25 days ago
ዩክሬን ድሮኔ መንገድ ስቶ ኢስቶኒያ በመግባቱ ይቅታ ጠይቃለሁ አለች
#ethiopia | የዩክሬን የጦር ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በስህተት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሶ መግባቱን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ያስታወቀ ሲሆን፥ ድሮኑም በኔቶ የፀረ-አየር መከላከያ መትቶ መጣሉ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄሮይሂ ትይኪ በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢስቶኒያን ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለት ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ነገር ግን ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ሩሲያን ተጠያቂ ያደረጉት ሚኒስትሩ፥ “ሞስኮ ሆን ብላ የድሮኑን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጋለች” ሲሉ ክስ ሰንዝረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ዩክሬን #ኢስቶኒያ #ኔቶ #ሩሲያ #የአየር_ክልል_ጥሰት #meduza #thiqaheth

4 months ago
የአፍሪካ መዲና በላብራቶሪ መነጽር፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የነዋሪውን እንግልት ይፈታዋል?
የከተማዋ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ከሀገሪቱ አንጋፋ የጥናት ተቋም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በ2018 በጀት ዓመት የሚጠናቀቁ ሁለት ግዙፍ ስልታዊ ጥናቶችን ለማካሄድ ተፈራርሟል።
ስምምነቱ "Building Urban Resilience" (የከተማ መቋቋም አቅምን መገንባት) እና "Counting Every Life" (ዲጂታል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ) በሚሉ መጠሪያዎች የቀረቡ ናቸው።
ነገር ግን ጥያቄው፦ ይህ ስምምነት የከተማዋን ነዋሪ ሕይወት በእርግጥ ይለውጠዋል ወይንስ ሌላ የቢሮክራሲ ሰነድ ሆኖ በመደርደሪያዎች ላይ ይከመራል? ይህ ዘገባ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን፣ የምሁራን የሰላ ትችቶችን እና የወደፊት ስጋቶችን በጥልቀት ይፈትሻል።
1. የአደጋ ስጋት መከላከል፡ ከ"እሳት አጥፊነት" ወደ "አደጋ መከላከል"
አዲስ አበባ በየዓመቱ በአማካይ ከሺ በላይ ድንገተኛ አደጋዎች (በተለይም የእሳት ቃጠሎ) ያስተናግዳል። እነዚህ አደጋዎች የሚከሰቱት ደግሞ በአብዛኛው መሠረተ ልማት ባልተሟላላቸው፣ የቤት አሰራራቸው ለቃጠሎ በሚያመቹ እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታቸው ባልተስተካከለ ሰፈሮች ነው።
🌍 የዓለም ተሞክሮ፦ የቶኪዮ እና የሜክሲኮ ሲቲ ትምህርት
እንደ ቶኪዮ ያሉ ከተሞች አደጋ ከመከሰቱ በፊት "Micro-Zoning" የተባለ ስልት ይጠቀማሉ። ይህም እያንዳንዱ ወረዳ የራሱ የሆነ የአደጋ ስጋት ካርታ (Hazard Map) እንዲኖረው ያደርጋል። አዲስ አበባ አሁን የጀመረችው ጥናት ይህንን በወረዳ ደረጃ ያለውን ስጋት የመለየት ስራ የሚያከናውን ከሆነ፣ ግዙፍ እመርታ ነው። ነገር ግን እንደ ሜክሲኮ ሲቲ ሁሉ፣ ጥናቱ በወረቀት ላይ ብቻ ቢሰፍርና በቂ በጀት ካልተመደበለት፣ አደጋው ሲመጣ መከላከል አይቻልም።
🎓 የምሁራን እይታ፦
የከተማ ፕላን ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ አዲስ አበባ "Reactive" (አደጋ ሲመጣ የምትደነግጥ) ከተማ ነች። "ጥናቱ በወረዳ ደረጃ መውረዱ መልካም ነው፤ ነገር ግን ወረዳዎች አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ራሱን የቻለ ስልጣንና በጀት የላቸውም። ጥናቱ ይህንን መዋቅራዊ ለውጥ ካላመጣ፣ ሰነዱ ብቻውን ህንፃዎችን ከአደጋ አይታደግም" ይላሉ።
2. ዲጂታል ማንነት፡ የቢሮክራሲው ሞት ወይንስ አዲስ መልክ?
