8 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ይህን ዘገባ ትናንት በቪዲዮ አቅርበነው ነበር፤ ብዙዎቻችሁ፣ 'ኢንተርኔት ፍጥነት በሌለባቸው አካባቢዎች ቪድዮ ለማየት ስለሚቸገሩ' በጽሑፍ ይቅረብልን ባላችሁን መሠረት እንደሚከተለው ቀርቧል | ወዳጅነት... ከለላና መሸሸጊያ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፤ ለዲዛይነር ቅድሳን ይርጋለም ግን ወዳጅነት የሞት ወጥመድ ሆኖ አረፈው። የ2026ቱ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" የውበት ንግሥት የሩት ይርጋለም ታላቅ እህት የሆነችው ቅድሳን፣ በሞዴሊንግ ዓለም ውስጥ ስኬትን ከምትመኘውና ከእህቷ ጋርም የትምህርት ቤት ትውውቅ ከነበራት ቅድስት ሙሉቀን ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ነበራት። ሆኖም ከዚህ ጓደኝነት ጀርባ፣ ጥልቅ የሆነ ምቀኝነት እና አደገኛ ሴራ ተሸሽጎ ነበር።
ሁሉም ነገር የተጀመረው አርብ ዕለት በተደረገ አንድ የስልክ ጥሪ ነው። ለአንድ ዓመት ያህል ተጠፋፍታ የነበረችው ቅድስት፣ የናፍቆት በሚመስል የጓደኝነት መንፈስ ለቅድሳን ደወለች። "አዲስ ኮንዶሚኒየም ተከራይቻለሁ፤ መጥተሽ ቤቴን እዪልኝ። ደግሞም የማገናኝሽ አዲስ የስራ እድል አለ" በማለት የጓደኛዋን ልብ አባበለች። በጓደኛዋ ላይ አንዳችም ክፋት ያልጠረጠረችው ቅድሳን፣ ሜክሲኮ አካባቢ ተገናኝተው አብረው ወደ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም አመሩ። ቅድሳን የጓደኛዋን አዲስ ሕይወት ለማየት በደስታ ስትጓዝ፣ እየሄደች ያለችው ግን ወደራሷ የሞት ቀጠሮ ነበር።
አዲሱ ቤት ደጃፍ ላይ ደርሰው ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ የነበረው ወዳጃዊ ድባብ ቅጽበታዊ በሆነ ሽብር ተተካ። ቤት ውስጥ አድፍጦ ይጠብቅ የነበረው የቅድስት ፍቅረኛ ደሳለኝ፣ ቅድሳን ድምጿን አውጥታ እንኳ ርዳታ እንዳትጠራ አፍኖ አሰራት። ያመነቻት ጓደኛዋ እጅ ከፍንጅ ለሞት አሳልፋ ሰጠቻት።
አጋቾቹ ወዲያውኑ የሟች ቤተሰቦች ጋር በመደወል የሁለት ሚሊዮን ብር ቤዛ ጠየቁ። የቤተሰብ ልብ በጭንቀት እየመታ የድርድር ሀሳቦች ሲለዋወጡ፣ አጋቾቹ አንድ ዘግናኝ እውነት ተገነዘቡ። የጠየቁትን ገንዘብ ቢያገኙ እንኳ፣ ሟች በቅርበት ስለምታውቃቸው ነገ ሚስጥራቸውን አሳልፋ እንደምትሰጣቸው አሰቡ። ፍርሃት እና ምቀኝነት ያደነደነው ልባቸው፣ እዚያው አርብ ዕለት ጭካኔ የተሞላበት ውሳኔ ላይ ደረሰ። የቅድሳንን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አጠፉ። አስከሬኗንም ማንም እንዳያገኘው በሚል እዚያው አካባቢ በተከራዩት ሌላ ተጨማሪ ቤት ውስጥ ደበቁት።
ይሁን እንጂ...የፈጸሙት ግፍ በጨለማ ሊቀበር አልቻለም። ፖሊስ ባደረገው አፋጣኝ እና የተቀናጀ ክትትል፣ ዋነኛ ተጠርጣሪዋ ቅድስት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ጎተራ አካባቢ በቁጥጥር ስር ዋለች። የወንጀሉ ተባባሪ የነበረው ደሳለኝ ደግሞ፣ ሁኔታው ሲከፋበት ለማምለጥ ሞክሮ አዳማ ከተማ ውስጥ ተደብቆ እያለ በፖሊስ መረብ ውስጥ ወደቀ። በአጠቃላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስምንት ሰዎች ታሰሩ። ዋነኛ ተጠርጣሪዎቹም ወንጀሉን መፈጸማቸውን አምነው፣ እንዴት እንዳከናወኑት በቦታው ተገኝተው ለፖሊስ አሳይተዋል።
ይህ ክስተት የ2026ቷን የውበት ንግሥት ሩትን ብቻ ሳይሆን፣ መላውን ማኅበረሰብ በሐዘን እና በስጋት ውስጥ ጥሏል። ሩት በልብ ስብራት "ከጠላቴ እኔ እጠነቀቃለሁ፤ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ" ብላ ያሰፈረችው መልእክት፣ የዚህን ትረካ አሳዛኝ ማጠቃለያ ይወክላል፦ ጠላት ፊቱን አውቆ ሲመጣ፣ ክህደት ግን በወዳጅ ፈገግታ ታጅቦ ይመጣል።

11 days ago
የታዳሽ ኃይል ልማት ጉዞዋን ያጠናከረችው ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማትና የቀጣናው ትስስር ጉዞ እየተሻሻለ እና ወደ አስተማማኝ አጋርነት እያደገ ይገኛል፡፡
ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ወሳኝ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን እውነት በመረዳት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሪነት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያሰፉና የሚያዘምኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነች ትገኛለች።
ይህ ስትራቴጂካዊ ጉዞ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከጨለማ ከማውጣት ባለፈ ሀገሪቱን የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ታላቅ ብሔራዊ ራዕይ ነው።
የዚህ ግዙፍ የኃይል መሠረተ ልማት ግንባታ ግንባር ቀደም ተምሳሌት የሆነው የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጽናት፣ የጥበብ፣ የአብሮነትና የመተባበር መገለጫ ነው።
ግድቡ የዓባይን ወንዝ ተፈጥሯዊ ፍሰት ሳይገታና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ጥቅም ሳይነካ የውሃውን ኃይል ወደ ንጹህ የኤሌክትሪክ ብርሃንነት በመቀየር ረገድ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል።
የውሃ አሞላልና የግንባታ ምዕራፎቹን በተሳካ ሁኔታ እያጠናቀቀ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ተቋም፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በእጥፍ ለማሳደግ ታላቅ አቅም ሆኗል።
ግድቡ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለከተሞች መስፋፋትና ለገጠር አካባቢዎች የብርሃን ምንጭ በመሆን የኢኮኖሚውን ሞተር በማንቀሳቀስ ላይ ነው።
ነገር ግን የኢትዮጵያ የኃይል ስትራቴጂ በውሃ ሀይል ወይም በሕዳሴው ግድብ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም።ሀገሪቱ የኃይል ምንጮቿን ከማስፋት ረገድ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
በውሃ ኃይል ረገድ እንደ ኮይሻ፣ ግልገል ጊቤ እና ሌሎች የወንዝ ተፋሰሶች ላይ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሜጋ ዋት ሀይልን ለብሔራዊ ኃይል ቋት እያበረከቱ ናቸው።
ከዚህም በተጓዳኝ፣ ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ጸጋ በመነሳት የንፋስ ኃይል፣ የፀሐይ ብርሃን ኃይል እና የምድር ውስጥ እንፋሎት ልማቶችን በስፋት እያከናወነች ትገኛለች።
እንደ አሸጎዳ እና አዳማ ያሉ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች እንዲሁም የአሉቶ ላንጋኖ የምድር ውስጥ እንፋሎት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን ታዳሽ ኃይል ይበልጥ አስተማማኝ እና ከተፈጥሮ መዛባት የተጠበቀ እያደረጉት ይገኛሉ።
ይህ በሀገር ውስጥ የሚመነጨው ግዙፍ የኃይል አቅም ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ ቀጣናዊ ትስስርን ለመፍጠር ትልቅ መሣሪያ እየሆነ ነው።
ኢትዮጵያ "የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማማ" የመሆን ራዕይዋን ለማሳካት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመዘርጋት ላይ ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅት ለጎረቤት ሀገራት እንደ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ የምትገኝ ሲሆን÷ ይህ ትስስር ወደ ታንዛኒያ እና ሌሎች የደቡብ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት እንዲደርስ ሰፊ የዲፕሎማሲና የቴክኒክ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፤ የሙከራ ሸያጭ የተጀመረባቸው ሀገራትም አሉ።
ይህ የኃይል ሽያጭ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ከመሆኑም በላይ በቀጣናው ሀገራት መካከል ያለውን የሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ማጠናከሪያ የዲፕሎማሲ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብና በሌሎች ዘርፈ ብዙ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ላይ እያደረገችው ያለው ርብርብ የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍላጎትን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ የሃይል ምንጮች 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል አመንጭታለች፡፡
በእመቤት ሲሳይ

