21 days ago
የጸጥታ ተቋማት ሪፎርም፡ ሉዓላዊነትን ከመጠበቅ እስከ የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ
**************
የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት፣ ሰላምና የዜጎች ደኅንነት በጠንካራ የጸጥታ ተቋም ላይ የተመሠረቱ ናቸው። የዘመኑ የጸጥታ ምህዳር ግን ቀድሞ ከነበረው በእጅጉ ተለውጧል። ዛሬ ሀገራት ከባህላዊ የደኅንነት ስጋቶች በተጨማሪ ሳይበር ጥቃት፣ የተደራጀ ወንጀል፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መቋቋም ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ሁኔታ የጸጥታ ተቋማት የሚሠሩበትን መንገድ እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል። በኢትዮጵያም በቅርብ ዓመታት የተካሄዱ የጸጥታ ዘርፍ ሪፎርሞች ተቋማትን በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በመሠረተ ልማትና በአሠራር ለማዘመን ያተኮሩ ናቸው።
የጸጥታ ተቋማት ተልዕኮ የሀገርን ሉዓላዊነትና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ከመጠብቅ ባሻገር የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ፣ ወንጀልን መከላከልና ሕግ ማስከበርን ያካትታል።
በዘመናዊ የጸጥታ አሠራር ውስጥ ደግሞ ተቋም አደጋ ከተፈጠረ በኋላ ብቻ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን ስጋቶችን ቀድሞ መለየት፣ መተንበይና መከላከል የሚችል አቅም መገንባት ይጠበቅበታል። በዚህ ረገድ የመረጃ አቅም፣ የምርመራ ብቃት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ተቋማዊ ቅንጅት ወሳኝ ናቸው።
በተለይ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ሳይንስ አቅምን ማሳደጉ የወንጀል ምርመራን ከግምትና ከግል ግንዛቤ ወደ ሳይንሳዊ ማስረጃ ለማሸጋገር የሚያግዝ ለውጥ ነው። የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ የምርመራ ቴክኒኮችን ጨምሮ ዘመናዊ አቅምን እንድገነባ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
የጸጥታ ምህዳሩ ወደ ዲጂታል ዓለም በመስፋፋቱ የሳይበር ደኅንነት የብሔራዊ ደኅንነት ዋና አካል ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሳይበር ደኅንነት ፖሊሲም ዲጂታል ለውጥ ከሚያመጣቸው ዕድሎች ጎን ለጎን በዜጎች፣ በመረጃዎችና በወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ የሳይበር ስጋቶችን መቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ያስቀምጣል።
ዘመናዊ መሣሪያ መግዛት ብቻ የጸጥታ ተቋምን ዘመናዊ አያደርገውም። ቴክኖሎጂውን በብቃት የሚጠቀም፣ መረጃን የሚተነትን፣ ሕግንና የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን የሚያከብር የሰው ኃይል ከመሣሪያው እኩል ወሳኝ ነው።
በዚህም የፖሊስ ምርምርና ስልጠና ተቋማት የግጭት አመራር፣ የሰላም ግንባታ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ያሉ ዘርፎችን በምርምር መዳሰሳቸው የሙያዊ አቅም ግንባታው አካል ነው።
የጸጥታ ተቋማት ሪፎርም በአንድ ጊዜ ተከናውኖ የሚያበቃ ሂደት አይደለም። የስጋቶች ባህሪ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ ተቋማትም በተመሳሳይ ፍጥነት መማር፣ መላመድና መታደስ ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ሽግግር ከባህላዊ የጸጥታ አሠራር ወደ ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ሳይንሳዊ ምርመራ፣ ዲጂታል አቅም፣ የሰው ኃይል ግንባታና የተቀናጀ የጸጥታ አሠራር የሚያመራ ሂደት ነው። የዚህ ሽግግር ዋና ግብም ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ፣ ሕግን በማስከበር እና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ማረጋገጥ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #securityreform #regionalstability #endf #nationalsecurity #institutionbuilding

2 months ago
ከዚህ ድርጊት ጀርባ የተቀመጠው አካል ማነው?!