ሁለተኛው ጥናት "Counting Every Life, Securing Every Right" የሚል ሲሆን፣ ዓላማው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን (ልደት፣ ጋብቻ፣ ሞት) ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ ነው። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ አንድ ነዋሪ የልደት ምስክር ወረቀት ለማውጣት ቢያንስ ከ3-5 ቀናት እንግልትና በወረቀት የተሞላ ፋይል ይገጥመዋል።
🌍 የዓለም ተሞክሮ፦ የኢስቶኒያ ተአምር
ኢስቶኒያ 99% የመንግስት አገልግሎቶችን በዲጂታል ትሰጣለች። አንድ ዜጋ በህይወቱ ወረቀት የሚፈርመው ሲጋባ እና ቤት ሲገዛ ብቻ ነው። አዲስ አበባ ይህንን ልምድ ለመቅሰም የጀመረችው ጥናት፣ ዜጎች ከወረዳ ወረዳ መረጃ ፍለጋ እንዳይመላለሱ የሚያደርግ "Interoperable" (ተሳሳቢ) ዳታቤዝ መፍጠር ይኖርበታል።
ዲጂታላይዜሽን ማለት "የወረቀት ፎርምን ወደ ኮምፒውተር መተየብ" ማለት አይደለም። አሰራሩን (Process) መቀየር ማለት ነው። ምሁራን እንደሚጠቁሙት፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለው "የመረጃ ምስጢራዊነት አባዜ" እና የተቋማት መረጃን አለማጋራት (Data Silos) ለጥናቱ ትግበራ ትልቅ እንቅፋት ናቸው። በተጨማሪም፣ 80% የሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ የዲጂታል እውቀት (Digital Literacy) በሌለበት ሁኔታ፣ ሲስተሙ ለጥቂቶች ብቻ እንዳይሆን ያሰጋል።
3. የጥናት አባዜ እና የትግበራ ድርቅ (Implementation Gap)
ኢትዮጵያ ውስጥ በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥናቶች በከፍተኛ በጀት ይከናወናሉ። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ ጥናቶች "የፖለቲካ ፍጆታ" ተደርገው ይወሰዳሉ።
የዳታ ጥራት ስጋት፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን ሲያደርግ የሚጠቀመው መረጃ ከወረዳዎች የሚሰጠውን ነው። ወረዳዎች ደግሞ ሪፖርታቸውን "ለማሳመር" ሲሉ የተጋነነ ወይም የተሳሳተ መረጃ የመስጠት ዝንባሌ አላቸው። "Garbage in, Garbage out" እንደሚባለው፣ መነሻው የተሳሳተ ዳታ ከሆነ፣ የጥናቱ ውጤትም የተሳሳተ ይሆናል።
የሰው ኃይል ዝግጁነት፦ ዘመናዊ ሲስተም ቢገነባም፣ ያንን ሲስተም የሚረከበው የመንግስት ሰራተኛ በአሮጌው የቢሮክራሲ አስተሳሰብ የተተበተበ ከሆነ፣ ለውጥ ማምጣት አይቻልም። ቴክኖሎጂው ሳይሆን "አስተሳሰቡ" (Mindset) ይቀድማል።
4. የወደፊት ዕጣ-ፈንታ፦ ምን መደረግ አለበት?
