20 hours ago
አሳዛኝ የሐዘን ዜና | የሊዮኔል ሜሲ አባት ሆርሄ ሜሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
የዓለማችን ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት እና ዋና ወኪል የሆኑት ሆርሄ ሜሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ ሆኗል።
የልጁን ስኬታማ የእግር ኳስ ህይወት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በቅርበት ሲመሩ የቆዩት አባት ሆርሄ ሜሲ፣ በትውልድ ከተማቸው ሮዛሪዮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርብ ነሐሴ 01 (August 7) ምሽት 4:00 ገደማ ሕይወታቸው ማለፉን የሜሲ ቤተሰቦች እና የአርጀንቲና መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል።
እንደ ዴይሊ ሜይል (Daily Mail) እና ዘ ሰን (The Sun Football) ዘገባዎች ከሆነ፣ ይህ መረጃ በቤተሰቦቹ በኩል ይፋ የተደረገ እና ተረጋገጠ ነው።
ሆርሄ ሜሲ ላለፉት በርካታ ወራት ከልብ እና ከነርቭ ህመም ጋር ተያይዞ በጽኑ ሲታመሙ የቆዩ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው የህክምና ሁኔታቸውን ከሚዲያ እይታ ውጪ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ሜሲ በሜዳ ላይ ያሳየው የተለየ የሐዘን ስሜት እና እንባ፣ ከአባቱ የጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይታወቃል።
ሆርሄ ሜሲ ለአልቢሴሌስቴው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የአባትነት ሚናቸውን ከመወጣት ባለፈ፣ ገና በወጣትነቱ ከሮዛሪዮ እስከ ባርሴሎና እና ባሻገር ላስመዘገባቸው ድንቅ ስኬቶች እና ግዙፍ የቢዝነስ ግዛቶች ዋና መሃንዲስ በመሆን የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።
ይህ ወቅት ለሜሲ ቤተሰቦች እና ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ እጅግ ከባድ አጋጣሚ በመሆኑ፣ ለሊዮኔል ሜሲ፣ ለእናቱ ሴሊያ ኩቺቲኒ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።
ነፍስ ይማር!
Via Daily Mail , The Sun Football
Seledadotio

24 hours ago
በኮሬ ዞን የገዛ ባሏን የገደለችው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅን እስራት ተቀጣች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማለ ወረዳ ደርባ ማናና ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ወካለ ወይም ወይዶ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል።
ተከሳሽ ተስፋይነሽ ዘለቀ የተባለች ሲሆን ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ ድርጊቱን ፈጽማለች።
ተከሳሽ ከትዳር አጋሯ ሳሪያ ጋር በተነሳ አለመግባባት ምክንያት ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ እንደተሰወረች ተገልጿል።የትዳር አጋሯም ተከሳሽን ለመፈለግ ወደ ጎረቤት ቤት ሲሄድ ወደዚያ አልመጣችም የሚል ምላሽ ያገኛል። በመቀጠልም ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ በጓሮ በኩል ባትሪ እያበራ ሲፈልጋት ተከሳሽ ተደብቃ በነበረችበት ቦታ አጠገቧ እያለፈ እያለ ይዛዉ በነበረው ቆጮ መቁረጫ የቀኝ አንገቱን አንድ ጊዜ በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፖሊስም ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል የክስ መዝገቧን ለአቃቤ ህግ ያቀርባል።
አቃቤ ህግም ተከሳሽ በፈፀመችው ከባድ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶ ለፍርድ ቤት ያቀርባል።
ፍርድ ቤቱም ተከሻሽ ጥፋተኛ መሆኗን በቀረበለት የክስ መዝገብ በማጣራት በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via በሳምራዊት ስዩም
©️ዳጉ_ጆርናል #viagem