#ethiopia | ከፌዴሬሽኑ የሥራ ኃላፊነት የለቀቁና በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ የማይገኙ የቀድሞ የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተር በሲልቨር ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና እንዲሳተፉ መደረጉ ከፍተኛ ቅሬታና ጥያቄ አስነስቷል
ከሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ከአስተዳደራዊ ግድፈቶች ጋር ተያይዞ ሕጋዊ ምርመራ የሚደረግባቸው ግለሰብ በማን ይሁንታና ውክልና ሥልጠናውን ሊወስዱ ቻሉ የሚለው ጉዳይ ብዙዎችን አነጋግሯል።
የዓለም አትሌቲክስ አህጉራዊ ማኅበራትና አባል ፌዴሬሽኖችን በማስተባበር በየሁለት ዓመቱ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛና በስፓኒሽ ቋንቋዎች የሚሰጠውን የሲልቨር ደረጃ የዳኝነት በይነመረብ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
ይህ የትምህርት መርሃ ግብር ቢያንስ የ4 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸውንና ዕድሜያቸው 23 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የነሐስ ደረጃ ዳኞችን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ውድድሮችን የማስፈጸም፣ ቅሬታዎችን የመፍታትና ውሳኔዎችን የማብራራት ብቃት እንዲኖራቸው ይጠይቃል።
በዚሁ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተሰጠ በሚገኘው ሥልጠና ላይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በይፋ ተመርጠው የተላኩት አቶ አሠፋና አቶ ተከተል የተባሉ ሁለት ባለሙያዎች በመከታተል ላይ ናቸው። ሆኖም ግን ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል እንደደረሰችበት መረጃ ከሆነ ከእነዚህ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሦስተኛ ግለሰብ በስልጠናው ላይ እንዲካተቱ ተደርጓል።
ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆነ ከሥራ ኃላፊነታቸው የለቀቁና നിലവിൽ በሀገር ውስጥ የማይገኙት የቀድሞ የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ በዚሁ የሲልቨር ደረጃ የዳኝነት ሥልጠና ውስጥ ስማቸው ተካቶ እንዲሰለጥኑ መደረጉ በርካታ ወገኖችን አስገርሟል፣ ጥያቄም ፈጥሯል።
ከሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ከአስተዳደር ግድፈቶች ጋር ተያይዞ የስም ጥፋትና የሕግ ጥያቄ ያለባቸው ግለሰብ በሥልጠናው ውስጥ እንዲካተቱ የተደረገበት አሰራር አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጻል።
የቀድሞው ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ይህንን ዕድል ሊያገኙ የቻሉት የየትኛውን የፌዴሬሽን አመራር ውክልናና ፈቃድ አግኝተው ነው በማለት በርካታ የስፖርቱ ባለሙያዎች ጥብቅ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ከዚህ አጠራጣሪ ድርጊት ጀርባ ያለው አካል ማን እንደሆነ ተጨማሪ ማጣራቶችን በማድረግ ዝርዝሩን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
ከሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል
#athletics #worldathletics #ethiopianathletics #sportsnews #ethiopiansport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ዓለም አቀፉ የፓርላማ፣ መረጃና ደህንነት ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
**************
ዓለም አቀፉ የፓርላማ፣ መረጃና ደህንነት ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። ፎረሙ በአፍሪካ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን አዲስ አበባም መድረኩን በማስተናገድ ሁለተኛዋ የአፍሪካ ከተማ ሆናለች።
ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ ሽብርተኝነትን መከላከል፣ ቀጣናዊ ፀጥታ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በዋናነት ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ኢትዮጵያ ይህንን ዓለም አቀፍ ፎረም የምታስተናግደው 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሐዊና ግልጽ በሆነ መልኩ ባካሄደች ማግሥት መሆኑ ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።
አፈ ጉባኤው አክለውም፣ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመተባበርና በቆራጥነት ለመከላከል ሀገራችን ሰፊ ሥራዎችን እያከናወነች እንደምትገኝ ጠቁመዋል።
