2 months ago
የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ ሲጓጓዝ የተገኘ ተሽከርካሪ እስከ መወረስ የሚደርስ ቅጣት የሚስቀጣው አዋጅ ጸደቀ
#ethiopia | የሕዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው በ24ኛ መደበኛ ስብሰባው የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
አዋጁ የጸደቀው በሁለት ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምጽ ነው፡፡
"ማጓጓዣው የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ የተገኘ ከሆነ የተሽከርካሪው ባለቤት የገንዘብ ሚኒስቴር የሚያወጣው መመሪያ በሚወስነው መሰረት እንደነገሩ ክብደት እንዲሁም እንደጭነቱ መጠን በገንዘብ መቀጮ ወይም ማጓጓዣውን እስከመውረስ ሊያደርስ በሚችል ቅጣት ሊቀጣ ይችላል"ይላል ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ፡፡
አዋጁ እቃዎችን ለመደበቅ የሚያስችል አካል የተገጠመለት ተሽከርካሪ እና ሙሉ በሙሉ የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ ሲጓጓዝ የተገኘ ተሽከርካሪ እንዲወረስ ደንግጓል፡፡
አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ ኮንትሮባንድ የጫኑ የተሽከርካሪ ባለቤቶች የሚቀጡት የብር መጠን 100,000 ነበር ፡፡
ይህ የገንዘብ ቅጣት ዝቅተኛ ስለሆነ ችግርን ከመቀነስ ይልቅ ኮንትሮባንድ ንግዱ እንዲባባስ ማድረጉን በአዋጁ ተጠቅሷል፡፡
በተሸሻለው አዋጅ ግን መኪናው ወይንም ተሸከርካሪው ኮንቶሮባንድ ጭኖ ከተያዘ ሙሉ በሙሉ እንዲወረስ ያዛል ፡፡
በዙህም መሰረት ዕቃዎቹን ለመደበቅ እንዲያስችል ሆኖ የተሠራ፣ የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት ከሆነ ፣ማጓጓዣው የጫነው ዕቃ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ በሚወስነው መጠን የኮንትሮባንድ ዕቃ የሆነ እንደሆነ የዕቃው ግምታዊ ዋጋ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ማጓጓዣው ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል ይላል፡፡
በተጨማሪም ማጓጓዣው ከመወረሱ በፊት የማጓጓዣው ባለቤት ይህንኑ እንዲያውቀው ሊደረግ እና ማጓጓዣው ጥቅም ላይ ስለዋለበት ሁኔታ ማስረጃ እንዲያቀርብ እድል ሊሰጠው ይገባል ሲል ያክላል።
ይህም የኮንትሮባንድ ንግድን ለማስቀረት እና የዘርፉ ተሳታፊዎች ለመቀነስ እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡
ማሻሻያ አዋጁ አስተዳደራዊ መቀጫዎች በተመለከተ ደግሞ የተጣለባቸውን ግዴታ ያልተወጡ አጓጓዦች፤ በኮንትሮባንድ ንግድ ተሳታፊ የሆኑ የማጓጓዣ ባለቤቶች፤ የጉምሩክ ህግን የተላለፈ የመጋዘን ባለፈቃድ፤ በጌዜያዊነት ወደ አገር ያስገባውን እቃ የጊዜ ገደቡ ሲጠናቀቅ ያላስወጣ ሰው የሚኖርባቸው አስተዳደራዊ ቅጣት በአዋጁ ከፍ እንዲል ተደርጎ ተሻሽሏል።
ይግባኝ ለማቀረብ የሚከፈል ቀረጥ እና ታክስ አስመልክቶ አስመጪው ያመነውን ቀረጥ እና ታክስ ከፍሎ እና ልከፍል አይገባም የሚለውን ቀረጥ እና ታክስ 50 በመቶ አስይዞ ይግባኝ ማቀረብ እንዲችል ተሸሽሏል፡፡
በስራ ላይ ያለው የጉምሩክ አዋጅ ግን በጉምሩክ ኮሚሽን እንዲከፍል በተጠየቀው ቀረጥ እና ታክስ ያልተስማማ አስመጪ ለግብር ይግባኝ ኮሚሽን ይግባኝ ሊያቀርብ የሚችለው ቀረጥ እና ታክሱን ሙሉ በሙሉ ከከፈለ በኋላ እንድሆነ ይታወቃል፡፡
ይህ ድንጋጌ ሀገ-መንግስቱ ለዚጎች የተሰጠውን አቤቱታ የማቅረብ መብት የሚገድብ በመሆኑ ተሸሽሏል ይላል አዋጁ፡፡
ማሻሻያው ስለ አጓጓዥ ግዴታዎች እና ኮንትሮባንድ በማጓጓዝ ድርጊት ስለ መሳተፍ በተመለከተ ማንኛውም አጓጓዥ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ የመንገደኞች ወይም የጭነት መግለጫ ካላቀረበ፣ ከተፈቀደለት ሰው በስተቀር ሌላ ሰው ወደ ማጓጓዣው እንዲገባ ካደረገ ወይም ማጓጓዣው ከጉምሩክ ወደብ እንዲወጣ ከተወሰነ በኋላ ምክንያቱን ለጉምሩክ ሹም ሳያስረዳና ፈቃድ ሳያገኝ እንዲቆይ ካደረገ፤ ከ4,000 ብር ባላነሰ እና ከ10,000 ብር በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል ይላል፡፡
