Logo
SeledaPost
በዓለማችን ከፍተኛ የወንድ እጥረት የታየባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ ተደረገ

በዓለማችን ላይ ባለው የሥነ-ሕዝብ ስርጭት መሠረት በአንዳንድ ሀገራት በወንዶች እና በሴቶች ቁጥር መካከል ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ መሆኑን ጥናቶች አመለከቱ።

ይህ የወንድ እጥረት በግንባር ቀደምትነት የሚታይባት ላትቪያ በየ 100 ሴቶች 80 ወንዶች ብቻ የሚገኙባት ሀገር ስትሆን ምስራቅ አውሮፓዊቷ ሊቱዌኒያም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍተኛ የጾታ መዛባት ያለባት ሀገር ሆና ተመዝግባለች።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ በወንዶች ቁጥር ላይ ከፍተኛ ቅናሽ የታየባት ሩሲያ በአሁኑ ሰዓት የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በ11 ሚሊዮን ገደማ ብልጫ ያለው ሲሆን ጎረቤቶቿ ዩክሬን፣ ኢስቶኒያ እና ቤላሩስም በተመሳሳይ የወንዶች ቁጥር እጥረት ከታየባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

እንደ ተመራማሪዎች ገለፃ ለዚህ አሀዛዊ ልዩነት ዋነኞቹ ምክንያቶች ወንዶች ለከባድ የጉልበት ስራ መጋለጣቸው፣ በጦርነት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆን እና ከሴቶች ጋር ሲነፃፀር ለጤናቸው የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆኑ ለሞት ምጣኔው መጨመር ምክንያት ሆኗል።

ይህ የሕዝብ ቁጥር መዛባት በእነዚህ ሀገራት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱ የሆነ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በጋብቻ እና በስራ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.