በቴክኖሎጂው ዘርፍም ኢትዮጵያ አመርቂ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ያብራሩት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የዲጂታልና የሳይበር ደህንነት ይበልጥ የተጠበቀ እንዲሆን በየጊዜው ከሚፈጠሩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዕድገቶች ጋር ራስን በማላመድ ረገድ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ለጉባኤው ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪንግ ማሲንጋ በበኩላቸው፣ ይህ ፎረም ሀገራት መረጃዎችን የጋራ በማድረግ የዜጎቻቸውን ደህንነት ለማረጋገጥና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀለኞችን ተከታትሎ ለሕግ ለማቅረብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው፣ መሰል ዓለም አቀፍ የደህንነት ትብብሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የፎረሙ ሊቀመንበር ሮበርት ፒትንገር በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርንና ሌሎች ቀጣናዊ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ "እውነተኛ አጋር" መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች የምትገኝ ሀገር ናት ሲሉ ገልጸዋል።
በሳደት መሀመድሳኒ
#ethiopianbroadcastingcorporation #parliamentaryintelligencesecurityforum #pisf2026 #securityforumafrica

ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃና ደህንነት ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዋና ትኩረቱን በፓርላማ አባላት፣ በመረጃ ባለሙያዎችና በመንግሥት ባለስልጣናት መካከል በዓለም አቀፍ የደህንነት ስጋቶች ዙሪያ ትብብር ለማጎልበት ያደረገ ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃና ደህንነት ፎረም መካሄድ ጀምሯል።
በፈረንጆቹ 2014 በአሜሪካ ኮንግረስ የቀድሞ አባል ሮበርት ፒቴንገር የተመሰረተው ፎረሙ፤ ዋና ተልዕኮው በሕግ አውጪው አካልና በአስፈፃሚው የመረጃና ደህንነት ተቋማት መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ ነው።
በፎረሙ በፍጥነት እያደጉ የመጡ ድንበር ዘለል እና የቴክኖሎጂ ስጋቶችን ለመፍታት፣ የቀጣናውና የዓለም አቀፍ ሕግ አውጪዎችና የደህንነት ባለሙያዎች ይመክራሉ።
በዚህም ሕግና ቴክኖሎጂ የሚገናኙባቸውን የደህንነት ተግዳሮቶች መሠረት አድርጎ እንደሚመክር እና በዋናነት የሳይበር ደህንነት፣ ሕገወጥ ፋይናንስና ለሽብርተኝነት የሚውል የገንዘብ ምንጭን መከላከል እና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከልን ጨምሮ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።
በፎረሙ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፓርላማ መረጃና ደህንነት ፎረም መስራቹ ሮበርት ፒቴንገር፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቬን ማሲንጋን ጨምሮ ከ43 ሀገራት የተውጣጡ የፓርላማ አባላት እየተሳተፉ ነው።
ፎረሙ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
በዓለምሰገድ አሳዬ

Sponsored by
Surafel
7 months ago
በኬንያ ታግተው የነበሩ 66 ኢትዮጵያውያን እና 4 ኤርትራውያን በፖሊስ ነጻ ወጡ
#ethiopia | የኬንያ ፖሊስ በናይሮቢ ዳርቻ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሕገ-ወጥ የሰዎች አጋቾች ታግተው የነበሩ 70 የውጭ ሀገር ዜጎችን ነጻ ማውጣቱን አስታወቀ። እንደ ፖሊስ መግለጫ ከሆነ፣ ነጻ ከወጡት መካከል 66ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 4ቱ ደግሞ ኤርትራውያን ናቸው።
የታጋቾቹ ሁኔታና መዳረሻ
ስደተኞቹ በናይሮቢ አቅራቢያ በሚገኘው ሩዋይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በአንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው እንደነበር ፖሊስ በኤክስ (X) ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል። ተጎጂዎቹ ለጸጥታ አካላት በሰጡት ቃል፦
* ከሀገራቸው የወጡት በተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
* ዋና ዓላማቸው የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የነበረ ቢሆንም፣ በመንገድ ላይ በአጋቾቹ እጅ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
የፖሊስ እርምጃ
