ወቅት ህብረተሰቡ አብሮነቱንና ፍቅሩን የሚያጠናክርበት፣ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ እንደሁም ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚመገብበት የወል መድረክ ይፈጠራል።
እንደ ባህሉ ሥርዓት ከቤት እስከ ደጃፍ ጽዳት ይከናወናል፤ የአዲሱ ዓመት ማብሰሪያ እሳት የሚለኮሰው ደግሞ በጳጉሜን መጨረሻ ላይ ነው።
ከ12 በላይ የሆኑ የኮንታ ባህላዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ይህ አውድ እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ በደማቅ ሁኔታ ይቆያል።
ፎቶዎቹንና መረጃውን ላካፈለን ኮንታ ቲዩብ ምስጋና እያቀረብን፤ እንኳን ለዘመን መለወጫው የህንግጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ሰላም ያድርግልን።
#ህንግጫ #የኮንታብሔር #ባህልእናቱፊት #አዲስዓመት #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
በኮንታ ዞን ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊነቱን የጠበቀ አዲስ የጫካ ቡና መገኘቱ ተበሰረ!
#fastmereja :-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘው ታሪካዊው ኮንታ ዞን፣ እስከ ዛሬ በሰው እጅ ያልተነካና ተፈጥሮአዊ ይዘቱን ሙሉ በሙሉ ጠብቆ የቆየ አዲስ የጫካ ቡና (Wild Forest Coffee) ተበሰረ።
ይህ በሰው እጅ ያልተተከለና «ያልተመነዘረ አረንጓዴ ወርቅ» የተባለው አዲስ የቡና ዘር የተገኘው፣ በኮንታ ዞን «ኦሽካ ዴንቻ» ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ በሚገኘው «አሜክ ኤጄቻ» በተሰኘ ልዩ ቦታ ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አካባቢው ሰውና የዱር እንስሳት በተስማማ ሁኔታ የሚኖሩበት በመሆኑ፣ የቡናው ተፈጥሯዊ መዓዛና ጣዕም እጅግ ልዩ እንደሆነ ተገልጿል።
ድርጅቱ አዲሱ የቡና ዘር መገኘቱ ለሀገራችን አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ጠቁሞ፤ እንደ ጅማ፣ ይርጋጨፌ እና ሐረር ሁሉ «Konta Coffee» በሚል ስም ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመቅረብ፣ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብሏል።
በተጨማሪም ያልተነካውን የኮንታ የተፈጥሮ ጫካ እና የቡና መገኛ ቦታዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የኢኮ-ቱሪዝም ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያነቃቃው ገልጿል።
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ አቀንቃኝና የባህል አምባሳደር አርቲስት ወንድወሰን አበበ (ወንዴ ኮንታ) በበኩሉ፣ “«ኑ ቡና ጠጡ» የሚለው ጥሪ የቡና መጠጣት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሰላም፣ የፍቅር፣ የጽኑ ጉርብትና እና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብር ማሳያ ነው” ሲል ተናግሯል።
አርቲስቱ አክሎም ይህንን ውድ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጠብቆ ላቆየው ማኅበረሰብ እውቅና መስጠትና ባህሉን ከኪነ-ጥበብ ጋር አዋህዶ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን አብራርቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ለዕይታ ያልበቁና በምስል ያልተቀረፁ የባህል ትውፊቶችን ቅርፃቸውን እንደጠበቁ ለዓለም መድረክ ለማብቃት ሰፊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።
ይህንን ታሪካዊ ግኝት አስመልክቶ «ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም» (Konta Coffee) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱን የጫካ ቡና ይፋ ለማድረግ "ኑ ቡና ጠጡ" የተሰኘ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና የመርሃ ግብር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
በዚሁ መሠረት ቶካ ፊልም መንደር ከ«ኪን-ኢትዮጵያ የባህል ቡድን» እና ከ«ቤራ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንትስ» ጋር የጋራ የሥራ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ በቅርቡም በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

