ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን አዲስ የአካል ብቃትና ሥነ-ምግብ መጽሐፍ አስመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘርፍ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን፣ ሳይንሳዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከሥነ-ምግብ መመሪያዎች ጋር አቀናጅቶ የያዘውን “አካል በብቃት” የተሰኘ ሦስተኛ መጽሐፉን በትላንትናው እለት በይፋ ለንባብ አብቅቷል።
ቀደም ሲል ካሳተማቸው "የስፖርት ማሽን አጠቃቀም" እና "ስፖርት ያለ መሳሪያ" መጽሐፍት ቀጥሎ የቀረበው ይህ አዲስ ሥራ፣ በተለይም በሥራ ጫና ምክንያት ወደ ስፖርት ማዕከላት መሄድ ለማይችሉ የከተማ ነዋሪዎች እንደ ዋነኛ መመሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።
ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ባሉበት ቦታና በተመቻቸው ስፍራ ሆነው ጤናቸውን መጠበቅ እንዲችሉ ዝርዝር ትንታኔዎችን ያካተተው ይህ መጽሐፍ፣ ስፖርት መሥራት ለጥቂቶች ሳይሆን ለሁሉም የጤና ዋስትና መሆኑን በማስገንዘብ “ጊዜ የለኝም” የሚለውን የተለመደ ሰበብ ለመቅረፍ ያለመ ነው።
ለታሪክ አድቨርታይዚንግ እና ህትመት ወደ ንባብ ያመጣውና በ11 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ250 ገፆች የተቀነበበው ይህ መጽሐፍ፣ በ1,199 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በውስጡም የሕፃናት የአካል ብቃት፣ የባህላዊ ጭፈራ ከስፖርት ጋር ያለው ሳይንሳዊ ትስስር እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሞክሮ ተካቶበታል።
ኢንስትራክተር ዳዊት መኮንን በመጽሐፍ ዝግጅትና በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የአካል ብቃትን የኅብረተሰቡ የዘወትር ባህል ለማድረግ የጀመረውን የተቀደሰ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በምረቃው ወቅት ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #fitness #health #nutrition #dawitmekonnen #newbook #exercise #wellness

4 months ago
Administrator
4 months ago
Replying to Getu Temesgen's post
Administrator sent a gift of 12$