በማከልም ማንኛውም አጓጓዥ የጉምሩክ ወደብ በደረሰ ማጓጓዣ ላይ የጉምሩክ ሹም በሌለበት ዕቃ የጫነ፣ ያራገፈ ወይም ለመጫን ወይም ለማራገፍ ሙከራ ያደረገ እንደሆነ ከብር 15,000 በማያንስና ከብር 20,000 በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ ደንግጓል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ የተገኘው ማጓጓዣ ባለቤት በኮንትሮባንድ ወንጀል ተሳታፊ ሆኖ ከተገኘ የሚኖርበት የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ወንጀሉ እንዳይፈጸም ለማድረግ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ ካልወሰደ የኮንትሮባንድ እቃው መወረስ እንደተጠበቀ ሆኖ የተጫነውን የኮንትሮባድ ዕቃ ዋጋ አንድ መቶ ፐርሰንት ወይም ብር 200‚000 ከሁለቱ አነስተኛውን የገንዘብ መቀጫ ይቀጣል፡፡
የጭነት ማሸጊያን ወይም ኮንቴነርን በመክፈት የኮንትሮባንድ ዕቃን ቀላቅሎ ጭኖ የተገኘ ማጓጓዣ ባለቤት ዕቃው መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጓጓዣው ባለቤት ብር 500,000 የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

5 months ago
የአሜሪካ ዜግነት ላላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቅጣት ምህረት ተደረገ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ (Overstay) ለቆዩ የአሜሪካ ዜግነት ላላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቅጣት ምህረትና ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በኢሚግሬሽን ሕግ መሠረት የሚጣልባቸውን የገንዘብ መቀጫ ለመክፈል አቅም የሌላቸው ወገኖች ቅጣቱ እንዲነሳላቸው ሲያቀርቡ የነበረውን ተደጋጋሚ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ውሳኔው ተላልፏል።
የውሳኔው ዝርዝር ነጥቦች፡-
1. ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት፡ የነበረባቸው ቅጣት ሙሉ በሙሉ ተነስቶላቸዋል። ያለ ምንም ቅጣት በቀጥታ ወደ ሕጋዊ የቪዛ አሠራር እንዲገቡ ይደረጋል።
2. ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች፡ የነበረባቸው የቅጣት ገንዘብ በግማሽ (50%) ቅናሽ ተደርጎላቸዋል። ቀሪውን ግማሽ በመክፈል ወደ ሕጋዊ የቪዛ አሠራር መመለስ ይችላሉ።
ይህ የምህረት እና የቅጣት ቅናሽ ዕድል የሚቆየው ለ60 ቀናት ብቻ ሲሆን፣ የሚተገበረውም ከመጋቢት 15/2018 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 15/2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
ተጠቃሚዎች በዚህ የ60 ቀናት የጊዜ ገደብ ውስጥ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ አስፈላጊውን ሰነድ በማሟላት እንዲስተናገዱ ጥሪ ቀርቧል። ይህ ዕድል ለአንድ ጊዜ ብቻ የተሰጠ መሆኑን የገለጸው ተቋሙ፣ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በሚቀርቡ ግለሰቦች ላይ ግን የተለመደው የኢሚግሬሽን ሕግና ደንብ ተፈጻሚ እንደሚሆን አሳስቧል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

#fastmereja I የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በላይ (Overstay) ለቆዩ የአሜሪካ ዜግነት ላላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቅጣት ምህረትና ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች እና ተግዳሮቶቻቸው:- ችግርን በትክክል መለየት የመፍትሄው ግማሽ ነው እንዲሉ
- ክፍል ሁለት
በዶ/ር ጋሻው ዘርጋው አብዛ ለመሠረት ሚድያ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለቤትነት፣ በፊት ኮርነር ስፖርት ኮንሰልታሲ አስተባባሪነት እና በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የቡድን መሪነት፣ ከ90 በላይ የሚሆኑ የዘርፉን ባለድርሻ አካላት (ከፌዴሬሽንና ሊጉ አመራሮች ጀምሮ እስከ ተጫዋቾች፣ ደጋፊዎችና ጋዜጠኞች) በማሳተፍ ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ጥልቅ ጥናት መነሻ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦችን መሰረታዊ ችግሮች በክፍል አንድ ጽሁፍ መቅረቡ ይታወሳል።