1 day ago
"A new Ethiopian star is born; her name is Almaz Yohannis አዲስ የኢትዮጵያ ኮከብ ተወለደች፤ ስሟም አልማዝ ዮሐንስ ነው" የተባለላት አትሌት ከአትሌት በላይነህ ዲንሳሞ፣ ቱርቦ ቱሞ እንዲሁም ከአትሌት ሳሙኤል ፍሬው የትውልድ ሀገር ሲዳማ የተገኘች አትሌት ናት።
ከዚያ ምድር በዚህ ዕድሜ፣ በአለም አደባባይ የሀገሯን ስንደቅ ከፍ የምታደርግ አትሌት እንደምትገኝ ማን አስቦ ኖሯል? Maganu galatamo አለች አፏን በፈታችበት በሲዳሙ አፎ። ለዛሬ አማርኛ ይቅርታ ያድርግልኝ ብላ ቃለ መጠይቋን ልብ በሚነካ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆና በሲዳምኛ ገለፀችው። ቀጥላም ባሳለፈችበት የአትሌቲክስ ሕይወት ገና በጠዋቱ አቅሟን አይቶ ለዚህ ታላቅ ገድል ያጫትን አሰልጣኝ ሳሙኤል በቀለን አመሰገነች። ሳሙኤል በቀለ ከዛሬ አሥራ ስምንት ዓመት በፊት በጎዋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት መምህር የሥራ ባልደረባዬ ነበር። ሳሙኤል በቀለ ከአርቤጎና ምድር ብዙ አትሌቶችን ያፈራ ነባር የአትሌትክስ አሰልጣኝ ነው። አልማዝ ቀጠለች ከሁላ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ አዱላንና እና አሰልጣኞዋን አሰፋ ጋዲሳን አመሰገነች። በቀጣይ የአትሌትክስ ሕይወቷ ኦሎምፒክ ማሸነፍ ህልሟ መሆኖዋንም ተናገረች። እንኳን Magano ረዳት። ሀሹ!!
Athlet Almaz Yohanis hawalle Maganu kaa'linohe!
Via: ሳሙኤል በላይነህ

የጆኒ እና ሴዶ MMA ፍልሚያ መግቢያ ትኬት VVIP 100 ሺ ብር መሆኑ ተገለፀ::
ቀን: ነሐሴ 21
ቦታ: አድዋ 00 ሙዚየም (Adwa 00 Museum)
ቲኬት ለመግዛት: በ M-Pesa
የቲኬት ዓይነቶች እና ዋጋ:
1. VVIP Ringside - 100,000 የኢትዮጵይ ብር
* ልዩ የሪንግ አጠገብ መቀመጫ
* ያልተገደበ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት
* ወደ ተወዳዳሪዎች ልብስ መቀየሪያ ክፍል የመግባት እድል
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
2. VVIP Premium - 50,000 የኢትዮጵይ ብር
* 2ኛ ተከታታይ ረድፍ መቀመጫ
* 2 የምግብ እና 10 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
3. VVIP Normal - 30,000 የኢትዮጵይ ብር
* ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ረድፍ መቀመጫዎች
* 2 የምግብ እና 7 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
4. VIP - 20,000 የኢትዮጵይ ብር
* 1 የምግብ እና 4 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
5. Regular - 10,000 የኢትዮጵይ ብር
6. Early Bird - 4,000 የኢትዮጵይ ብር
(በተወሰነ ቁጥር የቀረበ)
ቲኬትዎን አሁኑኑ በ M-Pesa ይቁረጡ!
ቲኬቱም እያለቀ ነው ተብሏል.......
Via ETFC
Seledadotio
Seledadotio
ቀን: ነሐሴ 21
ቦታ: አድዋ 00 ሙዚየም (Adwa 00 Museum)
ቲኬት ለመግዛት: በ M-Pesa
የቲኬት ዓይነቶች እና ዋጋ:
1. VVIP Ringside - 100,000 የኢትዮጵይ ብር
* ልዩ የሪንግ አጠገብ መቀመጫ
* ያልተገደበ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት
* ወደ ተወዳዳሪዎች ልብስ መቀየሪያ ክፍል የመግባት እድል
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
2. VVIP Premium - 50,000 የኢትዮጵይ ብር
* 2ኛ ተከታታይ ረድፍ መቀመጫ
* 2 የምግብ እና 10 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
3. VVIP Normal - 30,000 የኢትዮጵይ ብር
* ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ረድፍ መቀመጫዎች
* 2 የምግብ እና 7 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
4. VIP - 20,000 የኢትዮጵይ ብር
* 1 የምግብ እና 4 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት
5. Regular - 10,000 የኢትዮጵይ ብር
6. Early Bird - 4,000 የኢትዮጵይ ብር
(በተወሰነ ቁጥር የቀረበ)
ቲኬትዎን አሁኑኑ በ M-Pesa ይቁረጡ!
ቲኬቱም እያለቀ ነው ተብሏል.......
Via ETFC
Seledadotio
Seledadotio
Sponsored by
Surafel
2 days ago
ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ወንዶች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !
ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።
ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው...
በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።
ይሄንን መሰል አፀያፊ ተግባር እንዳይከሰት መፍትሔ ግን ምን ይሆን ? በጣም አስደንጋጭ ነው ።
Via፦ የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ኮምኒኬሽን