የኬንያ የጸጥታ አካላት በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ምርመራ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባራትን ለመከላከል ቁጥጥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ይህ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ሕገ-ወጥ ስደት አሁንም ለዜጎች ሕይወት አደገኛ መሆኑን በድጋሚ አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኬንያ #ስደት #ኢትዮጵያ #ኤርትራ #ናይሮቢ #ሕገወጥ_የሰዎች_ዝውውር #kenya #ethiopia #humantrafficking #nairobi

9 months ago
645 ኪሎ ሜትር በተሽከርካሪ ወንበር ስር ተደብቆ የተጓዘው የ10 ዓመት ታዳጊ ሰውነቱ በጉዞው ተዳክሞ ባሰማው ድምፅ በሰላም ከወንበሩ ስር ወጣ
ከደምቢደሎ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ስር ተደብቆ፣ ከ645 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው የ10 ዓመት ታዳጊ በሰላም ተገኝቷል።
ታዳጊው ጉዞውን የጀመረው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ደምቢደሎ ላይ ሲሆን፣ ማንም ሳይመለከተው በአውቶብሱ ስር ያሉ የብረት ክፍሎችን ሙጥኝ ብሎ በመያዝ ለአስር ሰዓታት ያህል አደገኛ ጉዞ አድርጓል። ታዳጊው ይህንን ሁሉ ርቀት ያለምንም ጉዳት መጓዙን መረጃዎች ያመለክታሉ።
አውቶብሱ አዲስ አበባ ሊገባ 40 ኪ.ሜ ሲቀረው ሆለታ አካባቢ፣ ከታችኛው የአውቶብሱ ክፍል የሰው የጣር እንግዳ ድምፅ የሰሙ ተሳፋሪዎች ለሾፌሩ ጥቆማ ይሰጣሉ። ተሽከርካሪው ቆሞ በተደረገ ፍተሻም፣ ታዳጊው ከአውቶብሱ እስር ብረት በመያዝ በህይወት ተገኝቷል። ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በአስኮ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የተደረገና እየተመረመረ ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች ማንኛውንም ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የመኪናቸውን ደህንነትና ስር መፈተሽ እንዳለባቸው ትልቅ ትምህርት የተሰጠበት ሆኗል።
"ታዳጊው በጉዞው ላይ ጉዳት ደርሶበት ቢሆን ኖሮ ሾፌሩ ለከባድ የህግ ተጠያቂነት ይዳረግ ነበር፤ በመሆኑም ቅድመ ጥንቃቄ ወሳኝ ነው" ሲሉ ጉዳዩን የተከታተሉ አካላት ገልጸዋል።የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አቃቢ ሕግ አብዮት አስፋ ማንኛውም አሽከርካሪ ሆነ ረዳት ተሽከርካሪው ከመንቀሳቀሱ በፊት አስፈላጊውን ፍተሻ ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን ታዳጊው ይህን ያህል ኪሎ ሜትር በወንበር ስር ተጉዞ ሲመጣ ጥንቃቄ ያላደረጉ አሽከርካሪና ረዳት በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ና ድንበር የማሻገር ወንጀል ሊከሠሱ እንደሚችሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል

1 year ago
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሀዘን መግለጫ አወጣ::
በትናንትናው እለት፣ ሐምሌ 27፣ 2017 ዓ.ም. የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IMO) በሰጠው መግለጫ፣ በጀልባ ወደ የመን ሲያልፉ የነበሩ
ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት፣ 68 ወገኖቻችን ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።
ሌሎች 12 ሰዎች በህይወት ቢተርፉም፣ 74 ሰዎች እስካሁን ድረስ እንዳልተገኙ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) በዚህ አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፤ ለሟች ቤተሰቦች፣ ዘመዶች እና ወዳጆች መፅናናትንም ተመኝቷል።
ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ኢዜማ
መንግስት ላይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርቧል፦
1. ለስደት ምክንያት የሚሆኑ ችግሮች ይፈቱ:
* ዜጎች በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ግጭቶችንና የሥራ አጥነትን በቅድሚያ እንዲፈታ።
* የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ህጋዊ በሆነ መንገድ በውጪ ሀገር መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች፣ ተገቢውን ሥልጠናና የጉዞ እድል አጥጋቢ በሆነ መንገድ እንዲያመቻች።
2. የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀለኞች ተጠያቂ ይሁኑ:
* መንግስት የሰውን ህይወት የሚያጠፉ ሕገወጥ ደላላዎችን እና አዘዋዋሪዎችን በሕግ እንዲጠይቅ።
በመጨረሻም፣ ኢዜማ የሀገራችን ዜጎች በሀገር ውስጥ ችግሮች ቢኖሩም፣ ከፍተኛ የጉዳት ስጋት ወዳለበት አደገኛ መንገድ ከመጓዝ ይልቅ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ እንዲጓዙ ጥሪ አቅርቧል።
የሟች እህት ወንድሞቻችን ነፍስ ይማር!
Via ኢዜማ

Comments