18 days ago
ወሳኙ የንግድ መስመር ቀይ ባህር !!
በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ ኃይሎች የሳውዲ አረቢያ መርከቦች የባሕር እንቅስቃሴ ላይ እገዳ አወጁ።
ቡድኑ እገዳውን ያወጀው ሳውዲ አረቢያ በየመን ላይ "ኢፍትሃዊና ጨቋኝ ከበባ እየጣለች ነው" በሚል ክስ ነው።
የቀይባሕር ዋነኛ መተላለፊያ ባብ አል-መንደብ ሰርጥ ለሳውዲ መርከቦች እንደሚዘጋ ሁቲዎች አስታውቀዋል።
ይህ ከ2022 ጀምሮ በተመድ ድጋፍ ሲቆይ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያዳክም እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።
እገዳው የመጣው በሁቲዎች ቁጥጥር ስር ባለው የሳና አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከተፈጸመ ጥቃት በኋላ ነው።
የየመን መንግሥት የኢራና አውሮፕላን እንዳያርፍ ለመከላከል " ጥቃቱን ፈጽሜያለሁ " ቢልም ፤ ሁቲዎች ግን ሳውዲን ተጠያቂ በማድረግ የሚሳይል ጥቃት ከፍተው አሁን ደግሞ የባሕር ላይ እንቅስቃሴ እገዳ አውጀዋል።
ባብ አል-መንደብ ሙሉ በሙሉ ከተዘጋ የዓለም የነዳጅ አቅርቦት እስከ 7 በመቶ ሊቀንስ፤ በቀይ ባሕር የሚካሄደውን የንግድ መጓጓዣ እና የኃይል አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ሊያውክ ይችላል።
የየመን ሁቲዎች የባሕር ላይ እንቅስቃሴ እገዳ በቀጠናው እየተባባሰ ካለው የጂኦፖለቲካ ውጥረት ጋር የተያያዘ መሆኑ እየተነገረ ነው።
ኢራን በመሠረተ ልማቶቿ ላይ ለሚፈጸመው የእነ አሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት ምላሽ እንዲሆን፣ ሁቲዎች የምዕራባውያንና የባሕረ ሰላጤ ሀገራት የመርከብ መጓጓዣ ወሳኝ መተላለፊያዎችን እንዲያውኩ ሁቲዎችን " ግፊት አድርጋባቸዋለች ም" ተብሏል።
Seledadotio

1 month ago
የመደመር አንቀጽ
የአፍሪካ ቀንድ ለመካከለኛው ምሥራቅ መካከለኛው ምሥራቅ ለአፍሪካ ቀንድ እጅግ አስፈላጊ አካባቢ ናቸው።
በታሪክም ሁለቱ አካባቢዎች በሕዝቦች እንቅስቃሴ፣ በንግድ፣ በወታደራዊ ንቅናቄ፣ በሃይማኖትና በባህል ሲገናኙ ኖረዋል።
አሁንም በሁለቱ አካባቢ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየሰፋና እየተጠናከረ መጥቷል።
ከዚህም በኋላ በሚኖሩ ትውልዶች ዘንድ፤ በሁለቱ አካባቢዎች ሀገራት መካካል የሚኖረው ግንኙነት፤ በአሉታም ይሁን በአዎንታ እጅግ የገዘፈ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
ይኽ ግንኙነት በብልሐት ከተያዘ ሊጠቅም የሚችል፤ እንዲሁም አያያዙ ከተበላሸ ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ሊያስከትል የሚችል ነው።
ስለዚህም ግንኙነቱ ሊፈጥረው ከሚችለው ዕድልም ይሁን አደጋ አንጻር፤ በነባራዊ እንዲሁም በቀጣይ ዘመናት በቀንዱ እጅግ ትኩረት ከሚፈልጉ ግንኙነቶች መካከል ነው።
የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የተፅዕኖ እንቅስቃሴና ደኅንነታቸውን ለማስጠበቅ ትኩረት ካደረጉባቸው አካባቢዎች ዓይናቸው በዋናነት ያረፈው፤ ወደ ሌላኛው የቀይባሕር ዳርቻ፤ የአፍሪካ ቀንድ ነው።
ይኽ ባሕርን ተሻግሮ ተፅዕኖን የማስፋት ፍላጎት አሁን የተጀመረ ሳይሆን፤ በየዘመኑ በሁለቱም ዳርቻ የነበሩ ሀገራት ትኩረት ያደረጉበት የዘመናት ስትራቴጂ ነው፡፡
ከጥንት ጀምሮ በቀይ ባሕር ሁለት ጫፍ ያሉ ሀገራት፤ ባሕርን ተሻገርው ሌላኛውን የቀይ ባሕር ወሰን ለመቆጣጠርና ግንኙነት ለመፍጠር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነበረ።
ይኸም በአንደኛው የቀይ ባሕር በኩል የሚፈጠር አደጋም ሆነ ዕድል፤ በሌላኛው የቀይባሕር በኩል ተፅዕኖ እንደሚያደርስ ከመገንዘብ የሚመነጭ ነው።
በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን፤ የእኛው ዐፄ ካሌብ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ደቡብ ዓረቢያን ለመቆጣጠር ችሎ ነበር።
