Logo
Getu Temesgen
🥊 የአዲስ አበባ ኪክ ቦክሲንግ አሠልጣኞች ማህበር ህጋዊ ፈቃድ አገኘ
#ethiopia | ​"ማህበሩ መስፈርቶችን በማሟላቱ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እውቅና ተሰጥቶታል"

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፤ "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኪክ ቦክሲንግ አሠልጣኞች ማህበር" ህጋዊ መስፈርቶችን አሟልቶ መገኘቱን ተከትሎ ህጋዊ ፈቃድ እንደሰጠው አስታውቋል።

​በደብዳቤው ላይ የተገለጹ ዝርዝሮች:

✅ ማህበሩ በስፖርት ምክር ቤት የስፖርት ማህበራት እና ክለቦች መቋቋሚያ ደንብ መሰረት መስፈርቶችን አሟልቷል።

✅ በቢሮው የስፖርት ማህበራት ፈቃድ ቡድን ስር ዳግም ተመዝግቧል።

✅ ይህ ደብዳቤ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ህጋዊ ፈቃድ አግኝቷል።
​በመሆኑም የአዲስ አበባ ኪክ ቦክስ አሶሴሽን፤ የአሰልጣኞች ማህበሩን በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ እንዲያሳትፍ ቢሮው አሳስቧል።

​ለኪክ ቦክሲንግ አሰልጣኞች እና ለስፖርት ቤተሰቡ እንኳን ደስ አላችሁ!

​#kickboxing #coachesassociation #addisababasport #license #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.