ባለፈው ጽሁፍ ከጥናቱ ግኝቶች መካከል ሦስቱ አንኳር ተግዳሮቶች ቀርበዋል፤ እነሱም፦ ክለቦች የአካባቢያዊ መንግስታት (የፋይናንስ) ጥገኛ መሆናቸው ፣ የመንግስት እጅ በጉልህ የሚታይበት የአመራር አደረጃጀት ችግር እና የክለቦቹ ተቋማዊ ቁመና ደካማ መሆን ነበሩ። እነዚህ ሦስት አንኳር ነጥቦች የእግር ኳሳችንን መዋቅራዊ ስብራት እና የችግሩን ያሳዩን ናቸው። ይሁን እንጂ የጥናቱ ግኝቶች በእነዚህ ብቻ የተገደቡ አይደሉም።
በዛሬው የክፍል ሁለት ተከታታይ ፅሁፍ፣ ከጥናቱ የተገኙ ተጨማሪ ተግዳሮቶች ቀርበዋል። በመጀመሪያው ክፍል ሦስት ዋና ዋና ችግሮች የተዳሰሱ ሲሆን፣ የዛሬው ምልከታ የሚጀምረው በጥናቱ ከተለዩት የክለቦቻችን ማነቆዎች መካከል አራተኛው ከሆነው ተግዳሮት ነው።
የበጀት ዕቅድ እና አጠቃቀም ጉድለት
ክለቦች የበጀት ዕቅድ እጦት እና የበጀት አጠቃቀም ጉድለት እንዳለባቸው በተደረጉት ቃለመጠይቆች ጎልቶ የተነሳ ሌላው ነባራዊ እውነታ ነው። ክለቦች በጀታቸውን ከዓመት በላይ መተንባይ ባለመቻላቸው እና ልማታዊ ስራ ላይ ከመሰራት መገደባቸው የአገራችን እግር ኳስ ከሚኖርባቸው ነባራዊ ሁኔታዎች መካከል አንዱ መሆኑን በስፋት ተነግሯል። በርካታ የጥናቱ ተሳታፊዎች ተመክሮዋቸውን እንዳካፈሉት፣ ክለቦች በከንቲባ፣ በዞን አስተዳደር፣ ወይም በክልል አስተዳደር ይሁንታ በሚለቀቅ በጀት የሚተዳደሩ በመሆናቸው፣ ከአንድ አመት ያለፈ እቅድ ይዘው መቅረብ የሚችሉበት ቁመና ኖሯቸው አይስተዋሉም። በመሆኑም፣ የአመት በጀት ይዘው፣ ለቀጣዩ አመት ሊያሻግራቸው የሚችል ገንዘብን ለማሰባሰብ አስቀድመው የሚንቀሳቀሱበት አሰራርን ማደርጀት የእግር ኳሱ አመራር አካል ሃላፊነት እንደሚሆን እና ለዚህም በሞያው የሰለጠነ የሰው ሃይል ማደራጀት የግድ እንደሚል በአጽዕኖት ተጠቁሟል። በእኩሌታውም፣ አስቀድሞ ያልተያዘ እና በአግባቡ ያልተወጠነ የወጪ አይነት ሲተገበር ማየት የተለመደ መሆኑን የተወሰኑ ተሳታፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል። የጥናቱ ተሳታፊዎች በተደጋጋሚ ያጋሯቸው እንኳር ነጥቦች በጥቅሉ የሚከተሉት ናቸው፦ ከተጫዋቾች ክፍያ የዘለለ በጀት አለመቅረጽ፣ የፋይናንስ አቅምን ያላገናዘበ የክፍያ ስምምነት ውስጥ መግባት ፣ ዕቅድ ውስጥ የተካተቱ ክፍያዎች ላይ ውሳኔ የመስጠት ተነሳሽነት መጉደል፣ በጊዜያዊ ትኩሳቶች ተነሳስቶ እቅድ ውስጥ ያልተካተተ ክፍያ መፈጸም፣ እና በወቅቱ ክፍያዎችን አለመፈጸም የሚሉ ናቸው።
የበጀት ዕቅድ እጦትን በሚመለከት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የባለ ድርሻ አካላት መካከል የክለብ አስተዳዳሪዎች ቀዳሚ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን አስመልክቶ አንድ አስተዳዳሪ ያካፈሉት አተያየት የሌሎች ተሳታፊዎችን እይታ በሚያንፀባርቅ መልኩ ያስቀምጠዋል፦
"የእኛ ክለብ በጀት አይደለም ያለው፣ ድጎማ ነው። እኛ እቅድ አውጥተን ሰለሰጠን አይደልም ገንዘብ የሚመደብለን። እንደራሴዎቹ በሰብጀክቲቭ ዌዬ /መረጀ ላይ ባልተንተራሰ አሰራር/ ‘ይህ በጀት ይበቃችኋል’ ብለው የሚፈቅዱት። ከዛም፣ ያ የተፈቀደውም ገንዘብ በወቅቱ አይለቀቅም። 50 ሚሊዮን ቢፈቅድ፣ አሁን አስሩን ሰጥቶህ፣ የሚቀጥለው ምን ያህልና መቼ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሆነህ መናገር አትችልም" ብለዋል።
በተመሳሰለ መልኩ፣ ሌላ አስተዳደር ፣ የክለቦች የፋይናንስ አቅምን ያላገናዘበ የክፍያ ስምምነት ውስጥ መግባት እና ክፍያዎችን በወቅቱ አለመፈጸምን በምክንያትነት ይጠቅሳሉ። ዕቅድ ውስጥ የተካተቱ ክፍያዎች ላይ ውሳኔ የመስጠት ተነሳሽነት እንደሚጎድል ተመክሯቸው እንዳስተማራቸው ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል። በሃብት አጠቃቀም ዙሪያ ገንዘብ እንዴት፣ ለምን እና መቼ ማውጣት እንዳለባቸው የመወሰን እንከን በተደጋጋሚ እንደሚስተዋልባቸው ተጠቅሷል። ይህን በተመለከተ አንድ በአሰልጣኝነት ሞያ የተሰማሩ ተሳታፊ ያካፈሉት እይታ በርካቶች ያነሱትን ሃሳብ ጠቅለል አድርጎ ያመላክታል፦
