ቦንጋን ከታርጫ የሚያገናኘው መንገድ በመሬት መንሸራተት ተቆርጧል
#ethiopia | ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት ከቦንጋ ወደ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች የሚወስደው መንገድ መቆረጡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
የመንገድ መቆረጡ የተከሰተው በካፋ ዞን፣ ጠሎ ወረዳ፣ ሜገራ ቀበሌ በተለምዶ ቦቆ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
3 ቀናት ላስቆጠረው ችግር እልባት ለመስጠት የጠሎ ወረዳ አስተዳደርን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሺዋስ ዓለሙ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
የዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች ነዋሪዎች ከጂማ ታርጫ የሚያስኬደውን አማራጭ መንገድ እየተጠቀሙ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ አካባቢው ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በመሆኑ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

1 year ago