ከችርቻሮ የሱቅ ስራ የተነሳው ጊፍት ትሬዲንግ 35ኛ አመቱን አከበረ
#ethiopia | በኢትዮጵያ በገቢና ወጪ ንግድ ዘርፍ አንጋፋ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ጊፍት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩ በዓል በዛሬዉ እለት አክብሯል።
በንግድ ማህበረሰቡ፣ በመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና በድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ኩባንያው ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከግማሽ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ያቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይም ወደ አግሮ-ኢንዱስትሪ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ይፋ ባደረገው እቅድ መሠረት በአዳማ እና ሞጆ ከተሞች መካከል በሚገኘው የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ፍሪ ዞን ውስጥ 7,527.54 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡን ገልፀዉ ቦታው ከጅቡቲ ኮሪደር እና ከሞጆ ደረቅ ወደብ አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ፣ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳልጠው የተገለጸ ሲሆን፤ የአካባቢው የዲዛይን ስራ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ምዕራፍ መሸጋገሩ ተመልክቷል።
ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው እሴት በተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች ዘርፍ መሰማራት የጀመረ ሲሆን፣ በተለይም በድፍድፍ የአቮካዶ ዘይት ማምረት እና በከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አስመጪነት ዘርፍ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን ለማሳደግ እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የጥቁር አዝሙድ እርሻ መጀመሩን የጠቆመው ጊፍት ትሬዲንግ፤ በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ 300 ሄክታርየቡና እርሻ መሬት ተረክቦ ወደ ምርት እንደሚገባ አስታውቋል።
ከ50 ዓመታት በፊት በመርካቶ በታዋቂው የቢዝነስ ሰው በአቶ ገብረኢየሱስ ኢጋታ ሲማ በትንሽ የችርቻሮ ሱቅ የተጀመረው ይህ የንግድ እንቅስቃሴ፣ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ወደ ገቢና ወጪ ንግድ በማደግ ለዛሬው ግዙፉ ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ (ጊፍት ሪል እስቴት፣ ጊፍት ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ብረታ ብረት፣ ጊፍት ፕሮፐርቲ እና ጊፍት ቱር ኤንድ ትራቭል) መፈጠር መሰረት መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም B-29 የልብስ ሳሙና፣ የሮድ ስቶን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የጂንዳል ቆርቆሮዎች፣ የብረትና የኬሚካል ምርቶችን ጨምሮ በርካታ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ በማስተዋወቅ ረገድ ኩባንያው የነበረው ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተገልጿል።
ኩባንያው እ.ኤ.አ በ2030 በኢትዮጵያ በቡና፣ ቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ እና ቅመማ ቅመም ላኪነት ከግንባርቀደም 5 ኩባንያዎች አንዱ የመሆን ራዕይ ሰንቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #gifttradingrealstate #construction #technology

ጊፍት ትሬዲንግ 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩውን አከበረ!
#fastmereja :- በኢትዮጵያ በገቢና ወጪ ንግድ ዘርፍ አንጋፋ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ጊፍት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት የምስረታ ኢዮቤልዩ በዓል በዛሬዉ እለት አክብሯል።

Sponsored by
Surafel
17 days ago
የሰላም አማራጭን በማይቀበሉ አካላት ላይ አስፈላጊው ርምጃ ይወሰዳል - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አስተማማኝ ሰላምና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ።
የጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ ዓመት 6ኛ የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔ በአዳማ ጨፌ አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የክልሉ መንግሥት ሰላምን ለማስፈንና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የወሰዳቸው ርምጃዎች ውጤታማ ናቸው፡፡
በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ በተከናወነው ስራ የክልሉ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ጽኑ ፍላጎት በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን ገልጸዋል።
ሕዝቡ ዝናብና ፀሃይ ሳይበግረው በምርጫው በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ ለአፍራሽ አካላት ግልጽ መልዕክት ማስተላለፉን ነው ያስረዱት፡፡
በክልሉ በተለያየ መልክ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ሙከራ ቢደረግም በሰላም ወዳዱ ሕዝብና በጸጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ጥረት መክሸፉን አመልክተዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት ለዘላቂ ሰላም መስፈን ባለው ጽኑ ፍላጎት መሰረት የቀረበውን የሰላም አማራጭ በመቀበል ወደ ሰላም የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
የመንግሥት የሰላም በር አሁንም ክፍት መሆኑን ያረጋገጡት አቶ ሽመልስ ÷ የሰላም አማራጩን ተቀብለው ለሚመጡ ታጣቂዎች በሩ ክፍት ነው ብለዋል።
የሰላም አማራጭን ወደ ጎን በመተው በጥፋት ተግባራቸው በሚቀጥሉ አካላት ላይ የክልሉ መንግሥት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ርምጃ እንደሚወስድ አስገንዝበዋል።
በዚህም በክልሉ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈንና የሕግ የበላይነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል መንግሥት በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በአቤል ነዋይ

19 days ago
"ኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙ አካላት አሉ"
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለውና ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የመንግሥት አመራሮች በሚሳተፉበት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኦሮሚያ ክልል "ጠፍቶ" ለማየት የሚመኙና ኦሮሚያ የሚለውን ቃል መስማት የማይፈልጉ አካላት አሉ ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ምኞት "በፍጹም" ሊሳካ እንደማይችል የገለጹት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ ይልቁንም ክልሉ ወደፊት ይበልጥ እየጠነከረ፣ መሬት እየያዘና ውጤታማ እየሆነ እንደሚሄድ በኦሮምኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚያ ክልል ጠፍቶ ማየት ይፈልጋሉ ያሏቸውን አካላት ማንነት ግን በስም ለይተው በንግግራቸው ውስጥ አልጠቀሱም። አቶ ሽመልስ ይህን የተናገሩት፣ የክልሎች አወቃቀር ጉዳይ ለአገራዊ ምክክር ጉባኤው በአጀንዳነት በቀረበበት ማግስት ነው።
Seledadotio