ይህ ስምምነት ታሪካዊ ሊባል የሚችለው የሚከተሉት ነጥቦች ሲሟሉ ብቻ ነው፡
ግልጽነትና ተጠያቂነት፦ ጥናቱ በየደረጃው ያለውን ግስጋሴ ለህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት። በ2018 መጨረሻ ምን ተሳካ? ምን ቀረ? የሚለው በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል።
የግል ዘርፉ ተሳትፎ፦ መንግስትና ዩኒቨርሲቲ ብቻቸውን ከተማዋን ሊቀይሩ አይችሉም። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (Startups) በዲጂታላይዜሽን ሂደቱ ውስጥ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ መፈቀድ አለበት።
የዜጎች ዳታ ደህንነት፦ የነዋሪዎች የግል መረጃ (Privacy) በህግ መጠበቅ አለበት። መረጃው ለክትትል ሳይሆን ለአገልግሎት መሆኑን ህዝቡ ካላመነበት፣ ለዲጂታል ምዝገባው ያለው ትብብር ዝቅተኛ ይሆናል።
ማጠቃለያ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ለከተማዋ "የተስፋ ጭላንጭል" ነው። ነገር ግን ይህ ጭላንጭል ወደ ደማቅ ብርሃን የሚቀየረው በጥናቱ ውጤት ሳይሆን በጥናቱ ተፈጻሚነት ነው።
ከተማዋ በወረቀት ላይ ሳይሆን በመሬት ላይ፣ በሪፖርት ሳይሆን በነዋሪው እርካታ መመዘን አለባት። አዲስ አበባ በ2018 "ስማርት ሲቲ" (Smart City) ለመሆን የመጀመሪያውን እርምጃ ትረምዳለች ወይንስ በቢሮክራሲው አዙሪት ውስጥ ትቀጥላለች? መልሱ የሚገኘው ከጥናቱ መጠናቀቅ በኋላ በሚወሰዱት ደፋር የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ነው።

5 months ago
በዓለማችን ከፍተኛ የወንድ እጥረት የታየባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ ተደረገ
በዓለማችን ላይ ባለው የሥነ-ሕዝብ ስርጭት መሠረት በአንዳንድ ሀገራት በወንዶች እና በሴቶች ቁጥር መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ መሆኑን ጥናቶች አመለከቱ።
ይህ የወንድ እጥረት በግንባር ቀደምትነት የሚታይባት ላትቪያ በየ 100 ሴቶች 80 ወንዶች ብቻ የሚገኙባት ሀገር ስትሆን ምስራቅ አውሮፓዊቷ ሊቱዌኒያም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍተኛ የጾታ መዛባት ያለባት ሀገር ሆና ተመዝግባለች።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ በወንዶች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ቅናሽ የታየባት ሩሲያ በአሁኑ ሰዓት የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በ11 ሚሊዮን ገደማ ብልጫ ያለው ሲሆን ጎረቤቶቿ ዩክሬን፣ ኢስቶኒያ እና ቤላሩስም በተመሳሳይ የወንዶች ቁጥር እጥረት ከታየባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ ለዚህ አሀዛዊ ልዩነት ዋነኞቹ ምክንያቶች ወንዶች ለከባድ የጉልበት ስራ መጋለጣቸው፣ በጦርነት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆን እና ከሴቶች ጋር ሲነፃፀር ለጤናቸው የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆኑ ለሞት ምጣኔው መጨመር ምክንያት ሆኗል።
ይህ የሕዝብ ቁጥር መዛባት በእነዚህ ሀገራት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱ የሆነ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በጋብቻ እና በስራ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
seledadotio

8 months ago
ከፈለግን መላዉን አዉሮጳ እንዳልነበረ እናደርገዋለን ! /ፑቲን /
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮን ለማዳከም በአንድነት የተነሱትን አዲስ የ"አውሮፓ ጦር ሃይል"የተባለ ጥምር ጦር በማደራጀት ላይ የሚገኙትን ሀገራት በሩሲያ ላይ ትንኮሳ ለማድረግ ቢሞክሩ በታሪክ አይተዉት የማያዉቁት ምላሽ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ተነገረ ።
