Logo
YenetaTube
ሁሉም ወጣት ወደ ጦር ግንባር አባት ሃገር ሩሲያ ወይም ሞት ! /ፑቲን /

ከ ኔቶ አባለ ሀገራት ጋር በፍጥጫ ላይ የምትገኘው ሩሲያ በታሪኳ ግዙፍ የሆነ የሃገር ሉአላዊነት የማስጠበቅ ወታደራዊ ጥሪ አደረገች ።

በየአመቱ በየፀደይ እና በመጸው ወራት ወጣት ወንዶችን ለግዳጅ አገልግሎት ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ዝግጁ የምታደርገው ሩሲያ እ.ኤ.አ. ከ 2016 ጀምሮ በሀገሪቱ ትልቁ የበልግ የግዳጅ ስልጠና 135,000 ሰዎችን ለመደበኛ ወታደራዊ አገልግሎት ጥሪ ማቅረቧ ተሰምቷል ።

ምዕራባዉያኑና አሜሪካ በዩክሬን ጀርባ ታዝለዉ ስንቅና ትጥቅ በገፍ እያቀረቡ በሚደረገው የዩክሬን ሩሲያ በቀጠለበት ወቅት ቭላድሚር ፑቲን እድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ዓመት የሆኑ 135,000 ወንዶች የሀገሪቱን ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቀላቀሉ በሩሲያ ትልቁን ወታደራዊ የውትድርና ስልጠና እንድትወስድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ።

ሰኞ እለት በወጣው አዋጅ ፑቲን 'ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2025 135,000 የሩስያ ፌዴሬሽን ዜጎች ለውትድርና እንዲመዘገቡ' አዘዋል ።ተብሏል

ፑቲን ትናንት ምሽት በክሬምሊን ድረ-ገጽ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በዩክሬን ላይ 'ፍትሃዊ ጦርነት' ሲሉ የጠሩትን ኃይላቸው እያሸነፈ ነው ብለዋል።

ተዋጊዎቻችንና አዛዦቻችን ለሀገራቸው ሀያልነት ገናናነት እናም ሊያጠፋት ያሰፈሰፉ ጠቅላዮችን አደብ ለማስገዛት ይህን የጽድቅ ጦርነት እያካሄደችና ጠንክራ እየሰራች ነው።

"ለእናት ሀገር ያለንን ፍቅር እና ታሪካዊ እጣ ፈንታችን አንድነቶን በጋራ እየጠበቅን ነው እየተዋጋን እያሸነፍን ነው" ብለዋል ፕሬዘዳንቱ ።

እ.ኤ.አ. የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ጥቃቱን ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለደህንነታቸው ከፍተኛ ትኩረት የሰጡት ፑቲን ሩሲያን ሃያል ለማድረግ ከሶቪየት ዘመናት ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወታደራዊ ወጪዋን በብዙ ደረጃ ጨምረዋል ።

በየአመቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከኮሌጅ በሚመረቁበት በሚያዝያ እና በጁላይ መካከል ባለው የፀደይ ዘመቻ ብዙ ወንዶች ለወታደራዊ ግዳጅ ጥሪ በማድረግ ጥሪ የምታደርገው ሩሲያ በዘንድሮው አመት ያደረገችው ጥሪ ባለፉት አስር አመታት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ታይቶ አይታወቅም ተብሏል ።

የሩስያ ተዋጊ ጄቶች ወደ ኢስቶኒያ ከገቡ በኋላ በኔቶ የጦር አውሮፕላኖች ከተጠለፉ በኋላ ፑቲን ወደ ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ አካባቢዎች ሊፈጽም ይችላል የሚለው ስጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴርም ትናንት ምሽት ሻንድሪሆሎቭ እና ዛሪክን የተባሉትን የምስራቅ ዶኔትስክ ሁለት ሰፈሮች መቆጣጠሩን ገልጿል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ አንድሬ ቤሎሶቭ ግዛቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀዩ ጦር ላደረገው 'ደፋር እና ወሳኝ' እርምጃዎች እንኳን ደስ አለን በማለት መግለጫ አውጥቷል ። ሲሉ የዘገቡት ሞስኮ ታይምስና ደይሊ ሜል ናቸዉ ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.