3 days ago
በሙስናና ሕገ-ወጥ አሠራር የተሳተፉ አካላት ላይ የሕግ እርምጃ ተወሰደ
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ።
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፈጣን ልማትና ዕድገት እንድታረጋግጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም ሰፋፊና አስደናቂ ሀገራዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሂደት ግን ይህ ውጤት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር አመላክተዋል። ከተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሻገር፣ ሕገ-ወጥነት እና የሙስና ተግባራት የልማቱ ዋነኛ ፈተና ሆነው መቆየታቸውንም ክብርት ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ የሕገ-ወጥነት ችግር በአንድ ወገን ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸው ከውስጥም ከውጪም ያሉ በርካታ ኃይሎች በተደራጀ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበር። በንግዱ ማኅበረሰብ፣ በልማት ድርጅቶች፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በግለሰቦች እና በተገልጋዮች ጭምር በተደራጀ መንገድ በስፋት የሚታይ ነው።
እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዐቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጽሙ ቆይተዋል" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ድርጊቱ ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ፣ የዋጋ ንረትና ኮንትሮባንድ እንዲባባስ እንዲሁም በፍጆታ እቃዎች ላይ ሰው ሠራሽ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን የተደራጀ አሻጥር ለመግታት መንግሥት እና የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን አሻጥሩን ማክሸፍ መቻሉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት ረገድ መንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ እናትዓለም በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ የፈጸሙ እና ተቋማዊ አሻጥር በሠሩ አመራሮች እና ሌሎች የጥቅም ትስስሮችና ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። በተለይም በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት ሰፍኗል ሲሉ ገልጸዋል።
በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሙስና እና አሻጥር ወንጀሎችን ለማረም በተወሰዱት ሰፊ ኦፕሬሽኖች እና ሕግ የማስከበር እርምጃዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ በማሰብ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ እንዲንር ሲያደርጉ የነበሩ 13 አቅራቢ ድርጅቶች ባለቤቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፤ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ ከ7 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል።
በፋይናንስ ተቋማት እና የገንዘብ ዝውውር፡ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓል።
ለሕገ-ወጥ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ የነበሩ 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ ታግደዋል፤ ምርት ልከው የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ያላደረጉ 29 ላኪ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የህግ ተጠያቂነት ሰፍኗል።
በቤቲንግ እና ፊንቴክ ቢዝነሶች፡ የደንበኞችን መረጃ በመደበቅ መንግሥትን ግብር ያጭበረበሩ፣ ገቢያቸውን የሰወሩ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በፈጸሙ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዶ ባለቤቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ የእነዚህ ሕገ-ወጥ ተቋማት የባንክ ሒሳብ ታግዷል፤
በማዕድን ዘርፍ ሕገ-ወጥ ዝውውር፡ የወርቅ ምርትን ከገበያ ውጭ በኮንትሮባንድ በማስወጣት ወንጀል የተሳተፉ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን፣ አምራቾችን እና የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 183 ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ተደርገዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሕገ-ወጥ ወርቅ፣ የወርቅ ሚዛንና ማቅለጫ፣ የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጂስቲክስ አንጻር፡ በሕገ-ወጥ መንገድ የሽፋን ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት፣ ነዳጅ በመደበቅ እና አየር በአየር በመሸጥ ወንጀል የተሳተፉ 38 የመንግሥት አመራሮች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከ650 በላይ ግለሰቦች፣ ማደያዎች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ የህግ እርምጃ ተወስዷል።
በአፈር ማዳበሪያ ግዢ አሻጥር፡ በተቋሙ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ጥራት የጎደለውና ጊዜው ያለፈበት የአፈር ማዳበሪያ ግዢ እንዲፈጸም በማድረግ ሆን ብለው ችግር በፈጠሩ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ላይ የወንጀል ተጠያቂነት እርምጃ ተወስዷል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP)፡ ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት የፈጸሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እንዲሁ በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የሰዎች ዝውውር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሲስተምን በማዛባት እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ 8 ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እንዲሁም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ 44 ደላሎች እና አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ፣ ሕገ-ወጥ ፈቃድ የነበራቸው ተቋማት ሙሉ በሙሉ ታሽገዋል።
በገቢዎችና ጉምሩክ ዘርፍ፡ የግብር ውሳኔዎችን በመቀነስ፣ ሐሰተኛ ደረሰኞች በማወራረድ፣ እና በሲስተም መረጃ በማጥፋት የመንግሥት ገቢን ባሳጡ አካላት ላይ ኦፕሬሽን ተካሂዷል።
በራሳቸው፣ በዘመድ እና በሹፌሮቻቸው አካውንት በመጠቀም የጥቅም ትስስር የፈጠሩ 109 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከእነዚህ መካከል 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት እንደማንኛውም ፈተና በጽናት እየተጋፈጣቸው መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።
መንግሥት ሌብነትን ለማጥፋት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት እና በዲሲፕሊን የታነጸ አመራር ለመገንባት ቁርጠኛ ነው" ያሉት ወይዘሮ እናትዓለም፤ ሕዝቡ በስፋት የሚያነሣቸውን "ሌብነትን አስቁሙልን" ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረዉ ጠንካራ እርምጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ፣ ሕጋዊ መብቱን በመደለያ ባለመጠየቅ እና ከሕገወጦች ጋር ባለመተባበር ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገርን ከሕገወጥነትና ሙስና የመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
Via EBC

ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለምትወክለው ሞዴል ሩት ይርጋለም የእንኳን ደስ አለሽና የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ።
ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሞዴሏ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ በድል እንድትመለስ ተመኝተዋል።
ክብርት ሸዊት በንግግራቸው ሞዴሏ የባህል አምባሳደር ሆና ከተሾመች በኋላ የሀገሪቱን ብዝሃ ባህላዊ ዕሴቶች በቅርበት ለመረዳት በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ማድረጓን አንስተዋል።
በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ በመገኘት የህዝቡን ባህል፣ በአማራ ክልል ጎንደር በመሄድ የክልሉን ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ በመገኘት የገዳ ስርዓትንና ድቅ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን በበቂ ሁኔታ ጎብኝታለች ብለዋል።
ይህ በክልሎች ያደረገችው ቆይታ የሀገሪቱን ባህልና ጥበብ ጠልቃ እንድታውቅ የረዳት ሲሆን፣ ከ130 በላይ የዓለም ሀገራት ሞዴሎች በሚሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያን በብቃት ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዛት ገልፀዋል።
የገጠማትን ማንኛውንም ፈተና ተቋቁማ የሀገሯን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ አደባባይ ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ጠንካራ ወጣት በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እንደሚገባትም ክብርት ሸዊት ሻንካ አክለዋል።
ክብርት ሸዊት ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው መልዕክት በመጪው ውድድር ላይ በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ (Link) አማካኝነት ሁሉም ድጋፉን እንዲሰጥና ለሞዴሏ ስኬት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ሞዴል ሩት ይርጋለም በበኩሏ ለተደረገላት የሸኝትና መልካም ምኞት መርሀ ግብር ምስጋና አቅርባለች።
ሞዴሏ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ቆርጣ እንደተነሳች በመግለፅ የገጠማት ችግር ወደሗላ እንደማይመልሳት አንስታለች።
ከዓለም አቀፉ ውድድር በሗላም በሀገሯ ያሉ ባህላዊና ጥበባዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ እደምሰራ ገልፃለች።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ሴክተር አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና የሞዴሏ ቤተሰቦች ተገኝተው ለሞዴሏ የሀገር አደራ ተሰጥቷል።
Via የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

4 days ago
በትግራይ በዘውዱ ሀፍቱ ግድያ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ከእስር መፈታታቸውን 'ይኾኖ' ማህበር አስታወቀ
በትግራይ ክልል ወጣት ዘውዱ ሀፍቱን በመግደል ወንጀል በእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ከእስር መፈታታቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅት 'ይኾኖ' (Yikhono) አስታወቀ።
እንደ ማህበሩ ገለፃ፣ ሁለቱ ግለሰቦች በፈጸሙት ዘግናኝ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው የጽኑ እስራት ውሳኔ ከተላለፈባቸው ገና አንድ ወር ያህል እንኳ ሳይሞላው ነው ከእስር ነፃ የወጡት።
ዕድሜዋ 32 የነበረችው ዘውዱ ሀፍቱ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በታቀደ ጥቃት በህዝብ ፊት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ እና በመኪና በመጨፈለቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።
ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ውስጥ፦
በዳኞች ላይ ይደርስ የነበረ ዛቻ እና በችሎት ውስጥ የተፈጠሩ ረብሻዎች ሂደቱን ሲያስተጓጉሉት መቆየታቸው ተገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነታቸውን በማረጋገጥ ያለ ምንም ይቅርታ (ይግባኝ) የዕድሜ ልክ እስራት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።
ከእስር ተፈተዋል የተባሉት ተከሳሾች ያሬድ ገብረሥላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያም ሲሆኑ፣ ያሬድ በወቅቱ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የ22ኛ ሰራዊት አዛዥ ሆነው የሚያገለግሉት የኮሚሽነር ገብረሥላሴ በላይ ልጅ እንደሆነ ተገልጿል።
የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ቤተሰቦች እንደሚያስረዱት፣ በምርመራው እና በፍትህ ሂደቱ ወቅት የባለስልጣናት ተፅዕኖ እና ጣልቃ ገብነት እንደነበር ጠቁመዋል።
የግለሰቦቹ ከእስር መፈታት በክልሉ የፍትህ ስርዓት እና በሕግ የበላይነት ላይ ትልቅ ጥያቄ ማስነሳቱን የጠቆመው 'ይቅኖ' ማህበር፣ ውሳኔው የሴቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ #justiceforzewdu በሚሉ ሃሽታጎች ለወጣት ዘውዱ ሀፍቱ ፍትህ እንዲረጋገጥ፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ በሚገቡ ባለስልጣናት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪዎች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።
Via ጉርሻ page

በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡
በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ።
ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ።
በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡
በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ።
የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው
እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል።
በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
Via Sheger Fm

5 days ago
ይህን እሽግ እንደተራ መክሰስ ለገበያ ማቅረብ ወንጀል ነው!
#ethiopia | በከባድ የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናትን ሕይወት ለማዳን የሚሰጠው አጣዳፊ የምግብ መድኃኒት (RUTF) ወይ በተለምዶ ስሙ ፕላምፕሌት በገበያ ላይ ለንግድ መቅረቡና ለክብደት መጨመሪያ መዋሉ ከፍተኛ የሞራልና የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ወንጀል መሆኑ ተገለጸ።
በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ሕፃናትን ለማዳን በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀውን ይህን ሕይወት አድን እሽግ እንደ ተራ መክሰስ ለገበያ ማቅረብ በእርግጥም ህክምናው ለሚገባቸው ሕፃናት የሚደርሰውን እርዳታ በመንጠቅ ሕይወታቸውን ለሞት አደጋ የሚያጋልጥ ተግባር ነው።
በሌላ በኩል ይህ ምርት በካሎሪ፣ በቅባትና በቫይታሚኖች እጅግ የበለፀገ በመሆኑ ጤናማ ሰዎች ሳያስፈልጋቸው ሲመገቡት ለከፍተኛ የኩላሊትና የጉበት ጫና፣ ለደም ስኳርና ቅባት መዛባት እንዲሁም ለቫይታሚን መርዝነት ያጋልጣቸዋል።
በመሆኑም በነፃ ወይም በሕክምና ተቋማት በኩል ለተቸገሩ ሕፃናት የተላከን እርዳታ መሸጥም ሆነ መግዛት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል በመሆኑ፣ ሕይወት አድን መድኃኒቶች የንግድ ዕቃ አለመሆናቸውን ተረድቶ ኅብረተሰቡ ከዚህ ድርጊት ሊቆጠብ እንደሚገባ መልእክት ተላልፏል።
(via ጤና)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

6 days ago
የቢሾፍቱው ግዙፍ ኤርፖርት የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቅ ስምንት ወራት ይፈጃል ተባለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ለሚገነባው አዲስ ሜጋ ኤርፖርት የሚያስፈልገውን የቢሊዮን ዶላር ብድር የማጽደቅ ሂደት ስምንት ወራት እንደሚፈጅና እስከ መጋቢት 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
አየር መንገዱ የመሬት መንጥር እና የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጠናቀቃቸውን ገልጿል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት፣ የግንባታ ተቋራጮች ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቃቸው የኮንትራክተሮች መረጣ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከነሐሴ ወር ወደ መጪው ጥር መራዘሙን አስረድተዋል።
Via capital