በሞስክ ላይ የኢኮኖሚ የፖለቲካዊ ቴክኖሎጂ ስርዓት የበላይነት ለመዉሰድና በጋራ ለመዝመት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ረቡዕ በዴንማርክ ዋና ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ዉሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ፑቲን "የሩሲያን ሰላማችን እና ለደህንነታችን ሃይላችን ከአደጋዎች ለመጠበቅ ሉዓላዊነታችን የተጋፋ እና መንግስታችን ላይ አደጋ የሚያደርስ አዝማሚያ ካየን ፈጣን ምላሽ እንደምንሰጥ ሊታወቅ ይገባል ስንልማ። ብለዋል
ይህንን ያሉትም ሀሙስ እለት በደቡባዊ ሪዞርት ከተማ በሶቺ ውስጥ በተካሄደው የውጭ ፖሊሲ መድረክ ላይ ነዉ ።
ፕሬዘዳንቱ የሰሞኑን ሩሲያን ለመክበብ ያለመ ዉሳኔያቸዉን እየተከታተሉ መሆኑን በመጥቀስ የምዕራባውያን ግብዝነት እና የክልላዊ የበላይነት ፍላጎት ሰላምን የሚያደፈርሱ አብሮ ለመኖር የማያስችሉ የከበባ ተግባር ሁኖ ሳለ ሞስኮን እንደግጭት ጠማቂ አድርጎ ለማሳየት መንደፋደፋቸዉ ብስጭት እንዳሳደረባቸው ገልጸው የአጸፋ እርምጃም ፈጣን እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።
ሁሉም የኔቶ አገሮች እኛን እየተዋጉን ነው, እና ከአሁን በኋላ አይደብቁትም" ለዩክሬን መረጃን በመስጠት እና የጦር መሳሪያዎችን በማቅረብ በውጊያ ስራዎች ውስጥ እየተሳተፉ " መሆኑን አረጋግጠዋል ።
ሩሲያን በፖላንድ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ወረራ እና በኢስቶኒያ ላይ የፈፀመችዉ የተዋጊ ጄቶች ጥቃት ጨምሮ ሩሲያ የክልሉን አየር ክልል በጅምላ እየጣሰች ነው ሲሉ የአውሮፓ ባለስልጣናት ያቀረቡትን ክስ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት የአውሮፓ ሀገራት ሩሲያ ላይ በሬ ወለደ የውሸት ወሬ በመፍጠር ከመቶ ዓመታት በፊት የፈለሰፉትን ታዋቂ የጠላትነት ገፅታ እንደገና ለመፍጠር እየሞከሩ ነዉ ብለዋል ።
አክለውም በዩክሬን ያለውን ጦርነት የማስቆም ሃላፊነት በአውሮፓ ሀገራት ላይ ነው ያሉት ፑቲን እንደ አለመታደል ሆኖ እስካሁን ድረስ ግጭቱን ማቆም አልቻልንም, የዚህም ምክንያት ስንቅና ትጥቅ የሚያቀርቡ ዩክሬንን በርቺ በርቺ የሚሏት ግጭቱን እያባባሱት ያሉት በመጀመሪያ እና በዋናነት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው ሲል ከሰዋል ።
ይህ በንዲህ እንዳለ ፑቲን ዩክሬን በሩሲያ በተያዘችው ዛፖሪዝሂያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ ያለውን አካባቢ በመምታት አደገኛ ጨዋታ እየተጫወተች መሆኑን አስጠንቅቀው ሞስኮ በዩክሬን ቁጥጥር ስር ባሉ የኒውክሌር ፋብሪካዎች ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ጠቁመዋል።
"አሁንም በጎናችን በአውሮፓ ትልቁ የሆነው የኑክሌር ሃይል የሚሰሩ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች አለ። የኬቭን በአይነት ምላሽ እንዳንሰጥ የሚከለክለን ምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ ያስቡበት" ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን ሃሙስ ዕለት ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለመፍታት እና በሀገሮቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ እየጣረ ቢሆንም የአውሮፓ ሀገራት እያበላሹት ይገኛል
"ትራምፕ ማዳመጥ የሚችል ሰው ነው" ሲሉ አወድሰዋል በማለት የዘገበዉ ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

9 months ago
ሁሉም ወጣት ወደ ጦር ግንባር አባት ሃገር ሩሲያ ወይም ሞት ! /ፑቲን /
ከ ኔቶ አባለ ሀገራት ጋር በፍጥጫ ላይ የምትገኘው ሩሲያ በታሪኳ ግዙፍ የሆነ የሃገር ሉአላዊነት የማስጠበቅ ወታደራዊ ጥሪ አደረገች ።
