Logo
Getu Temesgen
🏆 ኩራት፦ ለሰባት ኢትዮጵያውያን የ"ጳጉሜን አዋርድ" ሽልማት ተሰጠ! 🇪🇹✨
#ethiopia | ​በካሊፎርንያ ግዛት ሎሳንጀለስ ከተማ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነ ደማቅ ስነ-ሥርዓት፣ የጷጉሜን የኢትዮጵያውያን መዝናኛና ባሕል ማዕከል (PEEC) ለሀገርና ለወገን ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰባት ኢትዮጵያውያን እውቅናና ሽልማት አበርክቷል።

​🌟 የዘንድሮው የ"ጳጉሜን አዋርድ" ተሸላሚዎች፦

​አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ)፦
በቱሪዝም ዘርፍ ከ86 በላይ ሀገራትን በመዞር ታሪካዊ ስፍራዎችን ያስተዋወቀ ልዩ ተሸላሚ።

​ጋዜጠኛ ጌታቸው ወልዩ፦
ለ40 ዓመታት በጋዜጠኝነት፣ በታሪክና በዓባይ ተፋሰስ ጥናት ሀገሩን በታማኝነት ያገለገለ።

​አርቲስት ተፈሪ አስፋ (Posthumous)፦
በኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላይ ላበረከተው የማይተካ ሚና (በድኅረ-ሕይወት) የክብር ሽልማት የተሰጠው።

​ዶክተር ሐዋኒ ንጉሤ፦
በበጎ አድራጎትና በትምህርት ዘርፍ ለሕጻናትና ለትውልድ ግንባታ ለሰሩት የላቀ ስራ።

​ደራሲ ወልደገብርኤል አስጌ፦
በሥነ-ጽሑፍና ታሪክ ዘርፍ "የነቢዩ መሐመድ ታሪክ" የተሰኘ ታሪካዊ ሰነድ በማኖራቸው።

​ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ (ተቦርነ)፦
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ በሰነድና በማኅደር በማቆየት ለተጫወቱት ሚና።

​አቶ ፍስሐ ወልደ-አማኑኤል፦
በእግር ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ።

​🙏 እንኳን ደስ አላችሁ!
እነዚህ ታላላቅ ግለሰቦች ለሀገራችን ብርሃን የሆኑ፣ በተሰማሩበት መስክ ሁሉ ጥበብንና እውነትን የተከሉ ባለሙያዎች ናቸው።

በባዕድ ሀገር ሆነው የሀገራቸውን ልጆች አበርክቶ የሚያከብሩት የጷጉሜን የባህል ማዕከል አባላትም ምስጋና ይገባቸዋል።

​ለተሸላሚዎቹ ያላችሁን ደስታና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በኮሜንት አጋሩን። 👏🇪🇹

​#pagumenawards #ethiopia #excellence #losangeles #ethiopianheros #art #journalism #sport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.