5 months ago
በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሥራ ሰዓት ስልክ መጠቀም ተከለከለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ባደረገው አዲስ የአሰራር ለውጥ (ሪፎርም)፣ ሰራተኞች በሥራ ሰዓት የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይችሉ አስታወቀ። እንደ አዲስ አበባ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) ዘገባ፣ ይህ መመሪያ በተለይ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ክፍል ውስጥ በሚሰሩ ባለሙያዎች ላይ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል።
ባለሙያዎች ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ስልካቸውንና የግል ቦርሳቸውን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሎከር ውስጥ ቆልፈው የማስቀመጥ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
ሰራተኞች ደንበኛ እያስተናገዱ ስልክ በመነካካት (social media በመጠቀም) የሚባክነውን ጊዜ ለማስቀረትና ለተገልጋዮች ተገቢውን ክብር ለመስጠት የታለመ ነው።
በቢሮው ውስጥ የሚያገለግሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ደንበኛ ፊት ስልክ መጠቀም ለተገልጋዩ ምቾት አይሰጥም ነበር፤ አሁን ግን ትኩረታቸውን ሥራቸው ላይ ብቻ በማድረጋቸው አገልግሎቱን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን ችለዋል።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሃኑ እንደተናገሩት፣ ይህ አሰራር "ቆይ ስልክ ላንሳ" ወይም "መልዕክት ልመለስ" የሚሉ ሰበቦችን በማስቀረት የተገልጋዮችን እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል።
ይህ ዲጂታል አሰራርን ከሥራ ስነ-ምግባር ጋር ያቆራኘው አዲስ መመሪያ፣ ቢሮውን የቀልጣፋ አገልግሎት ተምሳሌት እንደሚያደርገው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #tradebureau #publicservice #workethics #mobileban #ethiopianews #efficiency

Comments