በኦቶና ሆስፒታል የላብራቶሪ መሳሪያዎችን ሊሰርቅ የነበረ የጥበቃ ሰራተኛ እጅ ከፍንጂ ተያዘ
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና) ሦስት ወሳኝ የላብራቶሪ ማይክሮስኮፖችን አውጥቶ ለመሰወር ሲሞክር የነበረ የጥበቃ ሰራተኛ በተረኛ ጥበቃዎች ብርቱ ክትትልና ተጋድሎ እጅ ከፍንጂ መያዙ ተገለጸ።
በትላትናው እለተ የተፈጸመው ይህ ድርጊት ተራ የሕክምና ዕቃ ስርቆት ሳይሆን፣ የሺዎችን ሕይወት እና የሆስፒታሉን ዕለታዊ የሕክምና አገልግሎት ቀጥተኛ አደጋ ላይ የጣለ ከባድ ወንጀል መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ የሕክምና መገልገያዎቹን ደብቆ ከሆስፒታሉ ግቢ ሊያወጣ ሲል በተረኛ ባልደረቦቹ ንቁ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል። ድርጊቱ በግለሰቡ ብቻ የተፈጸመ ሳይሆን በጀርባ ያሉ አመቻቾችና አቀናባሪዎች እንዳሉበት በመጠረጠሩ፣ ወንጀሉን ያስተባበሩ አካላት በሙሉ ተለይተው ተገቢው የሕግ ትርጉም እንዲሰጣቸውና አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።
በአንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ማይክሮስኮፕ ማለት የተደበቁ በሽታዎችን አውጥቶ በማሳየት የሕሙማንን ሕይወት የሚያስጥል ዋና መመርመሪያ መሳሪያ ነው።
እነዚህን መገልገያዎች ማጣት በሕሙማን ላይ የሚከተሉትን ከባድ የጤና አደጋዎች ያስከትላል፦
እንደ ወባ፣ ቲቢ እና የተለያዩ ከባድ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን በፍጥነት በመመርመር አስቸኳይ የሕክምና ውሳኔ ለመስጠት ያገለግላሉ።
የደም ማነስን (Anemia) እና የደም ካንሰርን (Leukemia) በጥንቃቄ ለይቶ ለማወቅ ወሳኝ መገልገያዎች ናቸው።
እነዚህ መሳሪያዎች ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ የላብራቶሪ ውጤቶች ይዘገያሉ፤ ይህም በተለይ በፅኑ ሕሙማን፣ በሕፃናትና ነፍሰ ጡራት ሕይወት ላይ የቀጥታ አደጋ ይደቅናል።
የሕዝብና የመንግሥት ሀብት የሆኑትን የሕክምና መገልገያዎች ከስርቆትና ከእጅ አዙር ሴራ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የታየው የተረኛ ጥበቃዎች ንቅናቄ የሚደነቅ ሲሆን፣ የወንጀሉ ተሳታፊዎች በሙሉ ለሕግ እንዲቀርቡ የጀመረው ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

8 days ago
ከታች ያለው የአርሚ 70 አባል የፃፈው ነው!
ሸረሪና! አርሚ 70!
"አንድ የአርሚ 70 አባል የሆነ የቤተሰቤ አባል ከሱዳን ወሰን ሸረሪና አካባቢ ደውሎልኝ ነበር።
ዛሬ ማታ ሑመራ እንገባለን፤ ተዘጋጁ የሚል ትዕዛዝ ወርዶልናል።
ሙሉ ሌሊት ስንጓዝ አድረናል። ሲነጋ አካባቢ የመጣበት ቦታ የማይታወቅ፣ ከሰማይ ሲወርድ ምንም ድምፅ የሌለውና መሬት ላይ ሲያርፍ ብቻ ድምፅ የሚያሰማ ተኩስ ይፈነዳ ጀመር። ሩቅ ሆነን ስናያቸው የነበሩ የመካናይዝድ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ማለት ይቻላል ተቃጥለው እሳት ሲነድ ብቻ ይታያል።
እግረኛ የሆንነው ደግሞ የመካናይዝድ ተሽከርካሪዎች እየጠፋ እንደሆነ ስለተረዳን ሁላችንም ተበታትነናል። ከእኛ ጋር አንድ የሬዲዮ ኦፕሬተር እና የሬዲዮ መገናኛ የያዘ አለ፤ ነገር ግን ከኃላፊዎች የደረሳቸው ምንም ዓይነት መረጃ የለም።
ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እጃችንን እንዳንሰጥ በፊታችን የሚታይ ሠራዊት የለም። ጨንቆናል!
እኔም የምናገረው ጠፍቶኛል!!
የህወሓት ቡድን አፈቀላጤዎች ስራችሁን ስለጀመራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
via wedi shambel

