Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሀዘን መግለጫ አወጣ::

በትናንትናው እለት፣ ሐምሌ 27፣ 2017 ዓ.ም. የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IMO) በሰጠው መግለጫ፣ በጀልባ ወደ የመን ሲያልፉ የነበሩ
ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት፣ 68 ወገኖቻችን ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።

ሌሎች 12 ሰዎች በህይወት ቢተርፉም፣ 74 ሰዎች እስካሁን ድረስ እንዳልተገኙ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) በዚህ አሰቃቂ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፤ ለሟች ቤተሰቦች፣ ዘመዶች እና ወዳጆች መፅናናትንም ተመኝቷል።

ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ጋር በተያያዘም ኢዜማ

መንግስት ላይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርቧል፦

1. ለስደት ምክንያት የሚሆኑ ችግሮች ይፈቱ:

* ዜጎች በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ግጭቶችንና የሥራ አጥነትን በቅድሚያ እንዲፈታ።

* የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ህጋዊ በሆነ መንገድ በውጪ ሀገር መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች፣ ተገቢውን ሥልጠናና የጉዞ እድል አጥጋቢ በሆነ መንገድ እንዲያመቻች።

2. የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀለኞች ተጠያቂ ይሁኑ:

* መንግስት የሰውን ህይወት የሚያጠፉ ሕገወጥ ደላላዎችን እና አዘዋዋሪዎችን በሕግ እንዲጠይቅ።

በመጨረሻም፣ ኢዜማ የሀገራችን ዜጎች በሀገር ውስጥ ችግሮች ቢኖሩም፣ ከፍተኛ የጉዳት ስጋት ወዳለበት አደገኛ መንገድ ከመጓዝ ይልቅ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ እንዲጓዙ ጥሪ አቅርቧል።

የሟች እህት ወንድሞቻችን ነፍስ ይማር!

Via ኢዜማ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.