Logo
SeledaPost
#ግብር

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ከተያዘው የግብር አመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የከፈሉትን ግብር 25% የሂሳብ ሪፖርት ከሚቀርብበት ወር መጨረሻ ጀምሮ በየሶስት ወሩ በተጠናቀቀ 30 ቀናት ውስጥ አስቀድመው መክፈል እንዳለባቸው ተደንግጓል።

በአዋጁ መሰረት በሽያጭ ላይ የተቀነሰ የቅድመ ገቢ ግብር ተቀናሽ በማድረግ ግብሩ መከፈል አለበት።

በeTax ግብርን አሳውቆ ለመክፈል እንዲቻል Advance Quarterly payment Advice-Schedule C የሚል Account መከፈቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።

ግብር ከፋዮች ለ2017 የግብር ዓመት የተከፈለውን ግብር 25%(1/4) የመክፈያ ጊዜው የካቲት 30/2018 ሳያልፍ Efiled አድርገው ግብራቸውን እንዲከፍሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ዘግይቶ የሚከፈል ግብር #ወለድ እና #መቀጫ የሚያስከትል መሆኑ ተመላክቷል።

የአከፋፈል ሂደቱን በተመለከተ ከላይ ማብራሪያ ቀርቧል።

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.