እነዚህ ከላይ በቪዲዮ የምታያቸው ህፃናት በአረብ ሀገር ተሰዳ እረጅም አመት አብራቸው የነበረች ሰራተኛ ኮንትራቷን ጨርሳ ወደ ሀገሯ ስትመለስ ሲያለቅሱ እሚያሳይ ቪዲዮ ነው። እሚያለቅሱት ሕፃናቱ ብቻ ሳይሆኑ ወላጆችም ጭምር መለያየታቸውን መቋቋም ከብዷቸዋል።
ህፃናቱ ያደጉት በሷ እጅ በመሆኑ እንደ ሁለተኛ እናታቸው አድርገው ስለሚያዩአት የመለያየቱን ህመም መቋቋም አቅቷቸው በከፍተኛ አቅም ሲያለቅሱ ይታያል።
ወላጆችም አብረው ማልቀሳቸው እህታችን በቤታቸው ውስጥ የነበራትን መልካም ስነ-ምግባር፣ ታማኝነት እና የታየችበትን የፍቅር ልክ ግልጽ ያደርጋል።
በአርብ ሀገር ተሰደው እሚሰሩ የማህበራዊ ህይወት ባህልና እሴት መሰረቱ በፍቅር፣ በሩህሩህነት እና ልጅን እንደራስ አይቶ በማሳደግ ላይ የተገነባ ነው። ይህ ዓይነቱ ባህሪ በስራ አጋጣሚ ባህር ማዶ በሚሄዱ እህቶቻችን ዘንድ በጉልህ ይታያል፡
ሰራተኞች ልጅን የቤት ሰራተኛ ሆኖ "በስራ መመሪያ" ብቻ ከመንከባከብ ይልቅ በውስጣቸው ባለው እናትነታዊ ፍቅር ሞልተው ነው የሚያሳድጉት።
የገንዘብ ኮንትራት ሊያልቅ ይችላል፤ በፍቅር፣ በታማኝነት እና በደግነት የተገነባ የሰው ልጅ ግንኙነት ግን ድንበር እና ጊዜ ሳይገድበው በልብ ውስጥ ታትሞ ይኖራል።
ይህ ከላይ በቪዲዮ እንደምታዩት በውጭ ሀገር የሚሰሩ እህቶቻችን የሚያሳዩትን መልካም ሰብኦዊነት እና ፍቅር በግልጽ የሚያሳይ፣ እንዲሁም መልካም ስራ እና እውነተኛ ፍቅር ሁልጊዜም ዋጋ እንደለው የሚያሳይ ትልቅ ማስተማሪያ ነው።Via፦ ቤኪ የማርያም ልጅ
ከንፁህ ፍቅር በላይ ምን ነገር አለ🥰

11 days ago
ኮሎምቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው
የኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት አቤላርዶ ደ ላ ኤስፕሪኤላ ሀገራቸው ከምትከተለው አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ አካባቢዎች የሚገኙ 14 ኤምባሲዎችን ለመዝጋት ማቀዳቸውን አስታወቁ።
ይህ ውሳኔ የኮሎምቢያን የዲፕሎማሲ ወጪዎች ለመቀነስ እና የተረፈውን በጀት እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ጸጥታ እና መሠረተ ልማት ባሉ የሀገር ውስጥ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለማዋል ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በዕቅዱ መሠረት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በደቡብ አፍሪካ፣ ጋና እና ሴኔጋል የሚገኙ ኤምባሲዎች የሚዘጉ ሲሆን፣ በነዚህ ሀገራት የሚገኙ የኮሎምቢያ ዜጎች በአቅራቢያ በሚገኙ ሌሎች ተወካይ መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።
በተጨማሪም የኮሎምቢያው መጪ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር የተለየ አካሄድ በመከተል ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ፣ የሀገሪቱን ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር እና የንግድና ጸጥታ ትብብሮችን ለማጠናከር ማቀዱ ታውቋል። አዲሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ይህ የዲፕሎማሲ መዋቅር ማሻሻያ በስልጣን ቆይታቸው የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚገመገም ጠቁመዋል።

አንድ ቤተሰብ… አንድ ሕይወት… የእኛን እርዳታ ይጠብቃል!
አቤል መለሰ በትምህርቱ የላቀ ውጤት ያስመዘገበ፣ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በትጋት ሲዘጋጅ የነበረ ብሩህ ተማሪ ነበር።
ይሁን እንጂ ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ፣ በፒያሳ ሀገር አቀፍ ቲያትር አካባቢ ከተገነባ ሕንፃ 13ኛ ፎቅ ላይ የወደቀ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ከባድ ቁስ በራሱ ላይ በመውደቁ ከባድ የራስ ቅል ጉዳት ደረሰበት።
በላንሴት ጠቅላይ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ቢደረግለትም፣ ከአደጋው በኋላ ለ7 ወራት ያህል እስካሁን ድረስ በአልጋ ላይ ራሱን ስቶ ይገኛል።
መጀመሪያ የሕክምና ወጪውን የሸፈነው ተቋራጭ በኋላ ድጋፉን በማቋረጡ፣ ቤተሰቡ አሁን ከፍተኛ የሕክምና ወጪ ጫና ውስጥ ገብቷል።
ዛሬ አቤል ሕይወቱን ለማዳን የእኛን እገዛ ይሻል። 🙏
እባክዎ በሚችሉት መጠን ያግዙ። የእርስዎ ትንሽ ድጋፍ ለአቤል ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
የባንክ ሒሳብ (CBE)
እታለማሁ አሰፋው ወ/መድኅን (ወላጅ እናት)
1000348860538
+251-911-398024 / +251-931-534451
እባክዎ ይህን መረጃ SHARE በማድረግ ለብዙ ሰዎች ያድርሱ። ምናልባት የእርስዎ አንድ ሼር ወይም አንድ አስተዋጽኦ የአቤልን ሕይወት ለማዳን ወሳኝ ሊሆን ይችላል።
ፈጣሪ የሚረዱትን ይባርክ።
Via: ቤተሰቡ