"የክለቦች በጀት ከሆድ ያለፈ ሊሆን ይገባል፤ ማለትም ከደሞዝ፣ ሆቴል፣ እና ትራንስፖርት ወጪ አልፎ የልማት ስራ ላይ ሊውል ይገባል። የልምምድ ሜዳ፣ የማደሪያ ካምፕ መገንባት መጀመር አለባቸው። በዚህ በኩል፣ ወደ ክለቦች የሚመጡት ሰዎች የረጅም ጊዜ ራዕይ ያላቸው ናቸው ማለት ያስቸግራል። የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚኖረው ክለብ፣ ታዳጊዎች ላይ ይሰራል። እኛ አገር ግን የውጭ ተጫዋቾችን በከፍተኛ ክፍያ መቅጠር ይመረጣል። እነሱ ሲሄዱ ክለቦቹ ባዶ ይሆናሉ። ... በርካታ ስመ ገናና እና ተወርተው የጠፉ ከአስር በላይ ክለቦች ልጠቅስልህ እችላለሁ፦ የአየር መንገድ፣ አየር ሀይል፣ ኪራይ ቤቶች፣ ሙገር፣ ባቡር፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ብርሃነ ሰላም፣ ትራንስ፣ ሃረር ቢራ፣ ጉና፣ ዳሽን ቢራ፣ ወንጂ፣ መተሃራ፣ የተወሰኑት ናቸው። እኝህ ክለቦች የታጠፉበት አንዱ እና ዋነኛው ምክኒያት … የበጀት አጠቃቀም ጉድለት ተጽዕኖ ነው" ብለዋል።
ምክረ-ሃሳብ፦ ክለቦች ቢያንስ የሶስት ዓመት የበጀት እቅድ ነድፈው፣ ለክትትል እንዲያግዝ፣ በሚመለከትው የመንግስት አካል አጸድቀው ለሊጉ ሊያቀርቡ ይገባል። በየአመቱ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ለአዲስ ዓመት ውድድር ሲመዘገቡ፣ በሁሉም የቦርዱ አባሎቻቸው የተፈረመበት እና በአመራር አባላቱ የፀደቀ በጀት ለሊጉ ሊቀርብ ይገባል። እንደ አማራጭም፣ አስቀድመው የሚከፍሉትን ገንዘብ ባንክ ውስጥ መኖሩን የክለቡን የባንክ አካውንት የሚገልጽ ደብዳቤ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
የፋይናንስ አስተዳደር ግልጽነትና ተጠያቂነት
የፋይናንስ አስተዳደር ግልጽነትና ተጠያቂነት፣ የአገራችን ክለቦችን በሚመለከት በቀዳሚነት ከተነሱት ችግሮች መካከል አንዱ ነው። የጥናቱ ተሳታፊዎች፣ ክለቦች የተጫዋች ደሞዝ፣ የፊርማ ክፍያ፣ የቦነስ ክፍያ፣ የመሳሰሉ አከፋፈሎችን በሚመለከት ግልጽነት እና ተጠያቂነታቸው ሊፈተሽ እንደሚገባ በሰፊው አንስተውታል። እንደ በርካቶቹ እይታ፣ ለተጫዋቾች ዝውውር የሚከፈለው የክፍያ መጠን ከስፖርቱ እድገት ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ሆኖ አይታይም፡፡ በተዛመደም፣ አንዳንድ ክለቦች ከአላቸው የፋይናንስ አቅም በላይ ለማውጣት እንደሚነሳሱ እና ቃል እንደሚገቡ፣ ነገር ግን የውድድር ዘመኑ እየገፋ ሲሄድ ቃላቸውን ማከበር እንደሚፈታተናቸው ተሳታፊዎች አንስተዋል። በጥናቱ የተሳተፈ ጋዜጠኛ አንዳስቀመጠው፡
“ክለቦች እንዲፈርሱ ከሚያደርጉ ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፋይናንስ አስተዳደር ጉድለት ነው። በተለይ፣ ያልተመጣጠነ ወጪ፤ [በተለያዩ ዓመታት የተለያዩ] ክለቦች የፋይናንስ ቀውስ ሲያጋጥማቸው ማየት የተለመደ ነው፣ ይህን ለማስቀረት እንደ የገንዘብ ጨዋነት ደንብ (ፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ) የዝውውር ወጭን መቆጣጠር ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይ፣ ክለቦች የሚሰጣቸውን ገንዘብ በአግባቡ ለእግር ኳሱ እድገት እያዋሉ መሆኑን መቆጣጠር ጠቀሜታው ለ[እግር] ኳሱ ነው፤ ተጨማሪ ትርፍ እንደማግኘት ይሆናል” ብሏል
አብዛኞቹ የጥናቱ ተሳታፊዎች፣ ክለቦች በአመት ያገኙት የገንዘብ መጠን፣ ያወጡት መጠንና ለምን ወጭ እንዳደረጉት በትክክል በገለልተኛ አካል ኦዲት መደረግና የፋይናንስ አፈፃፀም ለሊጉ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ እይታቸውን አካፍለዋል። በዚህ ዙሪያ፣ የፋይናንስ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን በሚመለከት ክለቦች የባንክ አካውንታቸው፣ የገንዘብ አያያዛቸው፣ የሃብት አስተዳደራቸው፣ በተሳታፊዎቹ ዘንድ በተደጋጋሚ የተነሱ ትኩረት የሚሹ ነጥቦች ናቸው። ከባንክ አካውንት ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ እይታዎች የቀረቡ ሲሆን አንድ የክለብ አሰተዳደር ያጋሩት ምልከታ የብዙዎቹን ተሳታፊዋች አተያይ የሚያንፀባርቅ ነው፦
“በርካታ ክለቦች የራሳቸው የባንክ አካውንት የላቸውም። ለምሳሌ፣ የክለብ [ሃለመ] የባንክ አካውንት በከተማው የፋይናንስ መምሪያ ስር ነው። ነገር ግን ክለቡን ሄደህ የራሳችሁ ባንክ አካውንት አላቹህ ወይ ብለህ ብትጠይቅ አዎ ነው የሚሉህ፤ ይህ ሊፈተሽ የሚገባ ጉዳይ ነው። ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ዋነኛው መሰናክል የፋይናንስ አስተዳደር ችግር ነው።”