ዓረቦች የአካባቢው ኃያላን ሆነው በተነሡበት ከ8ኛው እስከ 14ኛው መክዘ በነበረው ጊዜ፤ ቀይ ባሕርን ተሻግረው የአፍሪካን ቀንድ ለመያዝ ሞክረው ነበር።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 245/246

3 months ago
የመደመር አንቀጽ
የምንገኘው የዓለም ዋነኛ የንግድ ኮሪደር በሆነው ሥፍራ አካባቢ ነው። የቀይ ባሕር አካባቢ የምሥራቁንና የምዕራቡን ዓለም አገናኝ ወሽመጥ ነው። በመሆኑም የአፍሪካና እስያ መገናኛ ድልድይ ነን። ይህንን ግን ለዕድገታችን አላዋልነውም። እንደ ሲንጋፖር ያሉት ሀገራት አካባቢያቸው የሰጣቸውን ትሩፋት ተጠቅመው በልጽገዋል። አካባቢያቸው የሰጣቸውን ተጽዕኖ የመፍጠር ትሩፋት ለዕድገታቸው ግብአት ያደረጉ ሌሎችም በርካታ ሀገራት አሉ። ሀገራችን በአንጻሩ በአፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ለዕድገቷ ግብዐትነት በሚገባ አልተጠቀመችውም።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 53
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc #ቀይባሕር #የባሕርበር

4 months ago
''ቀይ ባሕር ቢታመስም ለኢትዮጵያ ጭነቶች ቅድሚያ እሰጣለሁ'' ጅቡቲ
#ethiopia | በቀይ ባሕርና በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ቀውስ በዓለም አቀፉ የንግድ መርከቦች ፍሰት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ጅቡቲ ለኢትዮጵያ የሚገቡ የጭነት ምርቶች ቀዳሚ ትኩረት እንደምትሰጥ አስታወቀች።
የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ ቀጠናዎች ባለሥልጣን ሰብሳቢ አቡበከር ዑመር ሃዲ ለካፒታል ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳረጋገጡት፣ በቀጠናው ባለው ግጭት ምክንያት ቀደም ሲል ወደ ዱባይ (ጀበል አሊ) ያመሩ የነበሩ በርካታ መርከቦች አሁን ላይ መዳረሻቸውን ወደ ጅቡቲ በመቀየር ላይ ይገኛሉ።
የወደቦች አቅም እና የመርከቦች ፍሰት
ይህ ድንገተኛ የመርከቦች ፍሰት መጨመር በወደቦች ላይ የሥራ ጫና እና መጨናነቅ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ቢኖርም፣ ጅቡቲ ያሏት ስድስት ዘመናዊና ጥልቅ የባሕር ወደቦች ይህንን ጫና የመቋቋም ሙሉ ብቃት እንዳላቸው ሰብሳቢው ገልጸዋል።
በመሬት ትራንስፖርት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን መጨናነቅ ለመቀነስም፣ ጭነቶችን ከመርከብ ወደ መርከብ የማሸጋገር (Transshipment) ስልት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተጠቁሟል።
ለኢትዮጵያ የተሰጠው "ልዩ መስመር"
የጅቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስትራቴጂካዊ የሆኑ ምርቶች በተለይም እንደ ማዳበሪያ ያሉ የግብርና ግብዓቶች ያለምንም መስተጓጎልና መዘግየት እንዲስተናገዱ ልዩ መመሪያ ማውረዱን አቶ አቡበከር አረጋግጠዋል።
ይህም የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ቢዋዥቅም የኢትዮጵያ የንግድ መስመር እንዳይስተጓጎል ለማድረግ ታስቦ የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
የጸጥታ ስጋትና የጅቡቲ አቋም
የየመኑ አንሳሩላህ (ሁቲ) አማፅያን በቀይ ባሕር ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የሚሰነዝሩትን ጥቃት በተመለከተ፣ ጅቡቲ የጥቃቱ ኢላማ እንደማትሆን ባለሥልጣኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት፦
* የጅቡቲ ወደቦች መገኛ ከባቢል መንደብ በስተደቡብ መሆኑ።
* ወደቦቹ በቀይ ባሕር መግቢያና በሕንድ ውቅያኖስ ደጃፍ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ከቀጥተኛ የጦርነት ቀጠና ነፃ መሆናቸውን ነው።
በአጠቃላይ፣ ጅቡቲ የቀጠናውን የጸጥታ ቀውስ ተቋቁማ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የወደብ አገልግሎት በታማኝነትና በቅድሚያ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ቅዳሜ_ገበያ #ኢትዮጵያ #ጅቡቲ #የቀይባሕር #ንግድ #ወደብ #logistics #ethiopia #djibouti #redsea