28 days ago
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ጥልቅ አንድምታ፤ መንግሥት የገነባው የትዕግሥትና የአርቆ አሳቢነት ቁመና
************************
ከከባድ የጦርነት አውድማና መገፋፋት በኋላ፣ አሸናፊና ተሸናፊ በእኩል ማዕድ ተቀምጠው የሰላምን ጽዋ ሲጋሩ፤ የተዘጉ በሮች ሲከፈቱ እና የፈረሱ የልብ ድልድዮች ሲጠገኑ መመልከት ምን ያህል ልብን በደስታ ይሞላል?
ይህ በዓለማችን እጅግ ብርቅ የሆነው የሰላም መንገድ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት በኩል በኢትዮጵያ ምድር እውን ሆኖ የሀገራችንን የፖለቲካ አቅጣጫ ወደ ተሻለ ብሩህ ተስፋ አሸጋግሮታል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት የፖለቲካ ድርድር ብቻ ሳይሆን፣ መንግሥት ለሰላም ያለውን የጸና ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት፣ አሸናፊ ሆኖ ሳለ ተሸናፊውን ኃይል በአክብሮት አቅፎ ወደ ጠረጴዛ ያመጣበት ታላቅ የትዕግስትና የአርቆ አሳቢነት ማሳያ ነው።
በዚህም ስምምነት መሠረት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ማቋቋም ከመቻሉም ባሻገር፣ ከስልሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎችን ትጥቅ በማስፈታትና አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
ከዚህም አልፎ በርካታ የጦር ምርኮኞች በነፃነት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች (እንደ አየር መንገድ እና ቴሌኮም) ሙሉ በሙሉ ተመልሰዋል።
መንግሥት ለዜጎቹ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች ቤተሰቦችን ሀብትና ንብረት ከመውረስ ታቅቦ፣ በአንድ ሰው የፖለቲካ ጥፋት ሙሉ ቤተሰብ መጎዳት የለበትም በሚል ሰፊ አመለካከት ሀብታቸውን ጠብቆ አስረክቧል።
ይህ ዓይነቱ ርኅራኄና የሰላም እርምጃ በርካቶችን ያስደሰተ ቢሆንም፣ የሰላሙን መንገድ ያልወደዱና በስምምነቱ ያኮረፉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ዛሬም ድረስ አልጠፉም። እነዚህ ኃይሎች በትግራይ ክልል በየጊዜው ትንኮሳዎችን ከመፍጠራቸውም በላይ፣ የትግራይን ወጣቶች በጉልበት እያፈሱና እየሸጡ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዲማገዱ በማድረግ በሕዝቡ ላይ የማይሽር የውስጥ ቁስል እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገራችን የተፈጠረው እጅግ አስገራሚው እውነታ ደግሞ፣ "ለሕዝብ እንታገላለን" የሚሉ ኃይሎች በሕዝቡ ላይ እያመጡት ያለው መከራ ነው። ዛሬ ላይ አንድ የትግራይ ተወላጅ በትግራይ ክልል ከሚኖረው ይልቅ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በሐዋሳ ወይም በአዳማ እጅግ የላቀ ሰላም አግኝቶ ያለምንም ስጋት ወጥቶ ይገባል።
በተመሳሳይ ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ ኃይሎች ባሉበት ቀዬ ያለው ነዋሪ በፍርሃት፣ በግድያና በዘረፋ ሲታመስ፤ አንድ የአማራ ተወላጅ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ወይም በሶማሌ ክልል የተሻለ ሰላም አግኝቶ ይኖራል። ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ቆመናል የሚሉ ኃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ያለው ነዋሪ ከቀዬው ሲሰደድ፣ በአንጻሩ በአማራ፣ በአፋር ወይም በሶማሌ ክልል የሚኖር የኦሮሞ ተወላጅ የተሟላ ሰላም አግኝቷል።
ይህ እውነታ በግልጽ የሚያሳየው ከሕዝብ ተነጥሎ፣ ሕዝብን አስለቅሶና ዘርፎ የሚደረግ ማንኛውም ትግል ከጥፋት በቀር የሚያመጣው አንዳች ፋይዳ እንደሌለ ነው።
መንግሥት ይህንን ሁሉ እያየ ወደ ተሟላ ጦርነትና ግጭት ከመግባት ይልቅ ትዕግስትን የመረጠው ያለ ምክንያት አይደለም። የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ አውድ ልክ እንደ አንድ "መጥረቢያ" ነው። በመጥረቢያው ዘይቤ መሠረት ሦስት ተዋናዮች አሉ፤ ቆራጩ የብረት ክፍል፣ ብረቱ የገባበት የእንጨት እጀታ፣ እና መጥረቢያውን ይዞ የሚቆርጠው።
የብረቱ ክፍል የራሱ ዓላማ የለውም፣ የእንጨቱን ትዕዛዝ ይፈጽማል፤ እንጨቱም ቢሆን የራሱ ፍላጎት የለውም፣ በመጥረቢያው አዛዥ እጅ ይመራል። በመሆኑም መንግሥት ከብረቱ ወይም ከእንጨቱ ጋር በመላተም ጊዜውን ከማጥፋት ይልቅ፣ የኢትዮጵያን ሰላም የሚያደፈርሰው ዋነኛ ምንጭ የት እንደሆነ በሚገባ ተገንዝቦ አደጋውን ለመቀልበስ የሚያስችል ጠንካራ የመከላከያ ቁመና ገንብቷል።
ብረቱንና እንጨቱንም ቢሆን በተቻለ መጠን በማስተማር፣ በመታገስና በመመለስ፣ የኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት የጋራ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ለማስገንዘብ በከፍተኛ ብስለት እየሠራ ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ የፈተናና የትዕግስት ጉዞ ጀርባ የምትታየው ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ዓመታት "ልትፈርስ ነው፣ ልትወድቅ ነው" የተባለባትን የክፉዎች ትርክት ቀልብሳ በአዲስ የማንሰራራት መንፈስ ውስጥ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ አትወድቅም ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊትም የተኙትን የምታነቃ፣ የወደቁትን የምታነሳና ሊበለጽጉ ሲገባቸው ያልገባቸውን ወንድምና እህቶቿን ይዛ ወደ ከፍታ የምትገሰግስ ታላቅ ሀገር ናት። ለዚህም ማሳያው የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሳይቀሩ፣ የ"መደመር" እሳቤን በልባቸው አኑረው፣ ስለ ሚዛናዊ የክልሎች ተጠቃሚነት፣ ስለ ኮሪደር ልማትና ስለ ተለያየ ኢኮኖሚ ግንባታ በአንድ ልብ መምከራቸው ነው።
ይህ የሐሳብ መወራረስና መቀራረብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን አጽንቶ፣ ልዩነቶቹን በውይይት ፈትቶ፣ የወደፊቱን የብልጽግና ጉዞ በጋራ ለማፋጠን የሚያስችል የማይናወጥ መሠረት መጣሉን የሚያበስር አስደሳች ምዕራፍ ነው።

29 days ago
"በነገራችን ላይ፣ ዛሬ፣ በትግራይ ውስጥ ከሚኖር ትግራዋይ በላይ፣ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚችል፣ አፈሳ የማይካሄድበት፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አርባምንጭ፣ ሀዋሳ ያለ ትግራዋይ፣ ትግራይ ካለው ሰው በላይ ሰላም አለው። ትግራይ ካለው ሰው በላይ በሰላም ወጥቶ መግባት ይችላል። የሚያሳዝነው ይሄ ጉዳይ ግን ትግራይ ብቻ አይደለም። አማራ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች፣ 'ለአማራ ህዝብ ሰላም፣ ደህንነት፣ ጥቅም እንታገላለን' ብለው የሚሉ ሃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ካለው የአማራ ተወላጅ ይልቅ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ ያለው አማራ ሰላም አለው። እነዚህ እንታገላለን የሚሉ ሃይሎች ያሉበት አካባቢ የበለጠ ፍራቻ፣ የበለጠ ግድያ፣ የበለጠ ዘረፋና መታገዶች አሉ።
"ኦሮሚያ አካባቢ ለኦሮሞ እንታገላለን ብለው የሚመሉ፣ የሚገዘቱ ሃይሎች ከሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በላይ፣ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀስ፣ በሱማሌ የሚንቀሳቀስ፣ በአፋር የሚንቀሳቀስ ኦሮሞ የተሻለ ሰላም አለው። ዜጎች በገዛ ቀያቸው፣ መንደራቸው፣ በገዛ ልጆቻቸው እየታመሱ ይገኛሉ። ከቀያቸው ሸሽተው መኖር የተሻለ ሰላም የሚያገኙበት እየሆነ መጥቷል። ከህዝብ ተነጥሎ፣ ህዝብ አስለቅሶ፣ ህዝብ ዘርፎ፣ የሚደረግ ትግል ደግሞ የትም ማድረስ እንደማይችል ከታሪኮቻችን መማር የምንችል ይመስለኛል።
መንግስት አብዛኛውን ጉዳይ በትዕግስት የሚያየው፣ ወደ ግጭት የማይገባው፣ ለምንድነው ያላችሁ እንደሆነ፣ አላማ ቢስ ነው። አላማ የለውም። ይሄንን ግጭት ከፈጸምን በኋላ 'አሳካን' ብለን የምንናገረው አንዳች ቁምነገር የለም። በዚያም በዚህም ብንገል፣ ብንሞት ትርጉም የለውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ትግራይ አካባቢ ያለው የፖለቲካል አውድ የመጥረቢያ ፖለቲካ ሰለባ ነው ትግራዋይ እና ኢትዮጵያዊያን የሆኑት።"
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፓርላማው ከተናገሩት

