Logo
Getu Temesgen
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

​#ethiopia | ምክር ቤቱ የ9 የቦርድ አባላትን እና የ2 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን ሹመት አፅድቋል

​የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመትን አፅድቋል።

​በዚህም መሰረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሾመዋል።

​የተሾሙት የቦርድ አባላት ዝርዝር:
1️⃣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - ቦርድ ሰብሳቢ
2️⃣ ዶ/ር ወርቁ ጋቸና (የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር) - አባል
3️⃣ ዶ/ር መቅደስ ዳባ (የጤና ሚኒስትር) - አባል
4️⃣ ዶ/ር እንደገና አበበ (የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ) - አባል
5️⃣ አቶ ቸሩጌታ ገነነ (የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ) - አባል
6️⃣ ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ (የቀድሞ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር) - አባል

​ከዚህ ቀደም የነበሩ እና አባልነታቸው እንዲቀጥል የተደረጉ:
​አቶ ጃፋር በድሩ
​አቶ የሱፍ ኢብራሂም
​ዶ/ር አብዱልዋሳ አብዱላሂ

​የፍርድ ቤት ሹመት:
በተጨማሪም ምክር ቤቱ አቶ ልዑል ካሳዬ ወልዱን እና አቶ ምትኩ ማዳ ድልነሳውን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።


​#ebc #appointment #danielkibret #parliament #ethiopia #media #board #highcourt #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.