2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በዛሬው ዕለት ሕይወቷ እንዳለፈ የተነገረው ታዋቂዋ ቲክቶከር ቦኒ (Boni) ከማለፏ በፊት ያስተላለፈችው የመጨረሻ የቪዲዮ መልእክት እና ይህንን ተከትሎ የሥነ-ልቦና ባለሙያው ዶ/ር አበባየሁ አበበ የሰጡት ማሳሰቢያ፣ ማህበራዊ ሚዲያ በአእምሮ ጤና ላይ እያሳደረ ያለውን ከባድ ተጽዕኖ በግልጽ አጉልቶ አሳይቷል።
ቦኒ ህይወቷን ከማጥፋቷ በፊት ባጋራችው አሳዛኝ ቪዲዮ ላይ፣ ከፍተኛ ጥረት አድርጎ አለመሳካት የፈጠረባትን ጥልቅ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ገልጻለች። "ህይወት እናንተ በምትፈልጉት መንገድ አትኖርላችሁም" በማለት የተሰማትን የውስጥ ስብራት ያካፈለችው ቦኒ፣ በመጨረሻም "የዛሬው ቀን የእረፍት ቀኔ ነው" ስትል ተሰናብታለች። በተለይም በመልእክቷ ውስጥ "ለጠላችሁኝ (ላደረጋችሁብኝ) ሁሉ ትቼላችኋለሁ" ማለቷ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይደርስባት የነበረው ጫና እና የጥላቻ አስተያየት ለውሳኔዋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አመላካች ነው።
የቦኒን አሳዛኝ ህልፈት ተከትሎ የኢስት አፍሪካን ዌልነስ ኤንድ ሪሶርስ ሴንተር (East African Wellness and Resource Center,) ዳይሬክተር ዶ/ር አበባየሁ አበበ ለዘ-ሐበሻ በሰጡት የሥነ-ልቦና ትንታኔ፣ ይህ ክስተት ለትውልዱ ትልቅ የማንቂያ ደወል ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። ዶክተሩ የቦኒን ሁኔታ ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃላይ ተጽዕኖ ጋር በማያያዝ አብራርተዋል። በተለይም ቦኒ በመጨረሻ ቃሏ "ለጠላችሁኝ" ብላ እንዳነሳችው ሁሉ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች የሚሰነዝሩት ገንቢ ያልሆነ እና አጥፊ አስተያየት የሰዎችን ስነ-ልቦና በእጅጉ እንደሚጎዳና እስከዚህ ዓይነቱ አሳዛኝ ውሳኔ ሊያደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በተጨማሪም ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የራሳቸውን እውነተኛ ህይወት የሌሎች ሰዎች "ከተዋበ" ህይወት ጋር በማወዳደር ለከፍተኛ ጭንቀት እና ለዝቅተኛ በራስ መተማመን እንደሚዳረጉ ባለሙያው ገልጸዋል። ይህም ቦኒ "ህይወት በምትፈልጉት መንገድ አትኖርላችሁም" ላለችው የከፋ ስሜት አንዱ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው። ቲክቶክን ጨምሮ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንደ አልኮልና ሲጋራ ሱስ የመሆን አቅም እንዳላቸውና የሰውን የአእምሮ ሰላም እንደሚነጥቁ ያስረዱት ዶ/ር አበባየሁ፣ ከዚህ ምናባዊ እውቅና ፍለጋ ወጥቶ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ እና ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ እንዲሁም እውነተኛ የሰዎች ግንኙነትን ማጠናከር ለአእምሮ ጤና ፈውስ መሆኑን አጥብቀው መክረዋል።