"ኑ ቡና ጠጡ" ተብላቹኋል
* በኮንታ ዞን አዲስ የተፈጥሮ የጫካ ቡና መገኘቱን ይፋ ተደረገ
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በታሪካዊው ኮንታ ዞን እስከ ዛሬ በሰው እጅ ያልተነካና ተፈጥሮአዊነቱን ፍጹም ጠብቆ የቆየ አዲስ የተፈጥሮ ጫካ ቡና መገኘቱ ተበሰረ።
በኮንታ ዞን ጥቁርና ጥቅጥቅ ባለው «አሜክ ኤጄቻ» ጫካ ውስጥ የተገኘው የቡና ዘር የሀገራችንን የቡና ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚያስጀምር መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ታሪካዊ ግኝት አስመልክቶ «ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም» (Konta Coffee) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱን የጫካ ቡና ይፋ ለማድረግ "ኑ ቡና ጠጡ" የተሰኘ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና የመርሃ ግብር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
ድርጅቱ አዲሱ የቡና ዘር መገኘቱ ለሀገራችን አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ገልጿል።
እንደ ጅማ ይርጋጨፌ እና ሐረር ሁሉ «Konta Coffee» በሚል ስም ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመቅረብ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።
ያልተነካውን የኮንታ የተፈጥሮ ጫካ እና የቡና መገኛ ቦታዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የዘርፉን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃዋል ብሏል።
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ አቀንቃኝና የባህል አምባሳደር አርቲስት ወንዴ ኮንታ እንዳለው "ኑ ቡና ጠጡ" የሚለው ጥሪ የቡና መጠጣት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሰላም የፍቅር የጽኑ ጉርብትና እና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብር ማሳያ ነው ።
ይህንን ውድ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጠብቆ ላቆየው ማኅበረሰብ እውቅና መስጠትና ባህሉን ከኪነ ጥበብ ጋር አዋህዶ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው" ሲል ተናግሯል ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለዕይታ ያልበቁ የባህል ትውፊቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን እና ከቤራ ኢንተርቴይንመንት ጋር የጋራ የሥራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #discoverethiopia #kontacoffee #nubunatetu #ethiopiancoffee #wendekonta

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ዓይኖቹን ወደ ማስታወቂያ ሰሌዳነት የለወጠው ጉደኛ አትሌት
#ethiopia | በ1996ቱ የአትላንታ ኦሊምፒክ ወቅት አዘጋጆቹ የፑማ ኩባንያን የንግድ ምልክት ከስፖርት መድረኩ ለማራቅ ጥረት አድርገው ነበር።
ነገር ግን እንግሊዛዊው የሩጫ ሻምፒዮን ሊንፎርድ ክሪስቲ የኦሊምፒክ ባለስልጣናትን ያስደነገጠ ሌላ ዕቅድ ይዞ ቀረበ። የወንዶች የ100 ሜትር ውድድር ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ክሪስቲ ጥቁር መነፅር አድርጎ የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኘ።
አትሌቱ ጥቁር መነፅሩን ሲያወልቅ በቦታው የነበሩ ጋዜጠኞችና ፎቶግራፈሮች ያልተጠበቀ ነገር ገጠማቸው።
ከዓይኖቹ ላይ ያደረጋቸው ደማቅ ሰማያዊ ኮንታክት ሌንሶች የፑማን ታዋቂ የዘላይ ድመት አርማ ይዘው ነበር። የፎቶግራፈሮች ካሜራዎች ምስሉን ወዲያውኑ የቀረፁ ሲሆን የክሪስቲ የንግድ አርማ ያረፈባቸው ዓይኖች ምስል በዓለም ዙሪያ በፍጥነት ተሰራጩት።
ምንም እንኳን የኦሊምፒክ ባለስልጣናት አትሌቱ በውድድሩ ወቅት ሌንሶቹን እንዳያደርግ በኋላ ላይ ቢከለክሉም ኩባንያው የሚፈልገውን ዓላማ አስቀድሞ አሳካ።
ክሪስቲም ቢልቦርድ፣ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ወይም በትራክ ልብሱ ላይ የሰፈረ አርማ ሳይያስፈልገው የራሱን ዓይኖች ወደ ማስታወቂያ ሰሌዳነት በመለወጥ በስፖርቱ ታሪክ ከታዩት ድብቅ ማስታወቂያ ስልቶች አንዱን ፈጽሟል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago
በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ ልጃቸውን የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በኮንታ ልዩ ወረዳ የግንባ አጋሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ፣ በፈጸማቸው ሶስት ከባድ ወንጀሎች በሞት እንዲቀጣ የኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።
ተከሳሹ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከገበያ ስትመለስ የነበረችውን የ15 ዓመት ታዳጊ ጠልፎ ወደ ጫካ በመውሰድ ሊደፍራት ሲታገል፣ የልጇን ጩኸት ሰምታ የደረሰችውን እናት ወይዘሮ አይናቴ ኬቶን በጩቤ ወግቶ በመግደል ገደል ውስጥ ወርውሯታል።
ተከሳሹ እናትን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ካደባየ በኋላ የጠለፋትን ታዳጊ ልጅ አስገድዶ መድፈሩን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እና የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት፣ ተከሳሹ በፈጸማቸው በጭካኔ የመግደል፣ በታዳጊ ልጅ ጠለፋ እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ጥፋተኛ በማለቱ የሞት ቅጣት እንዲወሰንበት አድርጓል።
Seledadotio