በተመሳሳይ የገንዘብ አያያዝን በሚመለከት በጥናቱ የተሳተፉ አንድ ዳኛ እንደገለፁት “የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር ግልጽነት ያስፈልገዋል። አበል፣ ደመወዝ፣ የሆቴል ወጭ፣ ኮሚሽኖች፣ ተጠያቂነት በሚያረጋግጥ የገንዘብ አጠቃቀም ደንብ መመራት አለባቸው”። የሃብት አስተዳደራቸውን አስመልክቶ የተሰጡ በርካታ አተያየቶችን ሌላ ዳኛ የጥናቱ ተሳታፊ ያካፈሉት እይታ የሚያንጸባረቅ ይሆናል፦
"የኛ ክለቦች ደሃ ናቸው ማለትም ይከብዳል። ችግራቸው የቪዥን ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፦ እንደ መሬት ያለ ሃብት በእጃቸው ሆኖ ብዙዎቹ የተሰጣቸውን ቦታ አጥረው ከማስቀመጥ ያላለፉ አሉ። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ እና ወደ ገንዘብ መቀየር የሚችሉ የክለብ ደጋፊዎችም የባከኑ ሃብቶች ናቸው። ክለባቱ ሃብታቸውን የሚያስተዳድሩበት አቅም እና እውቀቱ ያንሳቸዋል" ብለዋል
በርከት ያሉ ተሳታፊዎች፣ በጥያቄ መልክም ያነሱት ተያያዥ ርዕሰ ጉዳይ የተጫዋቾች ደሞዝ ሚስጥራዊነት ነው።
ምከረ ሃሳብ፦
የፋይናንስ አስተዳደር ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚመለከት ዝርዝር ምክረ-ሃሳብ በጥናቱ የቀረበ ሲሆን፣ ለጥቆማ ያክል፦
በውጭ ገለልተኛ ኦዲተሮች ማስመርመር ፦ ክለባቱ ወጥ የሆነ የገለልተኛ ኦዲት ስርዓትን እንዲከተሉ በመጠየቅ፣ የተለመደውን በገለልተኛ የውጭ ኦዲተሮች የሚከናወን አመታዊ የሂሳብ ምርመራ ማካሄድ ይመከራል።
አማራጭ በጀት ማቅረብ ፦ ክለባት፣ ያለፈውን የውድድር ዓመት የኦዲት ሪፖርት ብቻ ሳይሆን፣ የመጪውን የውድድር ዘመን በጀት ሲያቀርቡ ብቻ ነው ክለቦች የሊግ የገቢ ክፍፍሉ ድርሻቸው ሊለቀቅ የሚገባው።
የኦፊሻል የባንክ አካውንት ሰነድ ማቅረብ፡- እያንዳንዱ የሊጉ አባል ክለብ በአገሪቷ ውስጥ በሚንቀሳቀስ ባንክ የተመዘገበ የራሱ የሆነ የእግር ኳስ ክለቡ የባንክ አካውንት ማቅረብ አለበት። አካውንቱም የክለቡን ስም እና አድራሻ በግልጽ የሚያሳይ፣ እና በክለቡ ሙሉ አስተዳዳር እና ቁጥጥር ስር መሆኑን የሚገልጽ መሆን አለበት።
የሚቀርቡ አመታዊ ሰነዶችን ማሳወቅ፡ - ክለቦች በጀታቸውን፣ አማራጭ በጀታቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ፣ አባል ክለባት በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር የተከናወነ የኦዲት ሂሳብ ሪፖርታቸውን በየዓመቱ ከ__ቀን እና ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኦዲት ሪፖርቱን ሲያቀርቡ ብቻ፣ ከሊጉ የሚችለውን የገቢ ክፍፍል ድርሻ ሊያገኙ የሚገባቸው።
የፋይናንስ መመሪያውን የሚተላለፍ ክለብ ቅጣትን ማሳወቅ፦ አንድ አባል ክለብ የሊጉን የፋይናንስ መመሪያ በሚተላለፍበት ጊዜ የተለያዩ መቀጫዎች እርምጃዎች ሊወሰድበት ይችላል።
የሰለጠነ የሰው ሃይል (አስተዳደራዊ) እጥረት
በርካታ የአገራችን እግር ኳስ ክለቦች በክህሎትና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ እና በመስኩ በሰለጠነ የሰው ሃይል የተደራጁ ባለመሆናቸው፣ በዘልማድ እንደሚመሩ የጥናቱ ተሳታፊዎች እይታቸውን በተደጋጋሚ አጋርተዋል። በእኩሌታውም፣ ለክለባቸው ያለመታከት የሚሰሩ የክለብ አስተዳደር ሰራተኞች መኖራቸውን ነገር ግን እኝሁ ሰራተኞችም በሞያው ያልሰለጠኑ መሆናቸው የራሱን ተጽዕኖ በአገራችን የእግር ኳስ ክለቦች ላይ እንዳሳደረባቸው በስፋት ተነስቷል።
አብዛኛውን ጊዜ ስልጠናዎች በዳኞች እና በአሰልጣኞች ዙሪያ ላይ እንደሚያተኩር እና የክለቦች አስተዳደርን በሚመለከት የሚዘጋጁ ስልጠናዎች የሌሉ መሆናቸውን የጥናቱ ተሳታፊዎቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በእነዚህ እና ሌሎች ተዛማጅ ምክኒያቶች፣ የክለባት አደረጃጀት በስፖርት አስተዳደር ሞያ በሰለጠኑ ባለሞያዎች ሊደራጅ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ተነስቷል። እንደ ባለ ድርሻ አካላቱ ምልከታ፣ በሞያው የሰለጠኑ አስተዳደሮች በቦታው ላይ መቀመጥ፣ ክለባቱ የጠነከረ መሰረት እንዲይዙ እና ስኬታቸው ዘላቂነት እንዲኖረው ያስችላል። ይህ እይታ፣ በተለይ በኮሚሽነሮች፣ በዳኞች፣ በክለብ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ እና በአሰልጣኞች ዘንድ በስፋት ተነስቷል።