የቦኒ አሳዛኝ ህልፈት እና የዶ/ር አበባየሁ አበበ ማሳሰቢያ የሚያስተላልፉት የጋራ መልእክት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ዓለም ከሚሰጠው ጊዜያዊ ደስታና እውቅና ጀርባ፣ አጠቃቀማችንን በጥንቃቄ ካልመራነው የሰውን ነፍስ ሊያቆስልና ህይወት ሊቀጥፍ የሚችል ከባድ አደጋ እንዳለው ነው። ስለሆነም የአእምሮ ጤናችንን ለመጠበቅ ከማህበራዊ ሚዲያ ይልቅ ለገሃዱ ዓለም ህይወታችንና ግንኙነታችን ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል።
የቦኒ አሳዛኝ ሞት.... VOEA Television ዩቱብ ቻናል ላይ ዶ/ር አበባየሁ አበበን ተመልከቱ።

ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን አዲስ የአካል ብቃትና ሥነ-ምግብ መጽሐፍ አስመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘርፍ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን፣ ሳይንሳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከሥነ-ምግብ መመሪያዎች ጋር አቀናጅቶ የያዘውን “አካል በብቃት” የተሰኘ ሦስተኛ መጽሐፉን በትላንትናው እለት በይፋ ለንባብ አብቅቷል።
ቀደም ሲል ካሳተማቸው "የስፖርት ማሽን አጠቃቀም" እና "ስፖርት ያለ መሳሪያ" መጽሐፍት ቀጥሎ የቀረበው ይህ አዲስ ሥራ፣ በተለይም በሥራ ጫና ምክንያት ወደ ስፖርት ማዕከላት መሄድ ለማይችሉ የከተማ ነዋሪዎች እንደ ዋነኛ መመሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።
ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ባሉበት ቦታና በተመቻቸው ስፍራ ሆነው ጤናቸውን መጠበቅ እንዲችሉ ዝርዝር ትንታኔዎችን ያካተተው ይህ መጽሐፍ፣ ስፖርት መሥራት ለጥቂቶች ሳይሆን ለሁሉም የጤና ዋስትና መሆኑን በማስገንዘብ “ጊዜ የለኝም” የሚለውን የተለመደ ሰበብ ለመቅረፍ ያለመ ነው።
ለታሪክ አድቨርታይዚንግ እና ህትመት ወደ ንባብ ያመጣውና በ11 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ250 ገፆች የተቀነበበው ይህ መጽሐፍ፣ በ1,199 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በውስጡም የሕፃናት የአካል ብቃት፣ የባህላዊ ጭፈራ ከስፖርት ጋር ያለው ሳይንሳዊ ትስስር እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሞክሮ ተካቶበታል።
ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን በመጽሐፍ ዝግጅትና በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የአካል ብቃትን የኅብረተሰቡ የዘወትር ባህል ለማድረግ የጀመረውን የተቀደሰ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በምረቃው ወቅት ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #fitness #health #nutrition #dawitmekonnen #newbook #exercise #wellness

4 months ago
ማስተር ሄኖክ 90 ቀናት ሁለት ዘመናዊ የጂም ማእከላትን በአንድ ቀን አስመረቀ!
