Logo
YenetaTube
የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል

ነጭ ናፍጣ በሊትር 180.46 ብር ገብቷል። ቤንዚንም በሊትር 167.50 ብር ሆኗል።

ከዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ማደያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ደብዳቤ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን ያስረዳል።

በደብዳቤው በተገለጸው መሰረት በሊትር፦
- ነጭ ናፍጣ 180.46 ብር
-​ ቤንዚን 167.50 ብር
-​ ኬሮሲን 320.66 ብር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 170.62 ብር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 167.37 ብር
-​ የአውሮፕላን ነዳጅ 319.76 ብር ሆኗል።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በቅሎ ቤት ፣ ሳሪስ አካባቢ ባሉ ማደያዎች ቅኝት ያደረገ ሲሆን፣ ማደያዎቹ ሽያጭ እያከናወኑ ያሉት በተሻሻለው ዋጋ መሰረት ነው።

የማደያዎቹ ሠራተኞች ቤንዚን 167.50 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 180.46 ብር እየሸጡ፣ ሹፌሮችም በዚሁ መሰረት እየቀዱ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በነዳጅ ምርቶች ላይ ከአንድ ወር በፊት የዋጋ ጭማሪ ተደርጎ ነበር።

tikvahethiopia

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.