ክለቦች ያሏቸው ውሱን ሰራተኞችም ሌሎች የመንግስት ሃላፊነቶችን ደርበው እንደሚሰሩ ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል። በርዕሱ ላይ በርካታ ተመሳሳይ እይታዎች የተጋሩ ሲሆን፣ በማሳያነት አንድ በማሰልጠን ሞያ የተሰማሩ ተሳታፊ ያካፈሉት እይታ ቀርቧል። አሰልጣኙ እንዳስቀመጡት፦
"ክለቦች አንድ ግለሰብ ሁሉን ስራ እንዲሰራ የሚደረግበት የዋን ማን ሾው /one man show/ ናቸው። ሲከፋም፣ አንዳንድ የክለብ ስራ አስኪያጆች ከእግርኳስ በተጨማሪ ሌላ ስራ ደርበው የሚሰሩ እና የሙሉ ጊዜ የእግር ኳስ ክለቡ ሰራተኛ ያልሆኑ አሉ። ... የስራ መደበላለቆች አሉ። አብዛኞቹ ክለቦች በአንድ ስራ አስኪያጅ እና በአንድ ጸሃፊ ብቻ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ አንድ ቢሮ ተሰጥቷቸው የሚሰሩ ናቸው። ይሄ ስራ አስኪያጅ ስንት ነገር ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ይከብዳል። ከተጫዋቾች ጋር ያለን ጉዳይ ሲፈታ ቀኑን ይጨርሳል። ፌስቡክ ላይ ይለጥፋል፣ የቡድን መሪ ይሆናል፣ የቴክኒክ ዳሬከተር ሆኖ ይሰራል፣ ለገቢ ማሰባሰብ እና እቅድ ለመንደፍ ጊዜውም አቅሙም አይኖረውም" ብለዋል።
ብዙዎቹ ተሳታፊዎች፣ የስፖርቱ ከፍተኛ አመራር አካል በቀጣይ ሂደት ውስጥ ችግሩን የመቅረፍ ሃላፊነት እንዳለበት አመልክተው፣ በክለቦች የአቅም ግንባታ ዙሪያ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መተግበር እንዳለባቸው አካፍለዋል።
ምክረ ሃሳብ፦ በአገራችን እግር ኳስ ሃላፊነት ያለበት ከፍተኛ አካል ክለቦች ድርጅታዊ መዋቅር ተከትለው የሰው ሃይላቸውን እንዲያሟሉ ሊጠይቅ ይገባል፣ የሚቀረጹ ፕሮግራሞችን ወደ ተግባር ለመቀየር፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርትም ይህን ይጠየቃል። ብሎም ክለቦቹ ለሚያሟሏቸው የስራ መደቦች የሰው ሃይል የሞያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲዘጋጅላቸው ሊያደርጉ ይገባል። በመሆኑም፣ መሰረታዊ የሆኑ የስራ መደቦችን በአጭር ጊዜ ዕቅድ ውስጥ በሰው ሃይል መሟላት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚጋባ ሃላፊነት ነው። ለዚህም የሞያ ማሻሻያ ስልጠና አስፈላጊነት በተሳታፊዎቹ በስፋት ተነስቷል፤ በተለይ የክለብ አመራር አካላት ስልጠና እንዲያገኙ በርካታ እይታዎች ቀርበዋል። በሃላፊነት ላይ ያሉት የክለብ ስራ አስኪያጆች የሰው ሃይል አስተዳደር እና የገቢ ማመንጫ የሞያ ማሻሻያ ስልጠና ሊሰጣቸው የግድ ይላል። ግብን ማስቀመጥ እና ተነሳሽነት መኖሩ የመጀመሪያ ርምጃ ሲሆን፣ ተነሳሽነቱን ወደ መሬት እንዲወርድ የሚያስችሉ ባለሞያዎችን ማፍራት ለግቡ መሳካት ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
የኢትዮጵያ ክለቦች ችግሮች ዘርፈ ብዙ ነው። ጽሁፉ በተከታታይ ክፍሎች የተሰናዳ ነው። ከተለምዷዊ አሰራር ተላቀው ዘመናዊ ተቋማት እንዲሆኑ ይህ ጥናት በስፋት ዳሰሳ አድርጓል። በክፍል ሶስት የጥናቱን ቀጣይ ግምገማ እናቀርባለን።
ስለ ፀሀፊው፦ ዶ/ር ጋሻው ዘርጋው አብዛ በአሜሪካ ሜሪላንድ ታውሰን ዩኒቨርስቲ የስፖርት ቢዝነስ ማኔጅመንት ፕሮፌሰርና ተመራማሪ እንዲሁም በጀርመን ሙኒክ ቢዝነስ ስኩል የ5 ዶክትሬት ተማሪዎች አማካሪ ናቸው። ዶ/ር ጋሻው በስፖርት ቢዝነስ ማኔጅመንት ዙሪያ በርካታ መፅሀፍትን የፃፉ አለም አቀፍ ተቋማትን የሚያማክሩና የሚያስተምሩ ምሁር ናቸው። እስካሁን 10 መፅሀፍትን አሳትመዋል። በስፖርት ማኔጅመንት ላይ ያተኮሩ ከ100 በላይ የሳይንሳዊ ምርምር የህትመት ውጤቶችን ለአንባቢዎች አቅርበዋል።

በዱባይ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በጦርነት ተዛማጅ ፖስቶች ምክንያት ለእስር ሊዳረጉ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ እየደረሳቸው ነው ተባለ
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኙ ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ አንቀሳቃሾች ከሀገሪቱ ብሄራዊ ደህንነት እና ሰላም ጋር የሚጋጩ መረጃዎችን እንዳያጋሩ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
