በባሕር ዳር የሚንቀሳቀሱ የመኖሪያ ቤት አልሚ አክሲዮን ማኅበራት አሠራራቸውን ዘመናዊ የሚያደርግ አዲስ መተግበሪያ እና ድረገጽ አስገመገሙ
#ethiopia | በቤት ልማት ዘርፍ ላይ የተሰማሩና መቀመጫቸውን በባሕር ዳር ከተማ ያደረጉ አራት የአክሲዮን ማኅበራት፣ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ያዘጋጁትን አዲስ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በባለሙያዎች አስገምግመዋል።
ዋዜማ፣ ፕላኔት፣ ዋን ሩፍ እና ታውን አፓርትመንት የተባሉት እነዚህ ማኅበራት፣ ለአባላቶቻቸው ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ተቋቁመው ወደ ሥራ የገቡ ኩባንያዎች ናቸው።
የኩባንያዎቹ መሥራች አቶ ዘላለም እሸቱ በምክክር መድረኩ ላይ እንደተናገሩት፣ አሠራርን በቴክኖሎጂ መደገፍ በአሁኑ ወቅት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል። ማኅበራቱ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚኖሩ ባለአክሲዮኖች በሚሰበሰብ መዋጮ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው፣ አዲሱ መተግበሪያ በሥራዎች ላይ ፍጹም ግልጸኝነትን ለመፍጠር ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።
ቀደም ሲል የነበረው አሠራር የቤት ግንባታ ገቢና ወጪዎችን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በሚደረግ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሚያቀርብ በመሆኑ የመረጃ ክፍተት ይፈጥር ነበር።
አዲሱ የቴክኖሎጂ አማራጭ ግን እያንዳንዱ የገንዘብ እንቅስቃሴ የወቅቱን የገበያ ዋጋ ባገናዘበ ማስረጃ እንዲደገፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ ባለአክሲዮኖችም ባሉበት ሆነው መረጃዎችን በቀጥታ መከታተል እንዲችሉ ያስችላቸዋል።
በዕለቱ የተገኙት የክልሉ ንግድ ቢሮ የአክሲዮን ክትትል ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ጓንቻ በበኩላቸው፣ በአሁኑ ወቅት የአክሲዮን ማኅበራት ዋነኛ ፈተና የአሠራር ግልጸኝነት ማጣት መሆኑን ጠቅሰው ይህ ጅማሮ ለሌሎችም አርአያ የሚሆንና ትልቅ መፍትሔ ይዞ የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በባለሙያዎች የተነሱ ጠቃሚ ማሻሻያዎችን በማካተት መተግበሪያው በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።
#bahirdar #digitaltransformation #realestateethiopia #technology #housingdevelopment #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

14 days ago