12 days ago
8 ኢትዮጵያውያን 160 ኪሎ ግራም ጫት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያስገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ አካላት ባካሄዷቸው የፍተሻ እና የቁጥጥር ስራዎች፣ የድንበር ህግ የተላለፉ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለጠ።
በጃዛን ክልል አል-ዳየር (Al-Daer) በተባለው ቀጠና የሚንቀሳቀሱ የድንበር ጠባቂ የፓትሮል አባላት 160 ኪሎ ግራም ጫት ይዘው ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን 8 የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተዘግቧል።
Via Saudi Gazette
እባካችሁን ወጣቶች ህይወታችሁን እና የወደፊት ተስፋችሁን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶች ላይ ከመሰማራት ተቆጠቡ! ጉርሻ page

13 days ago
የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️
ህወሃት የ 1983 ታሪክን እንደግማሁ እያለ ነው።
የሕወሓት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ በአንድ መድረክ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሁን ከተጣመርናቸው ኃይሎች ጋር መዋጋታችን አይቀርም ብለዋል፡፡ የሀላፊዋ ንግግር የጽምዶ ኃይሎችን የትብብር መሰረት የሚያናጋ ነው ተብሏል፡፡
ወይዘሮ ፈትለወርቅ ቃል በቃል የተናገሩ፡-
‹‹ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላጎት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል።
ለዚህም እየተዘጋጀን ነው፤ ይህ በተለያየ መልክ የተጀመረውን ትብብራችንን ስናየው የተለያየ ፍላጎት ያለን ሃይሎች ሆነን ነው ትብብር እየፈጠርን ያለነው። በአላማ፣ በፕሮግም፣ ወደፊት በረዥም ጊዜ እቅድ ምናምን አንድ ነን ማለት አይደለም። ትብብራችን በዛች በምታገናኘን ነገር ብቻ ነው።
እኛ ከፋኖ የምንለይበት የፖለቲካ አቋም አለን። ከሻዕቢያ ይሁን ከሌሎች የተለያዩ ሃይሎች የምንለያይባቸው መዓት ጉዳዮች አሉ። አንድ የሚያደርገን ግን የብልፅግና ስርዓት የሁላችንም ስጋት ነው የሚለው ነው። ይቺ ብቻ ናት የምታገናኘን።
እንደ ተሞክሮ ልንወስደው የሚገባን ነገር ደግሞ እንኳን አሁን በብዙ ጉዳዮች ልዩነት ካለንና በዓላማ ከማንገናኛቸው የተለያዩ ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና ኢህአዴግም እኮ ፈርሷል።
ኢህአዴግ እኮ የኦሮሞ፣የአማራ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ሃይሎች አራት ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነን የፈጠርነውና በፕሮግራም ወይም አላማ አንድ የነበረ ድርጅት ነበር። ግንኙነታችንም ስትራቴጂካዊ ነበር[ታክቲካል አልነበረም] ፣ በተለያየ ቋንቋ የተፃፈች አንዲት ፕሮግራም ነበር የነበረችን።
ግንባር ከመሆናችን ውጭ አንድ ድርጅት ማለት ነበርን፤ በዚህ ደረጃ የነበርን ሰዎች እኮ ተካክደናል[እንኳን ይሄ በዓላማ ከማይመስሉን ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና]›› ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
Via :- Andafta

17 days ago
120 ስልክ ሿሿ ያደረገው ግለሰብ….
በኡጋንዳ በቀን 120 ስልኮችን የሰረቀው ግለሰብ ከስልኮቹ ጋር የተያዘ ሲሆን፣ «ስልኮቻችሁ የተሰረቁባችሁ ሰዎች ወደ ኡጋንዳ ፖሊስ ጣቢያ እየመጣችሁ ተቀበሉ» ተብሏል።
የሚገርመው ነገር፣ ስልኮቹ የስክሪን ምስላቸው (Screen saver) እንኳን ሳይቀየር እንደነበረው ነው ያሉት።
ያ ማለት የተሰረቀባቸው ሰዎች በስክሪናቸው ላይ ያደረጉት ምስል የራሳቸው ከሆነ በቀላሉ ስልካቸውን ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው።
ስለዚህ ለክፉም ለደጉም የስልካችሁን Screen Saver የራሳችሁን አድርጉት።
ህዝቡም ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተመመ ነው።
Via Uganda Police

Welcome to Ethiopian Aviation University, where future leaders of African aviation are made. #ethiopianaviationuniversity

Comments