እንግዲህ ሀምሌ ገብቶአል አመታዊ ሂሳብ ማስራት የምትፈልጉ ድርጅቶች:ነጋዴዎች እንዲሁም ከግብር ጋር የተያያዙ የተለያየ ጉዳዮች ያላችሁ ግብር ከፋዮች ኮንታክት አድርጉኝ 🥰🫶🏻
4 months ago
❓🔐 ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ፣ የፋይሎች ደኅንነት ያሳስብዎታል?
ውድ ፋይሎችዎ፣ ፎቶዎችና ኮንታክቶች እንዳይጠፉ አዲሱን የ 'File Recovery' አገልግሎት ይጠቀሙ፤ ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ በዘላቂነት ያስቀምጥልዎታል።
✅ ለመመዝገብ ለዕለታዊ (15GB) A ፣ ለሳምንታዊ (110GB) B ፣ ለወርኃዊ (ያልተገደበ ስቶሬጅ) C ብለው ወደ 6791 ይላኩ!
👉 ለዕለታዊ 3 ብር፣ ለሳምንታዊ 18 ብር፣ ለወርኃዊ 300 ይከፍላሉ፡፡
🛑 አገልግሎቱን ለማቋረጥ STOP A፣ B፣ C ብለው ወደ 6791 ይላኩ።
#filerecovery #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

5 months ago
ሰውዬው "አትርሱኝ" የሚለውን ቃል እንደ እናቱ ምርቃት ሳይሆን እንደ ታክስ መክፈያ ደረሰኝ ነው የሚያየው። አንዳንዱ "አትርሱኝ" ባይ ደግሞ "አትርሱኝ" የሚለውን ቃል ሲጠቀም፣ ቃልኪዳን እየገባ ሳይሆን "ሪከርድ" እያደረገ ነው የሚመስለው።
ለካስ ሳናውቀው "አትርሱኝ" ማለት ያለ እረፍት እኔን በማሰብ ተሰቃዩ ማለት ሆኗል!
ይህ ሰውዬ አገር ሰላም ሆኖ፣ ፀሐይ ወጥቶ ሲገባም ጭምር "አትርሱኝ" ይላል። ቆይ ምን ያህል ቢረሳ ነው? ወይስ ረሺው ብዙ ነው? እኔ የምለው... ሰውዬው "የረሳኝ" ብሎ የሚጠረጥራቸው ሰዎች ብዛት፣ በምርጫ ወቅት "ያልመረጠኝ" ብሎ ከሚቆጥር ፖለቲከኛ ይበልጣል።
ለሠርግ ተጠርቶ "እንኳን ደስ አላችሁ" ከማለት ይልቅ "አትርሱኝ" ይላል። ሙሽሮቹ በጫጉላ ሰዓት እንኳ የእርሱን ፊት እያሰቡ "እንዴት ይረሳል?" እያሉ እንዲጨነቁ ይፈልጋል። ደግሞ እኮ የሚረሳ ነገር ቢኖረው አይቆጭም። ሰውዬው እንደ ድሮ ስልክ "ኮንታክት" በቃሉ የያዘው ቁጥር የለም፤ ግን "አትርሱኝ" ማለቱን አይረሳም።
አንድ ቀን እንዲያውም እንዲህ ሆነ... ሞት መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ፣ ሰውዬው መርዶውን ከመቀበሉ በፊት "እሺ መሞቴንስ እሞታለሁ፤ ግን በኋላ ስትመለስ እንዳትረሳኝ" ብሎታል ይባላል። መቃብሩ ላይ "አትርሱኝ" የሚል ፅሁፍ ካልተፃፈማ፣ ትንሳኤ ቀን መጥቶ "አልተፃፈም" ብሎ "ሪፖርት" እንደሚያደርግ አልጠራጠርም።
እሱ "አትርሱኝ" የሚለው ቃል ለእርሱ የህይወት "ሴፍቲ ቤልት" ናት። አየር በነፃ እንደምናገኘው ሁሉ እርሱም ትዝታን በነፃ ማግኘት ይፈልጋል። ግን የሚገርመው ነገር፣ እርሱን ለማስታወስ ስትሞክር የምታስታውሰው ብቸኛ ነገር እርሱ "አትርሱኝ" ማለቱን ብቻ ነው።
ወዳጄ... የዚህን ሰውዬ ስም ከረሳኸው አይከፋም፤ "አትርሱኝ" ማለቱን ከረሳህ ግን እራሱ መጥቶ "ለምን ረሳኸኝ?" ብሎ ትዝታህን "አፕዴት" ያደርገዋል። እንዲያውም እኮ "አትርሱኝ" ማለት የአማርኛ ቋንቋ "ቫይረስ" ሆኗል። አንድን ነገር ለመናገር መግቢያህ "አትርሱኝ" ከሆነ፣ ንግግሩ ሳይጀምር ሰልችቶሃል ማለት ነው።
በእውነት ለመናገር... ሰውዬው ከሞተ በኋላ እንኳ በመንፈስ መጥቶ የቁም ጓደኞቹን "ቅምጥል ትዝታ" እያሳከከ "እንዴ... የዛሬ አምስት ዓመት እንዲህ ብዬህ አልነበር? እንዴት ረሳኸኝ?" ሳይላቸው አይቀርም።
እኔ የምለው... ሐኪም ቤት ሄዶ "ዶክተር... መታመሜን እንዳትረሳው" ቢል ሐኪሙ መድኃኒት ይፅፍለታል ወይስ "የመርሳት በሽታ" ያለበት እራሱ ሐኪሙ እንደሆነ ይቆጥራል?
ለማንኛውም... ይህንን ወግ አንብባችሁ ስትጨርሱ "አትርሱኝ" እንዳትሉኝ። ምክንያቱም እኔ "ረሱኝ" ብዬ ኮርጃለሁ!
አበጀ በለው የላኩልን

