በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ ልጃቸውን የደፈረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በኮንታ ልዩ ወረዳ የግንባ አጋሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ፣ በፈጸማቸው ሶስት ከባድ ወንጀሎች በሞት እንዲቀጣ የኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።
ተከሳሹ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከገበያ ስትመለስ የነበረችውን የ15 ዓመት ታዳጊ ጠልፎ ወደ ጫካ በመውሰድ ሊደፍራት ሲታገል፣ የልጇን ጩኸት ሰምታ የደረሰችውን እናት ወይዘሮ አይናቴ ኬቶን በጩቤ ወግቶ በመግደል ገደል ውስጥ ወርውሯታል።
ተከሳሹ እናትን በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ካደባየ በኋላ የጠለፋትን ታዳጊ ልጅ አስገድዶ መድፈሩን የፖሊስ የምርመራ ውጤት እና የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት፣ ተከሳሹ በፈጸማቸው በጭካኔ የመግደል፣ በታዳጊ ልጅ ጠለፋ እና በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ጥፋተኛ በማለቱ የሞት ቅጣት እንዲወሰንበት አድርጓል።
Seledadotio

16 days ago