"በነገራችን ላይ፣ ዛሬ፣ በትግራይ ውስጥ ከሚኖር ትግራዋይ በላይ፣ በሰላም ወጥቶ መግባት የሚችል፣ አፈሳ የማይካሄድበት፣ በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ አርባምንጭ፣ ሀዋሳ ያለ ትግራዋይ፣ ትግራይ ካለው ሰው በላይ ሰላም አለው። ትግራይ ካለው ሰው በላይ በሰላም ወጥቶ መግባት ይችላል። የሚያሳዝነው ይሄ ጉዳይ ግን ትግራይ ብቻ አይደለም። አማራ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች፣ 'ለአማራ ህዝብ ሰላም፣ ደህንነት፣ ጥቅም እንታገላለን' ብለው የሚሉ ሃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ካለው የአማራ ተወላጅ ይልቅ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ ያለው አማራ ሰላም አለው። እነዚህ እንታገላለን የሚሉ ሃይሎች ያሉበት አካባቢ የበለጠ ፍራቻ፣ የበለጠ ግድያ፣ የበለጠ ዘረፋና መታገዶች አሉ።
"ኦሮሚያ አካባቢ ለኦሮሞ እንታገላለን ብለው የሚመሉ፣ የሚገዘቱ ሃይሎች ከሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በላይ፣ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀስ፣ በሱማሌ የሚንቀሳቀስ፣ በአፋር የሚንቀሳቀስ ኦሮሞ የተሻለ ሰላም አለው። ዜጎች በገዛ ቀያቸው፣ መንደራቸው፣ በገዛ ልጆቻቸው እየታመሱ ይገኛሉ። ከቀያቸው ሸሽተው መኖር የተሻለ ሰላም የሚያገኙበት እየሆነ መጥቷል። ከህዝብ ተነጥሎ፣ ህዝብ አስለቅሶ፣ ህዝብ ዘርፎ፣ የሚደረግ ትግል ደግሞ የትም ማድረስ እንደማይችል ከታሪኮቻችን መማር የምንችል ይመስለኛል።
መንግስት አብዛኛውን ጉዳይ በትዕግስት የሚያየው፣ ወደ ግጭት የማይገባው፣ ለምንድነው ያላችሁ እንደሆነ፣ አላማ ቢስ ነው። አላማ የለውም። ይሄንን ግጭት ከፈጸምን በኋላ 'አሳካን' ብለን የምንናገረው አንዳች ቁምነገር የለም። በዚያም በዚህም ብንገል፣ ብንሞት ትርጉም የለውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ትግራይ አካባቢ ያለው የፖለቲካል አውድ የመጥረቢያ ፖለቲካ ሰለባ ነው ትግራዋይ እና ኢትዮጵያዊያን የሆኑት።"
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በፓርላማው ከተናገሩት

29 days ago