Logo
FIDEL POST NEWS
645 ኪሎ ሜትር በተሽከርካሪ ወንበር ስር ተደብቆ የተጓዘው የ10 ዓመት ታዳጊ ሰውነቱ በጉዞው ተዳክሞ ባሰማው ድምፅ በሰላም ከወንበሩ ስር ወጣ

ከደምቢደሎ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ስር ተደብቆ፣ ከ645 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው የ10 ዓመት ታዳጊ በሰላም ተገኝቷል።

ታዳጊው ጉዞውን የጀመረው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ደምቢደሎ ላይ ሲሆን፣ ማንም ሳይመለከተው በአውቶብሱ ስር ያሉ የብረት ክፍሎችን ሙጥኝ ብሎ በመያዝ ለአስር ሰዓታት  ያህል አደገኛ ጉዞ አድርጓል። ታዳጊው ይህንን ሁሉ ርቀት ያለምንም ጉዳት መጓዙን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አውቶብሱ አዲስ አበባ ሊገባ 40 ኪ.ሜ ሲቀረው ሆለታ አካባቢ፣ ከታችኛው የአውቶብሱ ክፍል የሰው የጣር እንግዳ ድምፅ የሰሙ ተሳፋሪዎች ለሾፌሩ ጥቆማ ይሰጣሉ።  ተሽከርካሪው  ቆሞ በተደረገ ፍተሻም፣ ታዳጊው ከአውቶብሱ  እስር  ብረት በመያዝ በህይወት ተገኝቷል። ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በአስኮ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የተደረገና እየተመረመረ  ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች ማንኛውንም ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የመኪናቸውን ደህንነትና ስር መፈተሽ እንዳለባቸው ትልቅ ትምህርት የተሰጠበት ሆኗል።

"ታዳጊው በጉዞው ላይ ጉዳት ደርሶበት ቢሆን ኖሮ ሾፌሩ ለከባድ የህግ ተጠያቂነት ይዳረግ ነበር፤ በመሆኑም ቅድመ ጥንቃቄ ወሳኝ ነው" ሲሉ ጉዳዩን የተከታተሉ አካላት ገልጸዋል።የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አቃቢ ሕግ አብዮት አስፋ ማንኛውም አሽከርካሪ ሆነ ረዳት ተሽከርካሪው ከመንቀሳቀሱ በፊት አስፈላጊውን ፍተሻ ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን ታዳጊው ይህን ያህል ኪሎ ሜትር በወንበር ስር ተጉዞ ሲመጣ ጥንቃቄ ያላደረጉ አሽከርካሪና ረዳት በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ና ድንበር የማሻገር ወንጀል ሊከሠሱ እንደሚችሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.