Logo
Getu Temesgen
ከቦንጋ ወደ ኮንታና ዳውሮ ዞኖች የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ተቋረጠ
#ethiopia | በካፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ሜገራ ቀበሌ በተለምዶ ቦቆ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ነው መንገዱ የተጎዳው ተብሏል።

በዚህ ምክንያት ቦንጋ፣ ኮንታና ዳውሮ ዞኖችን የሚያገናኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል ።

የጠሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትርሴ ሻታቸዉ የሚመለከታቸዉ አካላት ችግሩን በፍጥነት በመቅረፍ የትራንስፖርት አገልግሎቱን እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.