13 days ago
የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅትን የቦታ እጥረት ዋነኛ ተግዳሮት መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያዎች የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅትን ጎብኝተው በማዕከሉ የሚሰጡ የሙያ ሥልጠናና ድጋፎችን ተመልክተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያው አቶ ሞገስ ገረመው፣ በማዕከሉ ያዩት የታዳጊ ወጣቶች አያያዝ፣ የቦታው ንጽህናና የሚሰጡት የሙያ ሥልጠናዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። ወጣቶቹ የተለያዩ ሙያዎችን እየተማሩ የራሳቸውን አቅም እንዲገነቡና በራሳቸው እንዲተማመኑ የሚያስችል እድል መፈጠሩንም ጠቁመዋል።
ሌላኛዋ የአስተዳደሩ ማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያ ወይዘሮ ሄለን ብርሃን በበኩላቸው፣ ማዕከሉ ብዙ ሰዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለማቃለል እየሰራ ያለ እና ለወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። በጉብኝታቸውም በሙዚቃ፣ በእጅ ሥራና በሌሎች ዘርፎች ያዩት የህፃናቱ ችሎታ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሄለን፣ በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ እየደገፈ ያለው ወደ 40 የሚጠጉ ህፃናትና ወጣቶች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ፣ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በየቤታቸው የሚገኙ ሌሎች ህፃናትም ወጥተው በችሎታቸው እንዲደገፉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ህፃናቱና ወጣቶቹ በሽመና፣ በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በስፖርት፣ በኮምፒዩተርና በኮዲንግ ዘርፎች ያዳበሩትን ክህሎትና የሚያከናውኑትን ሥራ ለጎብኚዎቹ አሳይተዋል።
የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ወይዘሮ ሰሎሜ ኩምሳ፣ የባለሙያዎቹ ጉብኝትና ድጋፍ ለህፃናቱ እና ድርጅቱ ለሚያከናውነው ሥራ ትልቅ ማበረታቻ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰሎሜ ገለጻ፣ ድርጅቱ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመማር ችግር ላላቸው ወጣቶች የሙያ፣ የኮምፒዩተር፣ የሙዚቃ፣ የሥነ ጥበብና የስፖርት ሥልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ይሰጣል። ድርጅቱ ባለፉት ዓመታትም ከ350 በላይ ወጣቶችን መደገፉን ገልጸዋል።
ማዕከሉ እያከናወነ ካለው ሥራ ጋር ተያይዞ የቦታ እጥረት ዋነኛ ተግዳሮት መሆኑን ወይዘሮ ሰሎሜ ጠቁመዋል። ተጨማሪ ቦታ ቢገኝ ብዙ ህፃናትን እና ታዳጊ ወጣቶችን መድረስና የሙያ ሥልጠናዎችን ማስፋት እንደሚቻል ገልጸው፣ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና የመንግሥት አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በማዕከሉ ከሰለጠኑ ወጣቶች መካከል 12ቱ በሽመና ሙያ በመሰማራት ነጠላ፣ ሻርፕና የባህል ልብሶችን እያመረቱ መሆኑ ተገልጿል። ማዕከሉ ከሙያ ሥልጠና በተጨማሪ ለወጣቶቹ የሥነ ልቦናና የሕክምና ድጋፍ፣ እንዲሁም ለወላጆችና መምህራን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።
ድጋፍ ለማድረግ፦
1000641844237 — የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
91675145 — አቢሲኒያ ባንክ
513049 — ቴሌ ብር አጭር ቁጥር
#ethiopia #visionchildrensorganization #childrenssupport #youthempowerment #communitysupport #volunteerism #skillstraining #inclusiveeducation #disabilityinclusion

16 days ago
በጎ ፈቃደኞች የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅትን ጎበኙ
#ethiopia | በጎ ፈቃደኞች የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅትን በመጎብኘት ለህፃናትና ወጣቶች የሚሰጠውን የሙያና የክህሎት ሥልጠና ተመልክተው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
በጉብኝቱ ወቅት ህፃናቱና ወጣቶቹ በሽመና፣ በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በስፖርት፣ በኮምፒዩተርና በኮዲንግ ዘርፎች የሚያዳብሩትን ክህሎትና የሚያከናውኑትን ሥራ ለጎብኚዎቹ አሳይተዋል።
የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ወይዘሮ ሰሎሜ ኩምሳ፣ የተደረገው ጉብኝትና ድጋፍ ለህፃናቱና ድርጅቱ ለሚያከናውነው ሥራ ትልቅ ማበረታቻ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰሎሜ ገለጻ፣ ድርጅቱ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመማር ችግር ላላቸው ወጣቶች የሙያ፣ የኮምፒዩተር፣ የሙዚቃ፣ የሥነ ጥበብና የስፖርት ሥልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ይሰጣል። ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ከ350 በላይ ወጣቶችን መደገፉን ገልጸዋል።
በማዕከሉ ከሰለጠኑ ወጣቶች መካከል 12ቱ የሽመና ሙያ ባለሙያዎች በመሆን ነጠላ፣ ሻርፕና የባህል ልብሶችን እያመረቱ መሆኑም ተገልጿል። ከሙያ ሥልጠናዎች በተጨማሪ ለህፃናቱ የሥነ ልቦናና የሕክምና ድጋፍ እንዲሁም ለወላጆችና መምህራን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።
የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በተጨማሪም ማዕከሉ ሰፋ ያለ ቦታ ቢያገኝ በርካታ ሥራዎችን በማስፋት ብዙ ህፃናትና ወጣቶችን መደገፍ እንደሚችል ገልጿል።
በጎ ፈቃደኞቹ ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር በመሆኑ፣ በቀጣይም ተሳትፎና ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

Comments