1 month ago
የቱሪዝም መዳረሻዎችን በዘመናዊ ስልት ለማስተዋወቅ የሚዲያ ፎረም ተመሰረተ
#ethiopia | የሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች በዘመናዊ መንገድ ለዓለም ለማስተዋወቅና የመረጃ ልውውጡን በተቀናጀ ስልት ለመምራት የሚያስችል የቱሪዝም ኮሙኒኬሽን ስልጠና በአዳማ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚሁ መድረክ ላይ የቱሪዝም ሚዲያ ፎረም በይፋ ተመስርቷል።
የፌደራልና የክልል የቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞችንና ኃላፊዎችን ያሳተፈው ይህ መርሃ-ግብር፣ በዘርፉ የሚታየውን የተበታተነ የኮሙኒኬሽን ስራ በማስቀረት የተቀናጀ የቱሪዝም ዲፕሎማሲ ለመገንባት ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሴ ክብሩ፣ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሀገሪቱ አምስት ዋና ዋና የኢኮኖሚ አመንጭ ዘርፎች ውስጥ አንዱ አድርጎ እየሰራበት መሆኑን ገልጸዋል።
በርካታ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማትና በነባሮቹ ላይ እሴት የመጨመር ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ እነዚህን ጸጋዎች በዘመናዊ ስልት ለአለም ማስተዋወቅና የሀገርን በጎ ገጽታ መገንባት የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሊወጡት የሚገባ ዋነኛ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለተሳታፊዎቹ ስልጠና የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት መምህር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የቱሪዝም ሚዲያ ስራ ከተለመደው የዜና አሰራር ወጥቶ ሳቢ፣ ታሪክን መሰረት ያደረገ እና ዲጂታል አማራጮችን የተጠቀመ ሊሆን እንደሚገባ አብራርተዋል።
አዲስ የተመሰረተው የሚዲያ ፎረም እስካሁን በዘርፉ በዘልማድ ከሚታየውና ለአንድ ወቅት ብቻ ከሚደረግ የመረጃ ልውውጥ ባለፈ፣ በክልሎችና በሚዲያ ተቋማት መካከል ወጥነት ያለውና ቀጣይነት ያለው የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት በመዘርጋት ለቱሪዝም እድገት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 11ኛውን ሀገር አቀፍ የስፖርት ሳይንስ የጥናትና ምርምር ጉባዔ አካሄደ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 11ኛውን ሀገር አቀፍ የስፖርት ሳይንስ የጥናትና ምርምር ጉባዔ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
በጉባዔው የተገኙት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ለውጥ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል።
የስፖርት ሪፎርም ሰነዶች ወደ ትግበራ መግባታቸው ዘርፉ የነበሩ የአመራርና የአሠራር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት መሠረት እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፣ ሪፎርሙ ጤናማና አምራች ዜጋ መፍጠር፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና ተወዳዳሪ አሸናፊ ትውልድ ማፍራትን ዋና ግቦች አድርጎ ይዟል።
በተጨማሪም አዲስ የስፖርት ፖሊሲና የስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ መጽደቃቸው ዘርፉን በህግና በስርዓት ለመምራት አስፈላጊ መሠረት እንደፈጠረ ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ስፖርት ወንድማማችነትን፣ አብሮነትን፣ ፍቅርና ሰላምን የሚያጎለብት በመሆኑ በሀገር ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰው፣ ባለሙያዎችም እውቀታቸውን በቀጣይነት በማሳደግ ዘመናዊ አሠራሮችን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አንበሳው እንየው በበኩላቸው፣ አካዳሚው ባለፉት 11 ዓመታት 159 የስፖርት ጥናቶችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
ከእነዚህ 45ቱ በአካዳሚው በራሱ አቅም የተከናወኑ ሲሆን፣ 114ቱ ደግሞ በተባባሪ ተመራማሪዎች የተጠኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በአዳማ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ሀገር አቀፍ ጉባዔ 12 የስፖርት ሳይንስ ጥናቶች ለተሳታፊዎች ቀርበው በስፋት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
#ethiopia #sports #ethiopiansportsacademy #sportsscience #research #adama #getu

አዲስ አበባ ክልል ልትሆን? ሕገ መንግስቱም ሊቀየር ነው?
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማድረጉ እየተሰማ ነው፡፡
ፓርቲው በይፋዊ ገጹ ላይ ባያረጋግጠው ስብሰባ መቀመጡን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
አንዳንድ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት ብልጽግና በዚህ ስብሰባው ሕገ መንግስቱን ለመቀየር፣ አዲስአበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ክልል ለማድረግ፣ የመሬት ፖሊሲን ለመቀየር፣ ስርአቱ ከፓርላሜንታዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ እንዲሆን መወሰኑ እየተሰማ ነው፡፡
እነዚህን መረጃዎችን በተመለከተ በይፋ የተረጋገጠ መረሃ ማግኘት ባይቻልም፤ እነዚህ ውሳኔዎች እውነተኛ ከሆኑ ግን ማርሽ ቀያሪ ውሳኔዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

በፈተናዎች ያልተበገረው ስኬት
ከአደጋ ወደ ዶክትሬት፤ የቸርነት ቡሳዋ የፅናት ጉዞ
#ethiopia | ሕይወት አንዳንድ ሰዎችን በፈተና ትሞክራለች፤ አንዳንዶች በፈተናው ይበገራሉ፣ ሌሎች ግን ከፈተናው በላይ በመቆም የስኬት ታሪካቸውን ይጽፋሉ። ቸርነት ቡሳዋ የዚህ እውነት ሕያው ምሳሌ ነው።
ከ30 ዓመታት በፊት በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት የአካል ጉዳተኛ የሆነው ቸርነት፣ ይህን ችግር እንደ መጨረሻ ሳይቆጥረው የትምህርትና የሙያ ጉዞውን በፅናት ቀጥሏል። በቅርቡም በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ የሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ከኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በማግኘት የረጅም ዓመታት ጥረቱን በስኬት አጠናቋል።
የፅናት ጉዞ
ቸርነት በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ለረጅም ጊዜ አገልግሏል። በነጌሌ ቦረና ከሰራ በኋላ ወደ ኦሮሚያ ፕላን ኮሚሽን ተዛውሯል። በትምህርት ጉዞው መካከል የሥራ ዝውውር፣ የቦታ ለውጥ እና የአስተዳደር መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም ግቡን አልተወም።
በአራት ዓመት ሊያጠናቅቀው የነበረው ትምህርት በአንድ ዓመት ቢራዘምም፣ በትዕግሥትና በጽናት አጠናቆ ለምረቃ በቅቷል።
ከስኬቱ ጀርባ የቆመው ድጋፍ
ቸርነት ለዚህ ደረጃ በመድረሱ በተለይ ባለቤቱ ሲስተር ኤልሳቤት ያደረገችለትን ድጋፍ በታላቅ ምስጋና ያስታውሳል። እንዲሁም ወንድሞቹን፣ ጓደኞቹን እና የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ለሰጡት ሞራላዊና ተግባራዊ ድጋፍ አመስግኗል።
የአራት ልጆች አባት የሆነው ቸርነት፣ ሁለት ልጆቹ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመማራቸው ኩራት እንደሚሰማው ይገልጻል። ቤተሰቡ የስኬቱ ዋነኛ መሠረት መሆኑንም ይናገራል።
"እውቀታችን ይታይ፤ ጉዳታችን አይፍረድብን"
ቸርነት ከግል ስኬቱ ባሻገር ለማኅበረሰብ የሚያስተላልፈው ጠንካራ መልዕክት አለው። ሕንጻዎችና የሕዝብ ተቋማት ሲገነቡ የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት ከግምት ማስገባት እንዳለባቸው ያሳስባል።
በተጨማሪም በቅጥርና በሥራ ዕድል ውድድር ወቅት የሰውን ብቃት፣ እውቀትና ችሎታ እንጂ የአካል ጉዳት ሁኔታውን መመዘኛ ማድረግ እንደሌለበት በጽኑ ያምናል።
"እንደማንኛውም ዜጋ ተወዳድረን ካሸነፍን ዕድሉን ማግኘት አለብን" የሚለው መልዕክቱ፣ እኩል ዕድልና ፍትሃዊ ተወዳዳሪነትን የሚጠይቅ ነው።
የተስፋ ምልክት
የቸርነት ቡሳዋ ታሪክ የአንድ ሰው የትምህርት ስኬት ብቻ አይደለም። የፅናት፣ የቤተሰብ ድጋፍ፣ የትጋት እና የተስፋ ታሪክ ነው።
ፈተናዎች ሕልምን ሊያዘገዩ ይችላሉ፤ ግን ፅናት ካለ ሊያቆሙት አይችሉም። ቸርነት ቡሳዋ ይህንን እውነት በሕይወቱ አረጋግጧል። ዛሬ የዶክትሬት ዲግሪው የግል ስኬቱ ብቻ ሳይሆን፣ ለብዙ ወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለማንኛውም በፈተና ውስጥ ላለ ሰው "አትተው፤ ቀጥል" የሚል ሕያው መልዕክት ሆኗል።

