ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የነገሌ አርሲን የማሸነፊያ ግቦች በረከት ወልዴ (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ሀቢብ ከማል አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ መደረግ በጀመረው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 እየመራ ይገኛል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የመሪነት ግብ ፍፁም ጥላሁን አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይገናኛሉ፡፡

1 month ago