6 months ago
ኮንታ : ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል
#ethiopia | በዓሉ በኮንታ ዞን አመያ ደብረ ኤፍራታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እና በጪዳ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ስቅለት በማሰብ በጸሎት፣ በስግደት እንዲሁም የሕመማት ሳምንትን በሚዘክሩ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርኃ ግብሮች ነው እየተከበረ የሚገኘው።
በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፤ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል።
የ#ኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

8 months ago
ኢዜማ በአባላቱ ላይ የሚፈጸመው “ህገ-ወጥ እስር እና እንግልት” በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በመጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና በጸጥታ አካላት በአባላቱ ላይ የሚፈጸመው እስር፣ ወከባና እንግልት ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንዳይሆን እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን አስታወቀ።
ፓርቲው በዝርዝር ባቀረበው ሪፖርት መሠረት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአመራርና የዕጩ አባላቱ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር እየተዳረጉ መሆኑን ጠቁሟል።
ዋና ዋና ተጠቃሽ የበደል ሪፖርቶች
* በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ኮንታ ዞን): የአባላት መብት ተጥሶ ለበርካታ ቀናት ያለ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ታስረው መቆየታቸውና የተወሰኑት ደግሞ ዋስትና ተከልክለው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ መደረጉ።
* በደቡብ ኢትዮጵያ (ጋሞ ዞን እና ኩቻ): አባላት ለወራት ታስረው ቢቆዩም፣ የፍርድ ቤት የነፃ መውጫ ትዕዛዝ ቢሰጥም በአካባቢው አመራሮች ፍቃደኝነት ሳይተገበር መቅረቱ።
* በካፋ ዞን (ጨና ወረዳ): የምርጫ ዕጩዎች እና የዞን አስተባባሪዎች በጥር 2018 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው እስካሁን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸው።
* በአፋር ክልል: የፓርቲው የዞን አስተባባሪዎች ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ መታሰራቸውና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው መከልከሉ ተገልጿል።
ኢዜማ እነዚህ እርምጃዎች ሆን ተብለው የፓርቲውን እንቅስቃሴ ለማዳከም አባላቱን በገንዘብና በስነ-ልቦና ለመጉዳት እንዲሁም ህዝቡን ለማስፈራራት የሚደረጉ “ህገ-ወጥ ተግባራት” ናቸው ብሏል።
ገዢው ፓርቲ በቃል የሚናገረው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና በተግባር የሚፈጽመው የአባላቶቻችን እስር ፍጹም ተቃራኒ ነው ያለው መግለጫው የታሰሩት አባላቱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
በመጨረሻም ፓርቲው መንግስትና የሚመለከታቸው የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው ማስተካከያ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

9 months ago
በኮንታ ዞን አንድ በጥበቃ በጎሽ ተወግቶ ህይወቱ ማለፉ ተነገረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው በኮንታ ዞን ኮይሻ 02 ቀበሌ ልዩ ሰፍራ ሀማካ ቡልኣ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ታህሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 አከባቢ አንድ በጥበቃ ላይ የነበረ ግለሰብ በጎሽ ተወግቶ ህይወቱ አልፏል፡፡
ህይወቱ ያለፈው የግል ድርጅት ጥበቃ እና ሌሎቹ ሦስት ግለሰቦች በጋራ የሰቀሉትን የማር ቀፎ ለመቁረጥ ወደ ወደቀፎ ቦታ እየሄዱ ባሉበት ሰዓት ከሌላ አከባቢ በባህላዊ ወጥመድ የተያዘ ጎሽ ወጥመዱን በመቁረጥ ግለሰቦቹን ለማጥቃት ሲል ሶስቱ ሮጠው ሲያመልጡ አንደኛ ተጎጂዉ ማምለጥ ባለመቻሉ ጎሹ በቀንዱ በመዉጋት እና በእግሩ በመርገጥ ጉዳት ሲያደርስበት ሮጠዉ ያመለጡ ሶስቱ ግለሰቦች ለአከባቢዉ ህብረተሰብ አስተባብረዉ ከጎሹ አስጥለዉ ወደህክምና ቢወስዱትም የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ መንገድ ላይ ህይወቱ ማለፋን ተገልፆል፡፡