የገጠሯን ቤተክርስቲያን እንርዳ
ለጊጪ ቡቢሳ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እንድረስላት !!!
✝️ ከአዲስ አበባ በ120ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ቤተክርስቲያን በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤ/ክ ስር ይገኛል።
✝️ ይሁንና በዚህ ሰዓት ግድግዳው በሙሉ በምስጥ እየተበላ ቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ አደጋ ላይ በመውደቁ ታቦቱ ወጥቶ በመቃብር ቤት ውስጥ ይገኛል።
✝️ በሀገር ውስጥም በውጪ ሀገራትም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንና የቅድስት ኪዳነ ምህረት ወዳጆች ተባብረን ቤተክርስቲያኑን እንጨርሰው።
✝️ የገዳሙ የባንክ አካውንት
1000742370527 - ኢ.ን. ባ /CBE/
✝️ ለበለጠ መረጃ በ +251948576116 ይደውሉ
በዚህ ጥሪ ላይ በመሳተፍ የበረከት ተካፋይ እንሁን። የቅድስት ኪዳነምህረት አማላጅነት አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንዲት_ጥምቀት #ቅዱሳን #ተዋህዶ #ድንግል #orthodoxchurch #ኢትዮጵያ
Sponsored by
Surafel
1 month ago
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-
✅ ከጠዋቱ 4፡00-ቀኑ 9፡30
👉 ሜክስኮ፣ ብሔራዊ ፣ ሰንጋተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ኩባ ፓርክ፣ ተ/ሃይማኖት፣ በርበሬ በረንዳ፣ ዲአፍሪካ እና አካባቢያቸው ፣
✅ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00
👉ጎፋ ካምፕ፣ ጀርመን አደባባይ፣መከኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ላፍቶ፣ ቄራ፣ቆሼ፣ ዘነበወርቅ፣ጎፋ እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉ሸገር ዳቦ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ለገ ጣፎ ከተማ ፣ የካሰዴ፣የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ወሰን ግሮሰሪ፣ ሲኤምሲ ሚካኤል፣ ካራሎ፣ለገጣፎ፣ ሲዲሲ ፣ ኮሰሮ፣ ለገዳዲ፣ ሰንዳፋ፣ 44 ማዞሪያ፣ ሲሬ ጎዩ፣ የካ ሰዴ፣ድሬ ሰኩር እና አካባቢያቸው፣
👉 ጁኒፐር ግላስ፣ ደጋ ውሃ፣ ቻንግልዶንግራን፣ ፊበላ፣ ቦልት ማልት፣ ሃዋ ትሬዲንግ፣ ብራውን ፉድ ፣ ማማ ዱኬት ፋብሪካዎች እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከለሊቱ 6፡00-ቀኑ 6፡00
👉 ድሬደዋ ውሃ፣ ፓይነር ሲሚንቶ፣ ቱሬ ሲሚንቶ፣ ሀረር ውሃ፣ ማረሚያ፣ ኩርቱ፣ በለዋ፣ ቃልቻ፣ ቢሻን በሄ፣ ሃሎብሳ፣ ለጎዳ፣ አሳሊሶ፣ ኢንዱስትሪ ኮንዶሚኒየም፣ ሻሎም ኢንጂነሪንግ፣ መልካ፣የኢንዱስትሪ እና አካባቢያቸው፣
✅ ከጠዋቱ 1፡30-5፡00
👉አዳማ ከወንጂ ቀበሌ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋት 12፡00-12፡00
👉በአሰላ፣ አዳሚቱሉ፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ እና አካባቢው
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ውድ ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ዛሬ ሊካሄድ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረው የአዳማ ከተማ እና የወላይታ ድቻ የሊግ ጨዋታ፣ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሜዳው በውሃ በመሙላቱ ሳይካሄድ ቀርቷል።
የስታዲየሙ የመጫወቻ ሜዳ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመቋጠሩ ምክንያት ጨዋታውን በተያዘለት ሰዓት ማስጀመር አልተቻለም።
ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እና ሜዳውን ለጨዋታ ዝግጁ ለማድረግ፣ ውሃ የሚያስወግድ ማሽን እስኪመጣ ድረስ ጨዋታው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዘግይቶ የነበረ ቢሆንም ጥረቱ ሊሳካ አልቻለም። የሜዳው ሁኔታ ተጫዋቾችን ለጉዳት ሊያጋልጥ የሚችል እና መደበኛ የጨዋታ እንቅስቃሴን የሚከለክል ሆኖ በመገኘቱ፣ ዛሬ ሊካሄድ የነበረው ይህ መርሃ ግብር ወደ ነገ ጠዋት 4፡00 ሰዓት እንዲራዘም የጨዋታው አዘጋጆች ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የነገሌ አርሲን የማሸነፊያ ግቦች በረከት ወልዴ (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ሀቢብ ከማል አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ መደረግ በጀመረው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 እየመራ ይገኛል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የመሪነት ግብ ፍፁም ጥላሁን አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይገናኛሉ፡፡

ማስታወቂያ
👌 ለየትኛውም አይነት ሜዳ አስተማማኝ ማሊያ! 👌
👇👇 የት አገኛለው ካሉ 👇👇
አድራሻ (አዲስ አበባ) :- 🏬 አዲስ አበባ ከትንሿ ስታዲየም አጠገብ አን ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
አድራሻ (ድሬዳዋ) :- 🏬 ድሬዳዋ ስታዲየም የመሸጫ ስፍራ ምድር ቤት
አድራሻ (አዳማ) :- 🏬 የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት የሚገኘው ካናብ ሞል 1ኛ ፎቅ
አድራሻ (ባህር ዳር ) :- 🏬 ቀበሌ 4 ጊዮርጊስ ህንፃ ፊት ለፊት ወደብ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
አድራሻ (ሆሳዕና) :- 🏬 ሀዲያ ዞን ፋይናንስ ጵ/ቤት ፊት ለፊት ሴች ዱና ሞል
ለመረጃና ለትዕዛዝ (አዲስ አበባ) :-📱0900006363
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ድሬዳዋ) :-📱0955495959
ለመረጃና ለትዕዛዝ (አዳማ) :-📱0951008686
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ባህርዳር) :-📱0918004342
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ሆሳዕና) :-📱0946555577
goferesportswear
👌 ለየትኛውም አይነት ሜዳ አስተማማኝ ማሊያ! 👌
👇👇 የት አገኛለው ካሉ 👇👇
አድራሻ (አዲስ አበባ) :- 🏬 አዲስ አበባ ከትንሿ ስታዲየም አጠገብ አን ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ
አድራሻ (ድሬዳዋ) :- 🏬 ድሬዳዋ ስታዲየም የመሸጫ ስፍራ ምድር ቤት
አድራሻ (አዳማ) :- 🏬 የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት የሚገኘው ካናብ ሞል 1ኛ ፎቅ
አድራሻ (ባህር ዳር ) :- 🏬 ቀበሌ 4 ጊዮርጊስ ህንፃ ፊት ለፊት ወደብ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
አድራሻ (ሆሳዕና) :- 🏬 ሀዲያ ዞን ፋይናንስ ጵ/ቤት ፊት ለፊት ሴች ዱና ሞል
ለመረጃና ለትዕዛዝ (አዲስ አበባ) :-📱0900006363
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ድሬዳዋ) :-📱0955495959
ለመረጃና ለትዕዛዝ (አዳማ) :-📱0951008686
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ባህርዳር) :-📱0918004342
ለመረጃና ለትዕዛዝ (ሆሳዕና) :-📱0946555577
goferesportswear
1 month ago
የገጠሯን ቤተክርስቲያን እንርዳ
ለጊጪ ቡቢሳ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እንድረስላት !!!
✝️ ከአዲስ አበባ በ120ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ቤተክርስቲያን በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤ/ክ ስር ይገኛል።
✝️ ይሁንና በዚህ ሰዓት ግድግዳው በሙሉ በምስጥ እየተበላ ቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ አደጋ ላይ በመውደቁ ታቦቱ ወጥቶ በመቃብር ቤት ውስጥ ይገኛል።
✝️ በሀገር ውስጥም በውጪ ሀገራትም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንና የቅድስት ኪዳነ ምህረት ወዳጆች ተባብረን ቤተክርስቲያኑን እንጨርሰው።
✝️ የገዳሙ የባንክ አካውንት
1000742370527 - ኢ.ን. ባ /CBE/
✝️ ለበለጠ መረጃ በ +251948576116 ይደውሉ
በዚህ ጥሪ ላይ በመሳተፍ የበረከት ተካፋይ እንሁን። የቅድስት ኪዳነምህረት አማላጅነት አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንዲት_ጥምቀት #ቅዱሳን #ተዋህዶ #ድንግል #orthodoxchurch #ኢትዮጵያ
1 month ago
ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ጣልቃገብነት ተላቀው ...
#ethiopia | የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፖለቲካ ጣልቃገብነት ተላቀው ነጻ የእውቀትና የሃሳብ ማፍለቂያ እንዲሆኑ የሚያስችል የሪፎርም ስራ እየተከናወነ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው መድረክ ላይ እንደተብራራው፣ የዚህ ታሪካዊ ሽግግር ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ-ገዝነት በማሸጋገር ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኛ የሆኑ፣ ሀገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ ዜጎችን ማፍራት ነው።
ለዚህም ስኬት ተቋማቱ በዘላቂ የውስጥ ገቢ ማስገኛ መንገዶች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩና የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲያጠናክሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህን የራስ-ገዝነት ዝግጁነት በውል ለመገምገም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 9 ገለልተኛ የባለሙያ ቡድኖችን በ9 ተለይተው በታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ አሰማርቶ ጥናታዊ ምልከታ አድርጓል።
በዚህ ታሪካዊ የዝግጁነት ግምገማ ውስጥ የተካተቱት የጅማ፣ የሀዋሳ፣ የአርባ ምንጭ፣ የሐረማያ፣ የጎንደር፣ የባህርዳር፣ የመቀሌ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ፣ በቀጣይም ግኝቶቹን መሰረት በማድረግ በማስረጃና በሀገራዊ ሃላፊነት ላይ የተደገፉ የሽግግር ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ከት/ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
#ethiopia #educationreform #highereducation #universityautonomy #moe #ethiopianuniversities

