የመደመር አንቀጽ
የአፍሪካ ቀንድ ለመካከለኛው ምሥራቅ መካከለኛው ምሥራቅ ለአፍሪካ ቀንድ እጅግ አስፈላጊ አካባቢ ናቸው።
በታሪክም ሁለቱ አካባቢዎች በሕዝቦች እንቅስቃሴ፣ በንግድ፣ በወታደራዊ ንቅናቄ፣ በሃይማኖትና በባህል ሲገናኙ ኖረዋል።
አሁንም በሁለቱ አካባቢ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየሰፋና እየተጠናከረ መጥቷል።
ከዚህም በኋላ በሚኖሩ ትውልዶች ዘንድ፤ በሁለቱ አካባቢዎች ሀገራት መካካል የሚኖረው ግንኙነት፤ በአሉታም ይሁን በአዎንታ እጅግ የገዘፈ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
ይኽ ግንኙነት በብልሐት ከተያዘ ሊጠቅም የሚችል፤ እንዲሁም አያያዙ ከተበላሸ ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ሊያስከትል የሚችል ነው።
ስለዚህም ግንኙነቱ ሊፈጥረው ከሚችለው ዕድልም ይሁን አደጋ አንጻር፤ በነባራዊ እንዲሁም በቀጣይ ዘመናት በቀንዱ እጅግ ትኩረት ከሚፈልጉ ግንኙነቶች መካከል ነው።
የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የተፅዕኖ እንቅስቃሴና ደኅንነታቸውን ለማስጠበቅ ትኩረት ካደረጉባቸው አካባቢዎች ዓይናቸው በዋናነት ያረፈው፤ ወደ ሌላኛው የቀይባሕር ዳርቻ፤ የአፍሪካ ቀንድ ነው።
ይኽ ባሕርን ተሻግሮ ተፅዕኖን የማስፋት ፍላጎት አሁን የተጀመረ ሳይሆን፤ በየዘመኑ በሁለቱም ዳርቻ የነበሩ ሀገራት ትኩረት ያደረጉበት የዘመናት ስትራቴጂ ነው፡፡
ከጥንት ጀምሮ በቀይ ባሕር ሁለት ጫፍ ያሉ ሀገራት፤ ባሕርን ተሻገርው ሌላኛውን የቀይ ባሕር ወሰን ለመቆጣጠርና ግንኙነት ለመፍጠር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነበረ።
ይኸም በአንደኛው የቀይ ባሕር በኩል የሚፈጠር አደጋም ሆነ ዕድል፤ በሌላኛው የቀይባሕር በኩል ተፅዕኖ እንደሚያደርስ ከመገንዘብ የሚመነጭ ነው።
በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን፤ የእኛው ዐፄ ካሌብ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ደቡብ ዓረቢያን ለመቆጣጠር ችሎ ነበር።
ዓረቦች የአካባቢው ኃያላን ሆነው በተነሡበት ከ8ኛው እስከ 14ኛው መክዘ በነበረው ጊዜ፤ ቀይ ባሕርን ተሻግረው የአፍሪካን ቀንድ ለመያዝ ሞክረው ነበር።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 245/246

1 month ago