በየአመቱ በየፀደይ እና በመጸው ወራት ወጣት ወንዶችን ለግዳጅ አገልግሎት ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ዝግጁ የምታደርገው ሩሲያ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ጀምሮ በሀገሪቱ ትልቁ የበልግ የግዳጅ ስልጠና 135,000 ሰዎችን ለመደበኛ ወታደራዊ አገልግሎት ጥሪ ማቅረቧ ተሰምቷል ።
ምዕራባዉያኑና አሜሪካ በዩክሬን ጀርባ ታዝለዉ ስንቅና ትጥቅ በገፍ እያቀረቡ በሚደረገው የዩክሬን ሩሲያ በቀጠለበት ወቅት ቭላድሚር ፑቲን እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ዓመት የሆኑ 135,000 ወንዶች የሀገሪቱን ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቀላቀሉ በሩሲያ ትልቁን ወታደራዊ የውትድርና ስልጠና እንድትወስድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ።
ሰኞ እለት በወጣው አዋጅ ፑቲን 'ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2025 135,000 የሩስያ ፌዴሬሽን ዜጎች ለውትድርና እንዲመዘገቡ' አዘዋል ።ተብሏል
ፑቲን ትናንት ምሽት በክሬምሊን ድረ-ገጽ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዩክሬን ላይ 'ፍትሃዊ ጦርነት' ሲሉ የጠሩትን ኃይላቸው እያሸነፈ ነው ብለዋል።
ተዋጊዎቻችንና አዛዦቻችን ለሀገራቸው ሀያልነት ገናናነት እናም ሊያጠፋት ያሰፈሰፉ ጠቅላዮችን አደብ ለማስገዛት ይህን የጽድቅ ጦርነት እያካሄደችና ጠንክራ እየሰራች ነው።
"ለእናት ሀገር ያለንን ፍቅር እና ታሪካዊ እጣ ፈንታችን አንድነቶን በጋራ እየጠበቅን ነው እየተዋጋን እያሸነፍን ነው" ብለዋል ፕሬዘዳንቱ ።
እ.ኤ.አ. የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ጥቃቱን ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለደህንነታቸው ከፍተኛ ትኩረት የሰጡት ፑቲን ሩሲያን ሃያል ለማድረግ ከሶቪየት ዘመናት ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወታደራዊ ወጪዋን በብዙ ደረጃ ጨምረዋል ።
በየአመቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከኮሌጅ በሚመረቁበት በሚያዝያ እና በጁላይ መካከል ባለው የፀደይ ዘመቻ ብዙ ወንዶች ለወታደራዊ ግዳጅ ጥሪ በማድረግ ጥሪ የምታደርገው ሩሲያ በዘንድሮው አመት ያደረገችው ጥሪ ባለፉት አስር አመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ታይቶ አይታወቅም ተብሏል ።
የሩስያ ተዋጊ ጄቶች ወደ ኢስቶኒያ ከገቡ በኋላ በኔቶ የጦር አውሮፕላኖች ከተጠለፉ በኋላ ፑቲን ወደ ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ አካባቢዎች ሊፈጽም ይችላል የሚለው ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴርም ትናንት ምሽት ሻንድሪሆሎቭ እና ዛሪክን የተባሉትን የምስራቅ ዶኔትስክ ሁለት ሰፈሮች መቆጣጠሩን ገልጿል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ አንድሬ ቤሎሶቭ ግዛቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀዩ ጦር ላደረገው 'ደፋር እና ወሳኝ' እርምጃዎች እንኳን ደስ አለን በማለት መግለጫ አውጥቷል ። ሲሉ የዘገቡት ሞስኮ ታይምስና ደይሊ ሜል ናቸዉ ።

Sponsored by
Surafel
9 months ago
ሩሲያ በኔቶ ላይ ንቀቷንና ድፍረቷን እያሳየች ነዉ!/ ፊንላንድ/
ለልእለ ሀያሏ ሀገር ሩሲያ የኔቶ አባል የሆኑ ሀገራት የአየር ክልል በተደጋጋሚ በመጣስ በነገር እየጎነተለች ትገኛለች መባሉ ተሰማ ።
ይህም የተባለዉ ሶስት የሩስያ ተዋጊ ጄቶች አርብ ዕለት የባልቲክ ሀገራት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሰው “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ድፍረት የተሞላበት” የተባለውን የወሰዱት እርምጃ ሲሆን ይህም በክሬምሊን ሃይሎች በኔቶ የጥበቃ ጥላ ስር ባሉ ሀገራት ላይ እያሳየች ያለችዉ ድፍረት የሞላበት ተግባር ተብሏል ።
