Logo
YenetaTube
ከፈለግን መላዉን አዉሮጳ እንዳልነበረ እናደርገዋለን ! /ፑቲን /

‎የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮን ለማዳከም በአንድነት የተነሱትን አዲስ የ"አውሮፓ ጦር ሃይል"የተባለ ጥምር ጦር በማደራጀት ላይ የሚገኙትን ሀገራት በሩሲያ ላይ ትንኮሳ ለማድረግ ቢሞክሩ በታሪክ አይተዉት የማያዉቁት ምላሽ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ተነገረ ።

‎በሞስክ ላይ የኢኮኖሚ የፖለቲካዊ ቴክኖሎጂ ስርዓት የበላይነት ለመዉሰድና በጋራ ለመዝመት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ረቡዕ በዴንማርክ ዋና ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ዉሳኔ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ፑቲን "የሩሲያን ሰላማችን እና ለደህንነታችን ሃይላችን ከአደጋዎች ለመጠበቅ ሉዓላዊነታችን የተጋፋ እና መንግስታችን ላይ አደጋ የሚያደርስ አዝማሚያ ካየን ፈጣን ምላሽ እንደምንሰጥ ሊታወቅ ይገባል ስንልማ። ብለዋል

‎ይህንን ያሉትም ሀሙስ እለት በደቡባዊ ሪዞርት ከተማ በሶቺ ውስጥ በተካሄደው የውጭ ፖሊሲ መድረክ ላይ ነዉ ።

‎ፕሬዘዳንቱ የሰሞኑን ሩሲያን ለመክበብ ያለመ ዉሳኔያቸዉን እየተከታተሉ መሆኑን በመጥቀስ የምዕራባውያን ግብዝነት እና የክልላዊ የበላይነት ፍላጎት ሰላምን የሚያደፈርሱ አብሮ ለመኖር የማያስችሉ የከበባ ተግባር ሁኖ ሳለ ሞስኮን እንደግጭት ጠማቂ አድርጎ ለማሳየት መንደፋደፋቸዉ ብስጭት እንዳሳደረባቸው ገልጸው የአጸፋ እርምጃም ፈጣን እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።

‎ሁሉም የኔቶ አገሮች እኛን እየተዋጉን ነው, እና ከአሁን በኋላ አይደብቁትም" ለዩክሬን መረጃን በመስጠት እና የጦር መሳሪያዎችን በማቅረብ በውጊያ ስራዎች ውስጥ እየተሳተፉ " መሆኑን አረጋግጠዋል ።

‎ሩሲያን በፖላንድ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ወረራ እና በኢስቶኒያ ላይ የፈፀመችዉ የተዋጊ ጄቶች ጥቃት ጨምሮ ሩሲያ የክልሉን አየር ክልል በጅምላ እየጣሰች ነው ሲሉ የአውሮፓ ባለስልጣናት ያቀረቡትን ክስ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት የአውሮፓ ሀገራት ሩሲያ ላይ በሬ ወለደ የውሸት ወሬ በመፍጠር ከመቶ ዓመታት በፊት የፈለሰፉትን ታዋቂ የጠላትነት ገፅታ እንደገና ለመፍጠር እየሞከሩ ነዉ ብለዋል ።

‎አክለውም በዩክሬን ያለውን ጦርነት የማስቆም ሃላፊነት በአውሮፓ ሀገራት ላይ ነው ያሉት ፑቲን እንደ አለመታደል ሆኖ እስካሁን ድረስ ግጭቱን ማቆም አልቻልንም, የዚህም ምክንያት ስንቅና ትጥቅ የሚያቀርቡ ዩክሬንን በርቺ በርቺ የሚሏት ግጭቱን እያባባሱት ያሉት በመጀመሪያ እና በዋናነት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው ሲል ከሰዋል ።

‎ይህ በንዲህ እንዳለ ፑቲን ዩክሬን በሩሲያ በተያዘችው ዛፖሪዝሂያ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ ያለውን አካባቢ በመምታት አደገኛ ጨዋታ እየተጫወተች መሆኑን አስጠንቅቀው ሞስኮ በዩክሬን ቁጥጥር ስር ባሉ የኒውክሌር ፋብሪካዎች ላይ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ጠቁመዋል።

‎"አሁንም በጎናችን በአውሮፓ ትልቁ የሆነው የኑክሌር ሃይል የሚሰሩ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች አለ። የኬቭን በአይነት ምላሽ እንዳንሰጥ የሚከለክለን ምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ ያስቡበት" ብለዋል ፑቲን።

‎ፑቲን ሃሙስ ዕለት ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለመፍታት እና በሀገሮቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ እየጣረ ቢሆንም የአውሮፓ ሀገራት እያበላሹት ይገኛል
‎"ትራምፕ ማዳመጥ የሚችል ሰው ነው" ሲሉ አወድሰዋል በማለት የዘገበዉ ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።

‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ



8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.