የ18 ሚሊዮን ብር የፒካፕ ተሽከርካሪን አካል በትነው ለመሸጥ የሞከሩ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ ፖሊስ፣ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ በተደረገ የተቀናጀና ስኬታማ ክትትል፤ በአሽከርካሪነት የተቀጠረበትን የኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረት የሰረቀ ግለሰብ ከስድስት ግብረ-አበሮቹ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
አበራ መረሳ የተባለው ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 (ልዩ ቦታው አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ) በሚገኝ አንድ የግል የኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም የድርጅቱን ንብረት በመሰወር ወንጀሉን ፈጽሟል።
ግምቱ 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 48405 HILUX የሆነ ዘመናዊ የፒካፕ ተሽከርካሪ ነው።
ዋናው ተጠርጣሪ ከተባባሪዎቹ (ወንዶሠን አባተ፣ ሶይብ ሙኒር፣ ክንዱ ደጉ፣ ስንታየሁ ተመስገን፣ ብሩክ ግርማ እና ባህሉ ሲሳይ) ጋር በመሆን ተሽከርካሪውን ከአዲስ አበባ በመውሰድ በአዳማ ከተማ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ደብቀውታል።
እዚያም የተሽከርካሪውን አካል ሙሉ በሙሉ በመበታተን፣ ለአንድ ግለሰብ በ600 ሺህ ብር ለመሸጥ ተስማምተው የ110 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (ቀብድ) ተቀብለው እንደነበር በምርመራ ታውቋል።
የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ድርጊቱን በቅርብ ክትትል ሲያጣራ ቆይቶ፤ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከፌዴራልና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር ባደረገው የጋራ ኦፕሬሽን ሰባቱንም ተጠርጣሪዎች ከተበታተነው የተሽከርካሪ አካል (ኤግዚቢት) ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀሉን መፈጸም ተከትሎ ለድርጅቶችና ለአሰሪዎች የሚከተለውን ማሳሰቢያ አስተላልፏል፦
"ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ሠራተኞችን አሽከርካሪዎችን በሚቀጥርበት ወቅት፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ የሠራተኞቻቸውን ማንነትና ታማኝነት የሚያረጋግጡ አስፈላጊ ህጋዊ ሰነዶችን በአግባቡ አሟልተው መያዝ ይኖርባቸዋል።"
Via የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ#ጉርሻ Page

ለከባድና ቀላል ጭነት መኪና ባለቤቶች: የጂፒኤስ መከታተያ ሥርዓት ቁልፍ ጥቅሞች 🚚📍
የጭነት መኪና ባለቤትነት፣ የከባድም ሆነ የቀላል ጭነት፣ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው። እነዚህ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የጀርባ አጥንት ሲሆኑ፣ የእነሱን እንቅስቃሴ በአግባቡ መቆጣጠር ለሥራው ስኬት ወሳኝ ነው።
በኢትዮጵያ በተለይ የነዳጅ ወጪ መናር፣ የመንገድ ሁኔታዎች እና የሎጂስቲክስ አስተዳደር የራሳቸው የሆኑ ፈተናዎች ሲሆኑ፣ የተሽከርካሪ ጂፒኤስ መከታተያ ሥርዓት ለእነዚህ ችግሮች ውጤታማ መፍትሄዎችን ይሰጣል።
ታዲያ የጂፒኤስ መከታተያ ሥርዓት ለከባድና ቀላል ጭነት መኪና ባለቤቶች የሚሰጣቸው ዋና ዋና ጥቅሞች ምንድን ናቸው? በአጭሩ እነሆ፦
የጭነት መኪናዎ ደህንነት እና ቅልጥፍና ያሳስብዎታል? ጂፒኤስ መከታተያ ዘመናዊ መፍትሄ ነው!
• ተሽከርካሪ ደህንነት 🔒: መኪናዎ የት እንዳለ በቅጽበት ይወቁ! ስርቆትን ለመከላከል እና ከተሰረቀ በፍጥነት ለማግኘት ይረዳል።
• ወጪ ቅነሳ 💰: የነዳጅ ፍጆታን ይቆጣጠሩ፣ አላስፈላጊ ወጪን ይቀንሱ። ትክክለኛውን መንገድ በመምረጥ ነዳጅ ይቆጥባሉ! ⛽
• የሥራ ቅልጥፍና 🚀: እያንዳንዱ መኪና የት እንዳለ በማወቅ ሥራዎችን በቀላሉ ያቀናብሩ። ለደንበኞችም ትክክለኛ መረጃ ይስጡ።
• አሽከርካሪ አስተዳደር 👨✈️: የአሽከርካሪዎችን የአነዳድ ዘይቤ እና የሥራ ሰዓት ይቆጣጠሩ። ደህንነትን ይጨምራል፣ ጉዳትን ይቀንሳል።
• የጥገና አስተዳደር 🛠️: የጥገና ጊዜን በማቀድ ድንገተኛ ብልሽቶችን ይቀንሱ።
በአጭሩ፣ ጂፒኤስ መከታተያ የንብረትዎን ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ወጪ ለመቆጠብ፣ ቅልጥፍናን ለማሳደግ እና የአሽከርካሪዎችን ደህንነት ለመከታተል ወሳኝ ኢንቨስትመንት ነው! 💪
ሳሚ አውቶሞቲቭ - አስተማማኝ የመኪና ደህንነትዎ! 🛡️
🛠️ ይህን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማስገጠም እና ለበለጠ መረጃ አሁኑኑ ይደውሉልን! 📞
📲 ስልክ ቁጥሮች:
• 0912072874
• 0947329334
• 0913917373
• 0906015555
• 0906065151 (አዳማ)
• 0948110505 (ድሬዳዋ ቢሮ)
• +25111470 5763 (የደንበኞች አገልግሎት)
1 month ago
ከሚሰራበት ድርጅት ውስጥ ተሽከርካሪ በመሰወርና አካሉ እንዲበተን ያደረገ ግለሰብ ከስድስት ግብረ አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ።
አበራ መረሳ የተባለው ተጠርጣሪ ወንጀሉን የፈፀመው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ስታዲየም አካባቢ ከሚገኝ አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት ነው፡፡
ተጠርጣሪው ወንዶሠን አባተ፣ ሶይብ ሙኒር፣ ክንዱ ደጉ፣ ስንታየሁ ተመስገንን፣ ብሩክ ግርማ፣ ባህሉ ሲሳይ ከተባሉ አባሪዎቹ ጋር በመመሳጠር ግምቱ 18 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 48 4 05 HILUX ፒካፕ ተሽከርካሪን ከድርጅቱ ይዞ በመውጣት ከአንድ ግለሰብ ጋር በ 6መቶ ሺ ብር ለመሸጥ ተስማምቷል።
ግለሰቡ ቀደም ብሎ የሽያጩን ቀብድ 110 ሺህ ብር በመቀበልና ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን አዳማ ከተማ ላይ የተሽከርካሪውን አካል በመነቃቃልና በመበታተን በአንድ መጋዘን ውስጥ አስቀምጧል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን ሲያጣራ የነበረው በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከሀገር መከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ከአዳማ ከተማ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ በአጠቃላይ 7 ተጠርጣሪዎችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሊያውልም ችሏል፡፡
የመንግስትም ሆና የግል ድርጅቶች ሠራተኞችን ሲቀጥሩ የሠራተኞቻቸውን ማንነት የሚገልጽ አስፈላጊ ሠነዶች አሟልተው መሆን እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
አበራ መረሳ የተባለው ተጠርጣሪ ወንጀሉን የፈፀመው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ስታዲየም አካባቢ ከሚገኝ አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት ነው፡፡
ተጠርጣሪው ወንዶሠን አባተ፣ ሶይብ ሙኒር፣ ክንዱ ደጉ፣ ስንታየሁ ተመስገንን፣ ብሩክ ግርማ፣ ባህሉ ሲሳይ ከተባሉ አባሪዎቹ ጋር በመመሳጠር ግምቱ 18 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 48 4 05 HILUX ፒካፕ ተሽከርካሪን ከድርጅቱ ይዞ በመውጣት ከአንድ ግለሰብ ጋር በ 6መቶ ሺ ብር ለመሸጥ ተስማምቷል።
ግለሰቡ ቀደም ብሎ የሽያጩን ቀብድ 110 ሺህ ብር በመቀበልና ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን አዳማ ከተማ ላይ የተሽከርካሪውን አካል በመነቃቃልና በመበታተን በአንድ መጋዘን ውስጥ አስቀምጧል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን ሲያጣራ የነበረው በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከሀገር መከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ከአዳማ ከተማ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ በአጠቃላይ 7 ተጠርጣሪዎችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሊያውልም ችሏል፡፡
የመንግስትም ሆና የግል ድርጅቶች ሠራተኞችን ሲቀጥሩ የሠራተኞቻቸውን ማንነት የሚገልጽ አስፈላጊ ሠነዶች አሟልተው መሆን እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
1 month ago
የገጠሯን ቤተክርስቲያን እንርዳ
ለጊጪ ቡቢሳ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እንድረስላት !!!
✝️ ከአዲስ አበባ በ120ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ቤተክርስቲያን በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤ/ክ ስር ይገኛል።
✝️ ይሁንና በዚህ ሰዓት ግድግዳው በሙሉ በምስጥ እየተበላ ቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ አደጋ ላይ በመውደቁ ታቦቱ ወጥቶ በመቃብር ቤት ውስጥ ይገኛል።
✝️ በሀገር ውስጥም በውጪ ሀገራትም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንና የቅድስት ኪዳነ ምህረት ወዳጆች ተባብረን ቤተክርስቲያኑን እንጨርሰው።
✝️ የገዳሙ የባንክ አካውንት
1000742370527 - ኢ.ን. ባ /CBE/
✝️ ለበለጠ መረጃ በ +251948576116 ይደውሉ
በዚህ ጥሪ ላይ በመሳተፍ የበረከት ተካፋይ እንሁን። የቅድስት ኪዳነምህረት አማላጅነት አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንዲት_ጥምቀት #ቅዱሳን #ተዋህዶ #ድንግል #orthodoxchurch #ኢትዮጵያ
2 months ago
ጠንክረው ከሰሩ የማይሳካ ነገር የለም - ከ60 ኮርሶች 47ቱን 'A+' ያስመዘገበችው ተመራቂ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀሰምኩት እውቀት በቀጣይ ተጨባጭ ሥራ ለመስራት ተዘጋጅቻለሁ አለች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከ60 ኮርሶች 47 'A+' እና 13 'A' በማስመዝገብ የተመረቀችው መሐንዲስ ሩት አባተ፡፡
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ1 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።
ከነዚህም መካከል የኤሌክትሪካል ፓወር ኤንድ ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ ተመራቂዋ ሩት አባተ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
በከፍተኛ ውጤት የተመረቀችው ሩት ይህንን ስኬት ልታስመዘግብ የቻለችው ከመጀመሪያው ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ጀምሮ በትምህርቷ ላይ ሙሉ ትኩረት በማድረግ ጠንክራ በማጥናቷ መሆኑን ተናግራለች።
“ሙያው ለሴቶች ፈታኝ እንደሆነ ቢነገርም፤ እኔ ግን ይህንን አመለካከት በመስበር ለሌሎች ሴቶች አርአያ መሆን እንደምችል በተግባር ማሳየት ችያለሁ” ትላለች።
ላስመዘገበችው ስኬት ሁልጊዜ ከጎኗ በመሆን በሁሉም ረገድ ድጋፍ ለሚያደርጉላት ቤተሰቦቿ ምስጋና አቅርባለች።
መሐንዲስ ሩት በቀጣይ ትምህርቷን በማጠናከር የማስተርስ ዲግሪዋን የመቀጠል ትልቅ እቅድ እንዳላት ተናግራለች።
በትምህርት ገበታ ላይ የቀሰመችውን እውቀት በተግባር ወደ መሬት በማውረድ የሚታይና ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጻለች።
በሶስና አለማየሁ