10 months ago
የሾኬላ ዋሻና ፏፏቴ - ድብቁ የቱሪዝም ሀብት
#ethiopia | የሾከላ ዋሻና ፏፏቴ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በኮንታ ዞን፣ አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓ ላሼ ቀበሌ ውስጥ ነው።
የዋሻው አጠቃላይ ይዘት እና ስፋት በዞኑ ውስጥ ካሉት ሌሎች ዋሻዎች ቀዳሚውን ደረጃ የሚይዝ እንደኾነም ነው የሚገለጸው።
ሾከላ የሚለውን የዋሻው ስያሜ የተገኘው፥ ከዋሻው አናት ላይ በግምት ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ወደታች የሚወረወረው ሾኬላ በተባለው ፏፏቴ ስም እንደተሰየመም ከዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዋሻው ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከአንዱ ዋሻ ወደ ሌላኛው ዋሻ ለመድረስ 100 ሜትር ርቀት አለው፡፡ የመጀመሪያው ዋሻ ሦስት ትላልቅና ስድስት ትናንሽ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ የዋሻው ስፋት በግምት 300 ካሬሜትር ስፋት ያለው ሲሆን የመግቢያ በር ከፍታው ደግሞ ሦስት ሜትር ያህል ነው፡፡
የዋሻው ሁለተኛ ክፍል የመኖሪያ ቤት 2 ሣሎን እንደሚባለው ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ክፍሉ በግምት 15x20 ሜትር የሚያክል ስፋት ሲሆን ክፍሉ ከሌላው ክፍል ጋር ተጠርቦ የተሰራ በሚመስል የድንጋይ ግድግዳ የተከለለ ነው፡፡
የዋሻው ሦስተኛው ክፍል ሰፋ ያለ ሲሆን በውስጡ የተለያዬ ቅርጽ ያላቸው ድንጋዮች እንዲሁም ከዋሻው ጣሪያ ያለማቋረጥ በሚንጠባጠበው ውሃ ጠብታ ከሚመስል ፈሳሽ የተሰሩ ውበት ያላቸው ጌጣጌጦች የተሞላ ነው።
በዋሻው ቀኝ በኩል ከላይ ቁልቁል ከ50 ሜትር እየተመዝገዘገ የሚወርደው የሾኬላ ፏፏቴ ለዋሻው ልዩ ግርማ ሞገስን ያጎናፈ ሲሆን በዋሻው ግራ በኩል ስድስት ትናንሽ ክፍሎችም ይገኙበታል።
የኮንታ ዞን በርካታ ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ያሉት ሲሆን ከስድስት ዓመታት በፊት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በዞኑ በነበራቸው ጉብኝት "ኮንታ ፈጣሪ ሳይሰስት የእጁን ጥበብ የገለጸበት አከባቢ ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
የሾኬላ ዋሻና ፏፏቴ ከዞኑ አመያ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ድንቅ የተፈጠረው ውብት ሲኾን ከዋሻውና ፏፏቴ በተጨማሪ በዙሪያ ገባው የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች፣ ነፋሻ አየር እና የአከባቢው ልዩ መልዐካ-ምድራዊ አቀማመጥ አይንን የሚማርክ ነው።
የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

