ብርሃን ገበያ በአምቦ ከተማ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
#ethiopia | በአምቦ ከተማ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያሰበው ትልም በተለያዩ አጋር ተቋማት ትብብር እውን ሆኗል::
ኢትዮጵያ አብላጫው የህዝብ ቁጥሯ ወጣት ነው::ታድያ ይሄ ብቻውን በረከት አልያ መርገምት ሊሆን አይችልም::ውሳኔው የእኛ ሲሆን ወጣቶቿን በአግባቡ የተጠቀመች ሃገር ታድጋለች ከሚለው ሃቅ ጋር መተላለፍ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል::
ሊንክ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ መቀጫውን በሃገረ ቻይና ያደረገው ኢዩ ሸገር ከአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለወጣቶች በአምቦ ከተማ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካንፓስ ፊት ለፊት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሱቆች ሰርተው ለወጣቶች አስረክበዋል::
በሃገር ውስጥ እና በውጭ የተለያይ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩት ሊንክ አስ ትሬዲንግ: ጢግሮስ ትሬዲንግ እና ኢዩ ሸገር
ገንብተው ያጠናቀቋቸውን ሱቆች ላስረከቧቸው
ወጣቶች ያለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ግብዐቶችን ያቀረቡ ሲሆን ለ 5 ዓመታት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል::
በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሻለ አፈፃፅም ላያሳየ/ላሳየች ወጣትም የመኪና ሽልማት የሚበረከት ሲሆን በርክክብ ስነ ስርዓቱ ወቅት የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹን ጨምሮ የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት
ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር እንዳልካቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት እና እንግዶች ተገኝተዋል::

12 months ago