Logo
FastMereja
ማስተር ሄኖክ 90 ቀናት ሁለት ዘመናዊ የጂም ማእከላትን በአንድ ቀን አስመረቀ!
#fastmereja I ላለፉት 10 ዓመታት "90 ቀናት ከማስተር ሄኖክ ጋር“ በሚለው ፕሮግራሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ሲቀይር የቆየው ብሬቩ ዌልነስ (Breve Wellness) በትላንትናዉ እለት ሁለት ግዙፍ እና ዘመናዊ የጂም ማእከላትን በአዲስ አበባ ከተማ አስመርቋል።

አዲሶቹ እና በከፍተኛ በጀት ተገንብተዉ የተመረቁት ዘመናዊ የጂም ማእከላት በሳር ቤት እና በሰሚት አካባቢ ነዉ የተከፈቱት።

እነዚህ ማእከላት ተራ የጂም ስፍራዎች ብቻ አይደሉም፤ የላቀ የአካል ብቃት ስልጠና (Fitness)፣ ሳይንሳዊ የስርዓተ ምግብ ምክር (Nutrition)፣የህይወት ክህሎት እና የስነ-ልቦና ስልጠና (Life Skills) ሲቪል ሰርቫንቱን እና ወጣቱን ያማከለ ሁለንተናዊ የለውጥ ማእከል መሆናቸዉን የብሬቩ ዌልነስ መስራች ማስተር ሄኖክ ኪዳነወልድ ገልጿል።

ማስተር ሄኖክ አክሎም አዲስ አበባን የአፍሪካ መዲና ብቻ ሳይሆን የስፖርት ስበት ማዕከል ለማድረግ ያለዉን ራዕይ እንዲሁም ቁርጠኝነት ፀልጿል።

በወዳጅነት ፓርክ 10,000 ሰዎችን በነፃ በማሰልጠን የጀመረው ይሄው የጤና ንቅናቄ፣ አሁን ደግሞ በላቀ ቴክኖሎጂ እና ምቹ ሁኔታ ስልጠናውን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር እነዚህን ዘርፈ ብዙ የጂም ማዕከላት ለመገንባት መቻሉ ነዉ የተገለፀዉ።

በምረቃው ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ኮሚሽነር በላይ ደጀንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የስፖርት አፍቃሪዎች እና የማስተር ሄኖክ ተማሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።

እንዲሁም በቅርብ ጊዜያት ተደራሽነቱን በይበልጥ ለማስፋት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.