ታላቁ ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ስላሴ በሰይፉ ሾው ፦
በዘሪሁን ተዝናኑ
★ የዛሬ 10 ዓመት ነው እንደድንገት አይኔ ብዥ ያለብኝ።
★በነገራችን ላይ ዕድሜዬ 70 ሞልቷል።
★ ከሐረር አንድ አይነስውር ደውሎ እንኳን ወደእኛ ክለብ መጣህ ያለኝ አለ።
★ ህይወት ለማንኛችንም ዋስትና አልገባችም።
በአደጋም ሆነ በጤና ማጣት ጠግቦ በመሰበርም ከነሙሉ
አካላችን ላንቀበር እንችላለን።
★ ሙሉ ነገር የነበረን ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች የአካል
ጉዳት ሊያጋጥመን ይችላል።
★ ሰይፍሻ አንተም ፀጉር ጎሎሃል ስለዚህ አካል ጉዳተኛ ነህ።
★ የኔ በሽታ ግላኮማ ነው። ግላኮማ ዓይንን የማጥቃት ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ከስኳር በሽታ ጋር ተያያዥነት ያለው ነው።
★ የዓይን ብርሃን ማጣት የምታውቀውን ሰውና ከተማ ታጣበታለህ።
★ ሀገሬን ከናቅፋ እስከ ሞያሌ ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፣
ከምስራቅ እስከምዕራብ ያላየሁት ሀገር የለም።
★ ንባብ ማለት ከዓይን ጋር ኮንታክት መፍጠር ማለት ነው።
★ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ጓደኛዬ ልጁን ድሮ በዓይኔ
ማየት ባለመቻሌ አልቅሻለሁ።
★ ልጆቼ ሲያገቡም ቬሎዋቸውን አላየሁም። ደስታቸውን
በዓይኔ አላየሁም። ሁለቱንም ሴት ልጆቼን በአንድ ቀን ነው
የዳርኳቸው።
★ አንደኛዋ ልጄ ስትወልድ ልጇን መልኩን አላየሁትም።
በዳበሳ ብቻ ነው። ግን እንዳየሁት ነው የምቆጥረው።
★ መጋቢት 17/2017 70ኛ ዓመቴን አስመልክቶ ተስፋ ኢንተርፕራይዝ ከልጆቼ ጋር አከበረልኝ።
★ ከዩኒቨርሲቲ እንደወጣሁ ፦ ጠልፎ በኪሴ ፣ የቬኑሱ ነጋዴ እና ንጉስ ሊርን ከደበበ እሸቱ ጋር ተውኛለሁ።
★ ከኔ ሲኒየሮች ጌትነት እንየውንና ተፈሪ አለሙን አደንቃለሁ።
እነሱ እያሉ ለምን እኔ እሸለማለሁ እላለሁ። ራሱን የሚደብቀውም አስታጥቃቸው ይሁንም እንደዛው።
★ተዋናይ ግርማ መኮንን መስከረም 7/1983 የሞተ የኛ ታላቅ መምህር ነው። ኮሜዲ ብትለው ፣ ትራጄዲ ብትለው ፣
ፋርስ ብትለው የማይችለው አይነት የትወና ስታይል የለም።
የሚተካው ሰው የለም። እኔ ነኝ ምርጥ ተዋናይ የሚለውን ሁሉ የሚያስንቅ ነበር። ይኼ ሰው በአጭር ተቀጨ።
ዕድለኛ ሆኜ አብሬው የመስራት ዕድሉን አግኝቻለሁ።
★ ከዩኒቨርሲቲ ወጥቼ ቴአትር መስራት ከጀመርኩኝ
42 ዓመት ሆኖኛል።
★ የአይነ ስውር ገፀ - ባህሪ ፈጥሮ ሊያጫውተኝ የሞከረ የለም።
★ ዳና ድራማ ላይ አይኔ እየደከመ እያነበቡልኝ አክት አድርጊያለሁ።
★ አደይ ድራማ ላይ ለአንድ ዓመት ከሁለት ወር ያህል
እየተነበበልኝ ተውኛለሁ።
★ ማንያዘዋል እንደሻው የተረጎመውን የመጨረሻው ፍርድ
የተሰኘውን ቴአትር እየተለማመድነው ነው። ታህሣሥ 9
ለዕይታ ይበቃል።
★ ጡረታ ወጥቼም ሀገር ፍቅር ከሠራተኛው እኩል ነው
የምገኘው።
★ ሰው በትዝታ ነው የሚኖረው። ወጣት ስትሆን ነው
በተስፋ የምትኖረው።
★ ፊልማችን በተለያየ ቋንቋ ቢሰራ ከዓለም ጋር የተሻለ
እንተዋወቃለን።
★ በ14 ዓመቴ ነው ሲጋራ ማጨስ የጀመርኩት። ልጆቼ ግን በአካል ሳጨስ አይተውኝ አያውቁም። ሲበቃኝ ግን በቃኝ።
አንድ ፓኬት መቶ ብር ሲገባ አቆምኩኝ። በቀን አንድ ፓኬት
ከግማሽ ነበር የማጨሰው።
አንድ ትልቅ ቪላ ቤት የሚገዛ ብር በዓመት በሲጋራ አጠፋ ነበር። እኛ እንደምናደርገው በዚህ ዘመን ወጣት በአደባባይ ሲያጨስ አላየሁም።
★ የዛሬ ወር ብሬል ተምሬ የመጀመሪያውን ሰርተፍኬት
ወስጃለሁ።
★ በህይወቴ የማልረሳው የመድረክ ገጠመኝ ፦
ጊዜው 1977 ዓ.ም እኔ ተፈሪ እና ደበበ መድረክ እየመራን
በላይነሽ ውባንተ የተሰኘች ዘፋኝ ፦
ምን አስገለበጠኝ ወተቱን በጋን
ችዬ እገፋዋለሁ የማልለውን
የማልለውን የሚለውን ሳትጨርስ መድረክ ላይ ወደቀች።
ወደ ሆስፒታልም ተወሰደች።
የተሾመ አሰግድን ስንብት ዘፈን
ይህች አጋጣሚ በአንድ አገናኝታን
የፍቅርን ሸማ ደርባ አጎናፅፋን
ሆኖም ሳናስበው ጊዜው በመሆኑ
በቃ ተለያየን መሪር ነው ሀዘኑ
በኋላ ስንሰማ ሆስፒታል የሄደችው ዘፋኟ ሞተች ተባለ።
በነጋታው ለቀብር ያ ሁሉ ተመልካች ተገልብጦ መጣ።
ከዛ በኋላ ስንብት የተሰኘውን ዘፈን ስሰማ ዘፋኟ ከአዕምሮዬ አትጠፋም።
በመጨረሻም ፦ ልበ - ብርዓኖቹ ታዳጊዎቹ አይነስውሮቹ እህትማማቾች ፦ ሄራንና ሶልያና ለአርቲስት ኪሮስ ኃ/ስላሴ
በብሬል የተፃፈ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አበርክተውለታል።
እግዚአብሔር መድሃኒቴ ነው
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው
>
ኪሮስ እንወድሃለን ! እናከብርሃለን !
ዕድሜ ከጤና ይስጥልን !
" ሄራንና ሶልያና " ❤❤❤❤❤
" እግዚአብሔር ለትልቅ ደረጃ ያብቃችሁ። "
>
አርቲስት ኪሮስ ኃ/ስላሴ ፦ ለሰጠኸን የኪነጥበብ ስራዎችና
ወደፊትም ለምትሰጠን ጥበባዊ ስራዎች እናመሰግናለን።
ፈጣሪ ዕድሜና ጤና ይስጥህ !
አክባሪህና አድናቂህ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