ከ60 ኮርሶች 47ቱን 'A+' ያስመዘገበችው ባለብሩህ ተስፋዋ ባለዋንጫ መሃንዲስ ሩት አባተ
#ethiopia | ዛሬ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ካስመረቃቸው 1 ሺህ 387 ተማሪዎች መካከል፣ የአንድ ሴት እጩ የመጪው ዘመን መሃንዲስ ስም በልዩ ክብርና በታላቅ ጭብጨባ አዳራሹን አናውጦታል።
ይህ ስም የሩት አባተ ነው። ሩት በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ያስመዘገበችው እጅግ አስደናቂ ውጤት የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጓታል።
የኤሌክትሪካል ፓወር ኤንድ ኮንትሮል ኢንጅነሪንግ (Electrical Power and Control Engineering) ተማሪዋ ሩት አባተ፣ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 60 ኮርሶች መካከል 47ቱን 'A+' እንዲሁም የቀሩትን 13 ኮርሶች 'A' በማምጣት ሙሉ 4.00 (አራት ነጥብ) ውጤት አምጥታለች።
በዚህም በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ (Very Great Distinction) በመመረቅ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ መሆን ችላለች።
ተወልዳ ባደገችባት አዳማ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀችው ሩት፣ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት የበቃችው ከቅድመ መደበኛ መሰረቷ ጀምሮ ባደረገችው ተከታታይ ጥረት መሆኑን ትገልጻለች።
“የአዳማ ልጅ ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ነው የተማርኩት፤ ሁሌም የደረጃ ተማሪ ነበርኩ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በትጋት እያጠናሁና እየሰራሁ ስለመጣሁ አቅሜን እያዳበርኩ እዚህ መድረስ ችያለሁ።
ዩኒቨርሲቲ ስገባም ከመጀመሪያ ዓመት ጀምሮ ለትምህርቴ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ራሴን ለፈተናዎች በአግባቡ በማዘጋጀቴ የላቀ ውጤት አምጥቻለሁ፤ ለዚህም ፈጣሪን አመሰግናለሁ” ስትል ሩት የስኬቷን ሚስጥር ታጋራለች።
ይህን ታላቅ ውጤት ስታስመዘግብ ሁሌም አብረዋት የነበሩትን የቤተሰቦቿን ውለታ በኩራት ታነሳለች። ምንም ዓይነት ትኩረቷን የሚሰርቅ ነገር እንዳይገጥማት ቤተሰቦቿ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዳደረጉላት ትናገራለች።
“ቤተሰቦቼ ሁሌም ከጎኔ ሆነው እንድበረታ አድርገውኛል።
ምንም ነገር ከትምህርቴ እንዳያዘናጋኝ በመምከርና በመደገፍ አብረውኝ የስኬቴ ተጋሪ ሆነዋል። እኔም ጥረታቸውን ከንቱ አላደረግኩም፤ አላሳፈርኳቸውም" ስትል በምስጋና ትገልጻለች።
ሴቶች የትኛውንም ማህበራዊና አካባቢያዊ ጫናዎች አልፈው ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ የምትመሰክረው ሩት፣ ይህ ውጤቷ ለሌሎች እህቶቿ ትልቅ ማበረታቻና አርአያ እንደሚሆን ታምናለች።
“እኛ ሴቶች የማንበብና የመማር ዕድል ካገኘን፣ የትኛውንም ዓይነት ማኅበራዊና አካባቢያዊ ጫናዎች አልፈን ለላቀ ስኬት መብቃት እንችላለን።
እኔም በቀጣይ የስኬታማ ሴቶች ህያው ምሳሌ ለመሆን ጠንክሬ እሰራለሁ።” ሩት በዚህ አሸናፊነቷ ብቻ ለመቆም አላሰበችም።
በቀጣይም በትምህርቷ ላይ ይበልጥ በመበርታት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቷን የመቀጠል እቅድ አላት።
ከሁሉም በላይ ግን የተማረችውን ትምህርት ለሀገሯ በተግባር ማዋል ትልቁ ህልሟ መሆኑን ትናገራለች።
"በኢነርጂውና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገሬ ጠቃሚና ችግር ፈቺ ባለሙያ ለመሆን እተጋለሁ" ስትል ጽኑ ምኞቷን ገልጻለች። ወጣቷ ባለዋንጫ መሃንዲስ ለዚህ ማዕረግ እንድትበቃ የረዷትን ፈጣሪዋን፣ ወላጆቿን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራኖቿንና ጓደኞቿን አመስግናለች።
ይህ የሩት ታሪክ የራሷ የትጋት ብቻ ሳይሆን የወላጆች የዕለት ተዕለት ክትትልና የጋራ ጥረት ውጤት ጭምር መሆኑን የእናቷ ምስክርነት ያረጋግጣል።
የሩት እናት ወይዘሮ አዜብ ሻውል፣ የመጀመሪያ ልጃቸው የዋንጫ ተሸላሚ ሆና መመረቋ በቤተሰቡ ውስጥ ልዩ ደስታና ኩራት መፍጠሩን ይናገራሉ።
“ሩት እድገቷ ከንባብ ተለይቶ አያውቅም፤ እጅግ ጥሩ ስነምግባር ያላት ልጅ ናት። ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ሁሌም አንደኛ እየወጣች ነው እዚህ የደረሰችው" በማለት እናቷ የልጃቸውን የልጅነት ትጋት ያስታውሳሉ።
በዩኒቨርሲቲም ቆይታዋ ሁልጊዜ ተሸላሚ መሆኗን በኩራት ያነሳሉ።
እናቷ አያይዘውም፣ የሩት አባት ሁሌም የቅርብ አማካሪና አስጠኝ በመሆን ለዚህ ውጤት ትልቅ እገዛ ማድረጉን ጠቅሰው፤ “ሩት ሀገሯን የምትጠቅም ልጅ ናት፤ ወደፊትም ከዚህ በላይ ትልቅ ደረጃ እንድትደርስ እመኛለሁ” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ሲዳማ ቡና ሻምፒዮንነቱን ለማረጋገጥ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በሲዳማ ቡና እና በነገሌ አርሲ መካከል ይደረጋል።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከዛሬው ጨዋታ አንድ ነጥብ የሚያገኝ ወይም ድል የሚያደርግ ከሆነ ቀሪ ሁለት መርሐ ግብሮች እያሉት ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።
በዚህም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን ይሆናል።
ተጋጣሚው ነገሌ አርሲ ጨዋታውን የሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚቆይ ይሆናል።
ሲዳማ ቡናም የሊጉ ሻምፒዮንነቱን ለማረጋገጥ ቀጣይ ጨዋታዎችን ለመጠበቅ ይገደዳል።
ሲዳማ ቡና ከዚህ ቀደም በ2002 እና በ2011 ዓ.ም የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ተቃርቦ ሳይሳካለት መቅረቱ ይታወሳል።
በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 10 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ።
ሲዳማ ቡና ሊጉን በ64 ነጥብ ሲመራ ነገሌ አርሲ በ56 ነጥብ ይከተላል።
አቤል ያለው እና ናትናኤል ዳንኤል በተመሳሳይ 14 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ እየመሩ ይገኛሉ።
ታምራት ኢያሱ በ12 እንዲሁም አዲስ ግደይ በ11 ግቦች ይከተላሉ።

