Logo
YenetaTube
ሩሲያ በኔቶ ላይ ንቀቷንና ድፍረቷን እያሳየች ነዉ!/ ፊንላንድ/

‎ለልእለ ሀያሏ ሀገር ሩሲያ የኔቶ አባል የሆኑ ሀገራት የአየር ክልል በተደጋጋሚ በመጣስ በነገር እየጎነተለች ትገኛለች መባሉ ተሰማ ።

‎ይህም የተባለዉ ሶስት የሩስያ ተዋጊ ጄቶች አርብ ዕለት የባልቲክ ሀገራት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሰው “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ድፍረት የተሞላበት” የተባለውን የወሰዱት እርምጃ ሲሆን ይህም በክሬምሊን ሃይሎች በኔቶ የጥበቃ ጥላ ስር ባሉ ሀገራት ላይ እያሳየች ያለችዉ ድፍረት የሞላበት ተግባር ተብሏል ።

‎ወረራው የተከሰተው በፊንላንድ ባህረ ሰላጤ ላይ ሲሆን MIG-31 ተዋጊ አውሮፕላኖች ያለፈቃድ ወደ ኢስቶኒያ አየር ክልል በመግባት ለ12 ደቂቃ ያህል እዚያው መቆየታቸውን የኢስቶኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

‎"ሩሲያ በዚህ አመት አራት ጊዜ የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሳለች, ይህም ተቀባይነት የለውም. ነገር ግን የዛሬው ወረራ, ሶስት ተዋጊ አውሮፕላኖች ወደ አየር ክልላችን የገቡት, ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ድፍረት የተሞላበት ነው" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርገስ Tsahkna በመግለጫው ተናግረዋል ።

‎አክለውም “የሩሲያ ድንበሮች መጣስና እና ንቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግፊት በፍጥነት መጨመር አለበት” ብለዋል ።

‎የኢስቶኒያ መንግስት በ MiG-31's ወረራ በሀገሪቱ ውስጥ ላለው ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት ተቃውሞ ማሰማቱን ተናግሯል።

‎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ኤንቢሲ ኒውስ ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም አስተያየትም ሆነ ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም ተብሏል።


‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ


9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.