ቴሌግራም አካውንታችሁን ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level
1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode
2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።
3. ከ2 በላይ device ላይ login አታድርጉ።
Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate sessions እያደረጋችሁ ቀንሷቸው።
4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።
5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።
6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።
7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው 1ዴ ካየው በኋላ የሚጠፋ) ሚሴጆችን ላኩ።
8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።
9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts
10. በተለያየ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አካውንታችሁ ላይ ሳትገቡ ብትቀሩ በራሱ Delete እንዳይሆንባችሁ self district የሚያደርግበትን ቀን አስርዝሙት።
ይህን ለማድረግ
Settings - privacy and security- delete my account - 24 months
seledadotio

12 months ago
በቱርክ አንድ ሰው ሚስቱን በስልክ ኮንታክቱ ላይ "ደልደል ያለች" ብሎ በመጻፉ የሞራል ካሳ ሊከፍል ነው
በቱርክ አንድ ባል የባለቤቱን ስልክ ቁጥር "ቶምቢክ"—በቱርክኛ "ደልደል ያለች" በሚል ስም አስቀምጦ ነበር።
ሴትየዋ እንዲህ ያለው ስም ክብሯን እንዳዋረደባትና ትዳሯን እንዳፈረሰባት ተሰምቷታል።
ፍርድ ቤቱ ሰውየውን "ጥፋተኛ" አድርጎታል—አሁን ለቀድሞ ባለቤቱ የሞራል ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበታል።

1 year ago
በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታ አስነሳ
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግንባር ቀደም የግል ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተደረገው ከፍተኛ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ፣ በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን አስነሳ። ዩኒቨርሲቲው በአንድ ሴሚስተር እስከ እጥፍ የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ፣ ተማሪዎች ክፍያው አስቀድሞና በበቂ ሁኔታ እንዳልተገለጸላቸው ገልጸዋል።
ተማሪዎች እንዳስታወቁት፣ ለአብነትም አናንያ የተባለው ተማሪ የአንድ ሴሚስተር ክፍያው ወደ 30 ሺህ ብር ያሻቀበ ሲሆን፣ ሜሮን ደግሞ የ"ፐር ኮንታክት ሀወር" ክፍያ ወደ 898 ብር መጨመሩን ተናግራለች። አዲሱ የክፍያ ማዘዣ የተሰጣቸው ክፍያ ለመፈጸም ወደ ገንዘብ ቤት በሄዱበት ወቅት መሆኑንም ተማሪዎቹ ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ባለቤትና ፕሬዝደንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው የተደረገው ጭማሪ አግባብነት ያለውና ፍትሃዊ መሆኑን ገልጸዋል። ለጭማሪው ምክንያት የሆነው የዩኒቨርሲቲው ወጪ ከፍተኛ መጨመር እና ከመንግስት የተጣሉ አዳዲስ የመሰረተ ልማት ግዴታዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ድረገፅ ላይ ማሳወቃቸውንም ገልጸዋል።