ቦቆጂ፣ የዓለም አትሌቲክስ ማማ፤ የሻምፒዮኖች መፍለቂያ
#fastmereja I በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በቆጂን መዘንጋት የዓለምን የሩጫ ታሪክ እንደ መዘንጋት ይቆጠራል። በአርሲ ዞን፣ ሌሙ እና ቢልቢሎ ወረዳ የምትገኘው በቆጂ ከተማ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስሟ የሚታወቁትን አትሌቶች በማፍራት የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደረገች ታላቅ የጀግኖች ማዕከል ናት። በከተማዋ አምባሳደር በጋዜጠኛ አንዱዓለም ጌታቸው አማካኝነት የጎበኘናት ይህች ከተማ፣ ከሩጫ ሜዳ ባሻገር በባህሏ እና በልዩ አቀባበሏ ተወዳጅ መሆኗን አስመስክራለች።
ከአዲስ አበባ ተነስተን አዳማንና አሰላን አቋርጠን ወደ በቆጂ ስንገባ፣ ከተማዋ የምትቀበለን በልዩ አየር ነው። የቆላማው ትኩሳት በአርሲው ብርድ ተተክቶ፣ ንፋሱ እንደ አትሌቶቹ አቀባበል በጋለ ስሜት ይገጥመናል። የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀዳ ሲንቄዎች እና ከንቲባዋ በባህላዊው አቀባበል "አና ዱፉ" በማለት፣ ጋቢ አልብሰው የጀመሩልን አቀባበል፤ የህዝቡን እንግዳ ተቀባይነትና የክብር መገለጫ ነው። ከንቲባ በርሃኔ ነገሰ እንደገለጹት፣ በቆጂ ለኢትዮጵያ የምታበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ፣ ከተማዋን ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራበት ነው።
የበቆጂ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የዓለምን የሩጫ ታሪክ የቀየሩ ድንቅ አትሌቶች የተፈጠሩባት፣ የአሸናፊነት መንፈስ የሚነፍስባት የተቀደሰች ምድር ናት። ደራርቱ ቱሉ፣ እጅጋየሁ ዲባባ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ታሪኩ በቀለ፣ እንዲሁም ለሜቻ ግርማ... እነዚህ ስሞች በቆጂን በዓለም የሩጫ ካርታ ላይ ያኖሩ ናቸው። ትምህርት ቤቱ ዛሬም በናፍቆት የተሞላ ነው፤ "የቀድሞ ተማሪዎቼ የት ናችሁ? እኔ ያሳደኳችሁ፣ የኮረኮምኳችሁ የትላንት ልጆቼ፣ መጥታችሁ ጎብኙኝ" እያለ በናፍቆት ይጠባበቃል። ይህ ትምህርት ቤት የዕውቀት ማዕከልነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ የፈጠረው ፋይዳ ሊዘነጋ የማይችል ታሪካዊ ሃብት ነው።
በቆጂ የሩጫ ብቻ አይደለችም! በከተማዋ እየተካሄደ ያለው የቴኳንዶ ስፖርት እንቅስቃሴ ሌላው የሚያስደንቅ ገጽታ ነው። "ዲ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ" የተባለ ማዕከል፣ በማስተር ደለለኝ አመራር ስር በቆጂን የቴኳንዶ ሻምፒዮኖች መፍለቂያ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት፣ የከተማዋን ስፖርታዊ ብቃት ሁለገብነት ያሳያል። ወጣቶች በሩጫ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የትግል ስፖርቶችም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸው፣ የከተማዋን የስፖርት ስትራቴጂ ትክክለኛነት ያሳያል።
ሌላኛው ትኩረት የሚስብ የጉብኝታችን ክፍል የቦቆጂ ሆስፒታል ነው። ከ500 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን የጤና እፎይታን እየሰጠ የሚገኘው ይህ ሆስፒታል፣ ከህክምና አገልግሎቱ ባሻገር በውስጥ ግቢው እየተከናወኑ ያሉት የማስዋብ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው። ለህጻናት እና አዋቂዎች የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጡ መናፈሻዎች መገንባታቸው፣ ሆስፒታሉን የከተማዋ የውበት መገለጫ እና ማህበራዊ መስተጋብር የሚፈጠርበት ስፍራ አድርጎታል።
በርካታ አትሌቶችን ያፈራችው ቦቆጂ ስቴዲየም እና የመሮጫ ትራክ የላትም፣ ከታዳጊዎች እስከ አባቶች የህዝቡ ጉጉት ቦቆጂ ስታድየም ተሰርቶ ማየት ሲሆን ይህን የህዝቡ ጉጉት ተመልክተው በተቀናጀ ስራ የቦቆጂን ስታድየም ሰርተው አጠናቀው ለመመረቅ እንደምንሄድ ተስፋ አደርጋለሁ።
በቆጂ የታላቁ ሩጫን በስኬት እንዳስተናገደች ሁሉ፣ የከተማዋን የቱሪዝም አቅም ለመጠቀም እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው። በቀጣይ የቱሪስት ስፍራዎቿን፣ የተፈጥሮ ውበቷን እና ታሪካዊ መዳረሻዎቿን በጥናት በመለየት ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሰራ ተጠቁሟል። በቆጂ በአየርዋ፣ በታሪኳና በጀግኖቿ የምትወደድ ከተማ ናት፤ ገና ያልተነገረላት ብዙ ምስጢር ስላላት ወደፊት በድጋሜ ተመልሰን የምንጎበኛት ይሆናል።

Comments