ከ20 በላይ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የእስራኤልን ህገወጥ የሰፈራ እቅድ ተቃወሙ
#ethiopia | ዩናይትድ ኪንግደም፣አውስትራሊያ እና ጃፓን እስራኤል በዌስት ባንክ አወዛጋቢ የሆነ ህገወጥ የሰፈራ እቅድ ለመገንባት የያዘችውን ውጥን ካወገዙት 21 ሀገራት መካከል ሆነዋል።
ይህ የእስራኤል እቅድ ለፍልስጤማውያን የወደፊት የሁለት ሀገር መፍትሄ የማይቻል ነው ብለዋል። "ይህን ውሳኔ እናወግዛለን እናም በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን" በማለት 21ዱ ሀገራት የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የእስራኤል የግንባታ እቅዶችን "የዓለም አቀፍ ህግን መጣስ ነው" በማለት ገልጸዋል።
መግለጫው ሊወጣ የቻለው በዚህ ሳምንት እስራኤል ከኢየሩሳሌም በምስራቅ 12 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፍራ ላይ “ምስራቅ 1” ወይም “E1” ተብሎ በሚጠራው መሬት ላይ በይፋ እንደምትንቀሳቀስ የሚገልጽ ዜና መሰራጨቱን ተከትሎ ነው።
ለእስራኤላውያን ሰፋሪዎች 3,400 አዳዲስ ቤቶችን ግንባታ የሚያጠቃልለው ልማት አብዛኛው ከዌስት ባንክ ግዛት የሚወሰድ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን የሚያቋርጥ ሲሆን በአካባቢው በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ የእስራኤል ሰፋሪዎችንም ያገናኛል። ምስራቅ እየሩሳሌም ለፍልስጤማውያን የወደፊት የፍልስጤም መንግስት ዋና ከተማ ዋና ምርጫ በመሆን ልዩ ትርጉም ይሰጣታል።
እንደ ዳጉ ጆርናል ዘገባ የ 21 ሀገራት ቡድን የሁለት ሀገር የመፍትሄ ሃሳብ የሚባለውን የእስራኤል እና የፍልስጤም መንግስት ምስረታ ማንኛውም እቅድ "የትኛውንም የፍልስጤም መንግስት በመከፋፈል እና ፍልስጤማውያን ወደ እየሩሳሌም እንዳይገቡ በመገደብ የማይቻል ይሆናል" ብሏል።
በ21ዱ ሀገራት ቡድን ውስጥ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ጣሊያን፣ ላትቪያ፣ ሊትዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዌይ፣ ፖርቱጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን እና ስዊድን ይገኙበታል ።

10 months ago