የህዝብ ክብረ በዓላትን ለማስተዋወቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በኢትዮጵያ የሚከበሩ የህዝብ ክብረ በዓላትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስቴር ዴኤታዋ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ለዘመናት የዳበሩ እና በትውልድ ቅብብሎሽ የጎለበቱ እምቅ የባህል ሀብቶች ባለቤት ነች። እነዚህን ሀብቶች በመጠቀም ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና ባህል ለማህበረ-ኢኮኖሚ እድገት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ሚኒስቴሩ በፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሰፊ ስራ እየሰራ ነው።
በመግለጫቸው፣ በመጪዎቹ ሶስት ወራት የተለያዩ የህዝብ በዓላት እንዲከበሩ የባህል ንቅናቄ መጀመሩን አስታውቀዋል። ይህ ንቅናቄ ከፌደራል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በቅንጅት የሚከናወን ሲሆን፣ የህዝብ ተሳትፎን በማሳደግ የጋራ እሴቶችን ለማጎልበት ያለመ ነው።
በ2018 በጀት ዓመት የአዲስ ዓመት አቀባበል እና የጳጉሜ ቀናት በኪነ-ጥበብ ስራዎችና የተጎዱ ዜጎችን በመርዳት የመተሳሰብ እና የአብሮነት ባህላችንን በማጎልበት መከበራቸውን ወ/ሮ ነፊሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ ክልሎች የተከበሩ የባህል በዓላትን በመጥቀስ፣ በትግራይ አሸንዳ፣ በአማራ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ለቀማና ቡሄ፣ በኦሮሚያ ጎቤ እና ሽኖዬ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉዋንዳ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የዳውሮ ቶኢ-ቤኣ እና የኮንታ እንግጫ ክብረ በዓላት በደመቀ ሁኔታ መከበራቸውን አብራርተዋል።
በመስከረም ወር የሚከበሩ በዓላትን በተመለከተም መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ኢትዮጵያ የጊፋታ፣ የዮ መስቀላ እና የጋዜ መስቀላ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የማሳላ፣ ያሆደ፣ መስቀል እና ሄቦ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማሽቃሮ ባሮ፣ በኦሮሚያ ኢሬቻ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጋሪ ዎሮ ክብረ በዓላት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
በመጨረሻም፣ እነዚህ በዓላት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክሩ በመሆናቸው፣ ህዝብና መንግስት በጋራ ተቀናጅተው የተሳካ በዓል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም፣ ሚዲያዎች እነዚህን በዓላት በአገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ አገራዊ ገፅታን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አሳስበዋል።

በኮንታ እና በካፋ ዞን ከባድ ዝናብ ያስከተለው መሬት መንሸራተት የ10 ሰው ህይወት ነጠቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ምሽቱን በጣለው ከባድ ዝናብ የ 6 ሰዎች እንዲሁም በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ 4 የአንድ ቤተሰብ አባላት በድምሩ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ምሽቱን በጣለው ከባድ ዝናብ የ 6 ሰዎች እንዲሁም በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ 4 የአንድ ቤተሰብ አባላት በድምሩ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
Sponsored by
Surafel
1 year ago
የደረሰ የመሬት ናዳ የለም!
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሽቱን የደረሰ የመሬት ናዳ አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።
በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ሀሰተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠነቀቅ ጥሪ ቀርባል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ መረጃን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ዛሬ ማለዳ በክልሉ በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ እና በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ የሰዎች ህይወት አልፏል ሲል ያሰራጨዉ መረጃ ሀሰተኛና ኃላፊነት የጎደለዉ መሆኑን ተናግረዋል።

የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል‼
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ምሽቱን በጣለው ከባድ ዝናብ የ 6 ሰዎች እንዲሁም በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ 4 የአንድ ቤተሰብ አባላት በድምሩ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል

ቦንጋን ከታርጫ የሚያገናኘው መንገድ በመሬት መንሸራተት ተቆርጧል
#ethiopia | ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት ከቦንጋ ወደ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች የሚወስደው መንገድ መቆረጡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
የመንገድ መቆረጡ የተከሰተው በካፋ ዞን፣ ጠሎ ወረዳ፣ ሜገራ ቀበሌ በተለምዶ ቦቆ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
3 ቀናት ላስቆጠረው ችግር እልባት ለመስጠት የጠሎ ወረዳ አስተዳደርን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
የዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች ነዋሪዎች ከጂማ ታርጫ የሚያስኬደውን አማራጭ መንገድ እየተጠቀሙ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ አካባቢው ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከቦንጋ ወደ ኮንታና ዳውሮ ዞኖች የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ተቋረጠ
#ethiopia | በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ሜገራ ቀበሌ በተለምዶ ቦቆ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ነው መንገዱ የተጎዳው ተብሏል።
በዚህ ምክንያት ቦንጋ፣ ኮንታና ዳውሮ ዞኖችን የሚያገናኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል ።
የጠሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትርሴ ሻታቸዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ችግሩን በፍጥነት በመቅረፍ የትራንስፖርት አገልግሎቱን እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን

Comments