5 months ago
🌊 የቀይ ባሕር ማዕበል እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስጋት
#ethiopia | ኢትዮጵያ ካለፈችባቸው ተከታታይ የፈተና ሰንሰለቶች (ኮቪድ-19፣ የሰሜኑ ጦርነት እና የሩሲያ-ዩክሬን ግጭት) ሳታገግም፣ አሁን ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው የኢራን፣ የእስራኤልና የአሜሪካ ፍጥጫ ሌላኛው የኢኮኖሚ "ጦርነት" ሆኖ ደጅ ላይ ቆሟል።
ጽሁፍዎ የነካቸውን ዋና ዋና ስጋቶች እና መወሰድ ያለባቸውን የመፍትሔ አቅጣጫዎች እንደሚከተለው አጠቃልለነዋል፦
1. የኢኮኖሚ ደም ስር (ቡና) ላይ የሚጋረጥ አደጋ
* የገበያ መጥፋት፦ ከኢትዮጵያ የቡና ኤክስፖርት ውስጥ እስከ 40% የሚሆነው ወደ ሳውዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚላክ በመሆኑ፣ ቀጠናው በጦርነት ታውኮ ትራንስፖርትና ንግድ ከተቋረጠ የዶላር ገቢያችን ክፉኛ ይመታል፡፡
* የክፍያ ሚዛን መዛባት፦ ቡና በመጋዘን ሲታጎር የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ተባብሶ መሰረታዊ ሸቀጦችን (መድኃኒትና ግብዓቶች) ለማስገባት አዳጋች ይሆናል፡፡ የወርቅ ገቢ እንደ ማስታገሻ ቢታይም፣ የቡናን ያህል ሰፊውን አምራች ማህበረሰብ አይጠቅምም፡፡
2. የሆርሙዝ ወሽመጥ እና የነዳጅ/ማዳበሪያ ጣር
* የነዳጅ ዋጋ ንረት፦ የዓለም የነዳጅ ንግድ 20% የሚያልፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት፣ የነዳጅ ዋጋን ከአንድ በርሜል 150 ዶላር በላይ ሊያስመነጥቀው ይችላል፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ መሰል ነዳጅ አስመጪ ሀገራት ከባድ ሸክም ነው፡፡
* የግብርናው ስጋት፦ ማዳበሪያ ከነዳጅ ተረፈ ምርት (Natural Gas) የሚመረጥ በመሆኑ፣ የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር የማዳበሪያ ዋጋም ይንራል፡፡ ይህ ደግሞ የሀገሪቱን የህልውና መሰረት የሆነውን ግብርና እና የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ይጥላል፡፡
3. ከመንግስት የሚጠበቁ የ"አባትነት" እርምጃዎች
መንግስት ባለበት የበጀት ጥበት ውስጥ ሆኖ የሚከተሉትን ስልታዊ እርምጃዎች መውሰድ ይኖርበታል ተብሎ ይታመናል፦
| ቅድሚያ ለህልውና | ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የቅንጦት ግንባታዎችን (ህንፃዎች/ፓርኮች) ለጊዜው አቁሞ በጀቱን ለምግብና ነዳጅ ድጎማ ማዋል፡፡
| የትራንስፖርት ድጎማ | የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ ቢጨምርም፣ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ እንዳይጨምር ልዩ በጀት መድቦ ዘርፉን መደገፍ፡፡
| የማህበራዊ ዋስትና | በመሰረታዊ ሸቀጦች (ዘይት፣ ስኳር፣ ስንዴ) ላይ ያለውን ድጎማ በመጨመር ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ዜጋ ከዋጋ ግሽበት መታደግ፡፡
| ወጪ መቀነስ | የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቅንጦት ወጪዎችን (ተሸከርካሪዎች፣ ስብሰባዎች) በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ፡፡
ማጠቃለያ፦
ኢትዮጵያ ከኮቪድ እሳት፣ ከሰሜኑ ጦርነት ረመጥና ከዩክሬን በረዶ ተርፋ እዚህ ደርሳለች። አሁን የመጣው የቀይ ባሕር ማዕበል ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄን፣ የኢኮኖሚ ዲሲፕሊንን እና የወገን ደራሽነትን ይጠይቃል።
via ይስሃቅ አበበ
#ኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ #ቀይባሕር #የነዳጅዋጋ #የቡናንግድ #የመካከለኛውምስራቅውጥረት #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
Comments