ወረራው የተከሰተው በፊንላንድ ባህረ ሰላጤ ላይ ሲሆን MIG-31 ተዋጊ አውሮፕላኖች ያለፈቃድ ወደ ኢስቶኒያ አየር ክልል በመግባት ለ12 ደቂቃ ያህል እዚያው መቆየታቸውን የኢስቶኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
"ሩሲያ በዚህ አመት አራት ጊዜ የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሳለች, ይህም ተቀባይነት የለውም. ነገር ግን የዛሬው ወረራ, ሶስት ተዋጊ አውሮፕላኖች ወደ አየር ክልላችን የገቡት, ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ድፍረት የተሞላበት ነው" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርገስ Tsahkna በመግለጫው ተናግረዋል ።
አክለውም “የሩሲያ ድንበሮች መጣስና እና ንቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግፊት በፍጥነት መጨመር አለበት” ብለዋል ።
የኢስቶኒያ መንግስት በ MiG-31's ወረራ በሀገሪቱ ውስጥ ላለው ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት ተቃውሞ ማሰማቱን ተናግሯል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ኤንቢሲ ኒውስ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም አስተያየትም ሆነ ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም ተብሏል።

10 months ago
ከ20 በላይ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የእስራኤልን ህገወጥ የሰፈራ እቅድ ተቃወሙ
#ethiopia | ዩናይትድ ኪንግደም፣አውስትራሊያ እና ጃፓን እስራኤል በዌስት ባንክ አወዛጋቢ የሆነ ህገወጥ የሰፈራ እቅድ ለመገንባት የያዘችውን ውጥን ካወገዙት 21 ሀገራት መካከል ሆነዋል።
ይህ የእስራኤል እቅድ ለፍልስጤማውያን የወደፊት የሁለት ሀገር መፍትሄ የማይቻል ነው ብለዋል። "ይህን ውሳኔ እናወግዛለን እናም በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን" በማለት 21ዱ ሀገራት የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የእስራኤል የግንባታ እቅዶችን "የዓለም አቀፍ ህግን መጣስ ነው" በማለት ገልጸዋል።
መግለጫው ሊወጣ የቻለው በዚህ ሳምንት እስራኤል ከኢየሩሳሌም በምስራቅ 12 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፍራ ላይ “ምስራቅ 1” ወይም “E1” ተብሎ በሚጠራው መሬት ላይ በይፋ እንደምትንቀሳቀስ የሚገልጽ ዜና መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።
ለእስራኤላውያን ሰፋሪዎች 3,400 አዳዲስ ቤቶችን ግንባታ የሚያጠቃልለው ልማት አብዛኛው ከዌስት ባንክ ግዛት የሚወሰድ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን የሚያቋርጥ ሲሆን በአካባቢው በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ የእስራኤል ሰፋሪዎችንም ያገናኛል። ምስራቅ እየሩሳሌም ለፍልስጤማውያን የወደፊት የፍልስጤም መንግስት ዋና ከተማ ዋና ምርጫ በመሆን ልዩ ትርጉም ይሰጣታል።
እንደ ዳጉ ጆርናል ዘገባ የ 21 ሀገራት ቡድን የሁለት ሀገር የመፍትሄ ሃሳብ የሚባለውን የእስራኤል እና የፍልስጤም መንግስት ምስረታ ማንኛውም እቅድ "የትኛውንም የፍልስጤም መንግስት በመከፋፈል እና ፍልስጤማውያን ወደ እየሩሳሌም እንዳይገቡ በመገደብ የማይቻል ይሆናል" ብሏል።
በ21ዱ ሀገራት ቡድን ውስጥ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ላትቪያ፣ ሊትዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ፣ ፖርቱጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን እና ስዊድን ይገኙበታል ።

Comments