ዱባይ ከኢራን ጋር በተያያዘ በሚሰነዘሩ የሮኬት ጥቃቶች ስጋት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ የመንግስትን ስም የሚያጠፉ ወይም ሽብር የሚፈጥሩ ምስሎችንና መረጃዎችን የሚለጥፉ ግለሰቦች እስከ 77,000 ዶላር የገንዘብ መቀጫ ወይም የእስር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
አንዳንድ ኢንፍሉዌንሰሮች የሚወድቁ ሮኬቶችን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ከለቀቁ በኋላ በህጉ ስጋት ምክንያት ወዲያውኑ ለማጥፋት ተገደዋል።
የሀገሪቱ የሳይበር ወንጀል ህግ እጅግ ጥብቅ በመሆኑ፣ ማንኛውም ስለ ጦርነቱ የሚሰጥ አስተያየት እንደ ወንጀል ሊቆጠር ይችላል። ባለስልጣናቱ ዓላማቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎች ስርጭትን ለመቆጣጠር እና በህዝብ ላይ ድንጋጤ እንዳይፈጠር መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ: The Telegraph ጋዜጣ እና Detained in Dubai የተሰኘውን የሰብአዊ መብት ድርጅት

#ግብር
በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ከተያዘው የግብር አመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉትን ግብር 25% የሂሳብ ሪፖርት ከሚቀርብበት ወር መጨረሻ ጀምሮ በየሶስት ወሩ በተጠናቀቀ 30 ቀናት ውስጥ አስቀድመው መክፈል እንዳለባቸው ተደንግጓል።
በአዋጁ መሰረት በሽያጭ ላይ የተቀነሰ የቅድመ ገቢ ግብር ተቀናሽ በማድረግ ግብሩ መከፈል አለበት።
በeTax ግብርን አሳውቆ ለመክፈል እንዲቻል Advance Quarterly payment Advice-Schedule C የሚል Account መከፈቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።
ግብር ከፋዮች ለ2017 የግብር ዓመት የተከፈለውን ግብር 25%(1/4) የመክፈያ ጊዜው የካቲት 30/2018 ሳያልፍ Efiled አድርገው ግብራቸውን እንዲከፍሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ዘግይቶ የሚከፈል ግብር #ወለድ እና #መቀጫ የሚያስከትል መሆኑ ተመላክቷል።
የአከፋፈል ሂደቱን በተመለከተ ከላይ ማብራሪያ ቀርቧል።
seledadotio

Sponsored by
Surafel
5 months ago
በሳውዲ አረቢያ የድንበር ጥሰት ከተያዙት ግለሰቦች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገለጸ
#ethiopia | የሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ባለሥልጣናት ባካሄዱት ሳምንታዊ የተቀናጀ የሕግ ማስከበር ዘመቻ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ ከተያዙ ግለሰቦች መካከል 54 በመቶው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ድንበር ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ 1,663 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ የዜግነት ስብጥራቸውም እንደሚከተለው ቀርቧል፦
* ኢትዮጵያውያን፦ 54%
* የመናውያን፦ 45%
* የሌሎች አገራት ዜጎች፦ 1%
አጠቃላይ የቁጥጥር እና የመባረር ሂደት
በተመሳሳይ ወቅት በተካሄደው ሰፊ ፍተሻ በአጠቃላይ 19,101 ሕገ-ወጥ ነዋሪዎች የተያዙ ሲሆን፣ የጥሰቶቹ ዓይነት በዝርዝር በሰንጠረዡ ቀርቧል፦
እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ፣ ከየካቲት 5 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 14,893 ሕገ-ወጥ ነዋሪዎች ከአገር እንዲወጡ ተደርጓል። በአሁኑ ወቅትም ተጨማሪ 21,491 የሚጠጉ ስደተኞች የማባረር ሂደታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ለተባባሪዎች የተሰጠ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ
የሳውዲ መንግሥት ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በማጓጓዝ፣ መጠለያ በመስጠትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ በሚሳተፉ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ በድጋሚ አስታውቋል። ድርጊቱ የተገኘባቸው ግለሰቦች፦
* እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና
* እስከ 1 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እንደሚቀጡ መንግሥት አስገንዝቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #viacapitalnews #ሳውዲ_አረቢያ #ኢትዮጵያ #ስደት #የሕግ_ማስከበር #ዜና

9 months ago
ጠንክሮ የሰራ ጠንክሮ ያልፍለታል ማለት በአጭሩ ይሄ ነው
ብራዚል እስር ቤት ውስጥ ጥፋት ስታጠፋ ፣ እርስ በእርስ ስትደባደቡ ለጥፋታችሁ መቀጫ እንዲሆን ለ16 ሰአታት ያክል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የኤሌክትሪክ ብስክሌት እንድትነዱ ይደረጋል።
ይህንን ቅጣት ብራዚላዊያን እስረኞች እንደሚወዱት ሚስቶቻቸውን አይወዱም ይባላል...በየቀኑ ለ16ሰአታት ብስክሌት ለመንዳት የውሸት እርስ በእርስ ይደባደባሉ ከባባድ ጥፋቶችን ይሰራሉ።
በትንሹ ለ ሳምንት ግፋ ቢል ለ15ቀን በየመሀሉ አንድ አንድ ቀን እያረፋ ይሄንን ቅጣት መቀጣት ይፈልጋሉ ምክንያቱ ደሞ ብስክሌት የመንዳት ችሎታቸው ከፍ ስለሚልና የእግራቸውም ጥንካሬ ስለሚጨምር ቅጣቱን እንደ ስፖርት እንጂ እንደ ቅጣት አያዮትም።
ግን ቅጣቱን የሚወዱት በዚህ ምክንያት ብቻ አይደለም... እስራቸውን ጨርሰው ሲወጡ በብስክሌት አቋራርጠው አሜሪካን መግባት ስለሚችሉም ጭምር ነው
እስከ ዛሬ ከሺዎች በላይ እስረኞች የነበሩ የብራዚል ዜጎች ከባዱን
የDarién Gap ጫካ ከዱር አራዊቶች ጋር በመጋፈጥ አልፈው ወደ አሜሪካ የገብ ሲሆን ይሄ እየታወቀ ግን እስከዛሬ ቅጣቱም አልቆመም
Darién Gap የሚባለው ጫካ በፖናማ እና በኮሎምቢያ መሀል ላይ የሚገኝ በዱር አራዊት የተሞላ ለህይወት አስፈሪ ጫካ ፈፅሞ በመኪና መጓዝ የማይቻል ቢሆንም እስረኞቹ ምንም ሳይበግራቸው ከ7ሺህ 300 ኪሎ ሜትር በላይ በብስክሌት አቆራርጠው አሜሪካ እየገብ ይገኛሉ

12 months ago
ብርሃን ገበያ በአምቦ ከተማ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
#ethiopia | በአምቦ ከተማ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያሰበው ትልም በተለያዩ አጋር ተቋማት ትብብር እውን ሆኗል::
ኢትዮጵያ አብላጫው የህዝብ ቁጥሯ ወጣት ነው::ታድያ ይሄ ብቻውን በረከት አልያ መርገምት ሊሆን አይችልም::ውሳኔው የእኛ ሲሆን ወጣቶቿን በአግባቡ የተጠቀመች ሃገር ታድጋለች ከሚለው ሃቅ ጋር መተላለፍ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል::
ሊንክ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ መቀጫውን በሃገረ ቻይና ያደረገው ኢዩ ሸገር ከአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለወጣቶች በአምቦ ከተማ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካንፓስ ፊት ለፊት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሱቆች ሰርተው ለወጣቶች አስረክበዋል::
በሃገር ውስጥ እና በውጭ የተለያይ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩት ሊንክ አስ ትሬዲንግ: ጢግሮስ ትሬዲንግ እና ኢዩ ሸገር
ገንብተው ያጠናቀቋቸውን ሱቆች ላስረከቧቸው
ወጣቶች ያለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ግብዐቶችን ያቀረቡ ሲሆን ለ 5 ዓመታት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል::
በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሻለ አፈፃፅም ላያሳየ/ላሳየች ወጣትም የመኪና ሽልማት የሚበረከት ሲሆን በርክክብ ስነ ስርዓቱ ወቅት የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹን ጨምሮ የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት
ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር እንዳልካቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት እና እንግዶች ተገኝተዋል::

Comments