#fastmereja I ላለፉት 10 ዓመታት "90 ቀናት ከማስተር ሄኖክ ጋር“ በሚለው ፕሮግራሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ሲቀይር የቆየው ብሬቩ ዌልነስ (Breve Wellness) በትላንትናዉ እለት ሁለት ግዙፍ እና ዘመናዊ የጂም ማእከላትን በአዲስ አበባ ከተማ አስመርቋል።
አዲሶቹ እና በከፍተኛ በጀት ተገንብተዉ የተመረቁት ዘመናዊ የጂም ማእከላት በሳር ቤት እና በሰሚት አካባቢ ነዉ የተከፈቱት።
እነዚህ ማእከላት ተራ የጂም ስፍራዎች ብቻ አይደሉም፤ የላቀ የአካል ብቃት ስልጠና (Fitness)፣ ሳይንሳዊ የስርዓተ ምግብ ምክር (Nutrition)፣የህይወት ክህሎት እና የስነ-ልቦና ስልጠና (Life Skills) ሲቪል ሰርቫንቱን እና ወጣቱን ያማከለ ሁለንተናዊ የለውጥ ማእከል መሆናቸዉን የብሬቩ ዌልነስ መስራች ማስተር ሄኖክ ኪዳነወልድ ገልጿል።
ማስተር ሄኖክ አክሎም አዲስ አበባን የአፍሪካ መዲና ብቻ ሳይሆን የስፖርት ስበት ማዕከል ለማድረግ ያለዉን ራዕይ እንዲሁም ቁርጠኝነት ፀልጿል።
በወዳጅነት ፓርክ 10,000 ሰዎችን በነፃ በማሰልጠን የጀመረው ይሄው የጤና ንቅናቄ፣ አሁን ደግሞ በላቀ ቴክኖሎጂ እና ምቹ ሁኔታ ስልጠናውን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር እነዚህን ዘርፈ ብዙ የጂም ማዕከላት ለመገንባት መቻሉ ነዉ የተገለፀዉ።
በምረቃው ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ኮሚሽነር በላይ ደጀንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የስፖርት አፍቃሪዎች እና የማስተር ሄኖክ ተማሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።
እንዲሁም በቅርብ ጊዜያት ተደራሽነቱን በይበልጥ ለማስፋት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

10 months ago
📢 ነፃ የጤና ምክር ፣ ምርመራና ህክምና ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል!
📍ትጉሀኑ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ባለሙያዎች በበጎ ፈቃድ ፣ በፍቅርና በፍፁም ቅንነት ነፃ የጤና ምክር ፣ ምርመራና ህክምና አገልግሎት በየካ ክፍለ ከተማ አዳራሽ እየሰጡ ነው!
ሁላችሁም ተጋብዛቹዋል!!!!
📍 ቦታ፡ የካ ክፍለ ከተማ አዳራሽ
📅 ቀን፡ ከሐምሌ 30 - ነሀሴ 6/2017
🕘 ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ምሽት 12:00
አገልግሎቶቹ፡
✅አጠቃላይ ምርመራዎች
የስኳርና የደም ግፊት ምርመራ
የልብ ምርመራ
ሁሉም የጤና ደህንነት ምርመራዎች/WELLNESS CHECK-UPS…
✅የጤና ምክር/ Counselling እና የጤና ትምህርት ) /psycho-social Services,
✅የጡት ካንሰር ምርመራ ፤ የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ
✅ልዩ እንክብካቤ (የሴቶች ጉዳይ እና የአካል ጉዳት እንክብካቤ አገልግሎቶች)
✅የውስጥ ደዌ ህክምና
✅የህፃናት ህክምና አገልግሎቶች
የአመጋገብ ምርመራ
የዕድገት ክትትል
✅የቆዳ ህክምና አገልግሎቶች
✅የዓይን ሕክምና አገልግሎቶች
✅የማህፀንና ፅንስ ህክምና
✅የመለስተኛ ቀዶ-ህክምና
✅የጥርስ ህክምና
✅የአእምሮ ህክምና
✅የቲቢ እና ኤች አይቪ ምርመራ
✅የላቦራቶሪ አገልግሎት
✅የመድኃኒት አገልግሎት
✅ራዲዮሎጂ/ኢሜጂንግ አገልግሎቶች
(ኤምአርአይ/MRI
ሲቲ-ስካን፣/CT-SCAN
ኤክስ-ሬይ፣ /X-RAY
አልትራሳውንድ፣/ULTRASOUND
ኢሲጂ፣ /ECG
ማሞግራፊ፣/MAMOGRAPHY
ኢኮካርዲዮግራፊ/ECHOCARDIOGRAPHY
✅የፊዚዮቴራፒ አገልግሎቶች
✅የድንገተኛ ህክምና እና አምቡላንስ አገልግሎቶች
በመርሀግብሩ ላይ ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር፣ ፓዮኔር ዲያግኖስቲክ ሴንተር እና ያኔት አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራዎችን በመስጠት የአጋርነት ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
☎️ 952 ነፃ መስመር ይደውሉ!
"የአገልግሎት ጥራት አርማችን!"
#ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል

Sponsored by
Surafel
Comments