Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አቋርጧቸው ከነበሩ በረራዎች መካከል የትኞቹን በድጋሚ አስጀመረ ?

በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ግጭት ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቀጠናው ያደርጉት የነበረውን በረራ በጊዜያዊነት ማቋረጣቸው ይታወቃል።

በሳምንት ከ 100 በላይ ምልልሶችን ያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ ሃገራት ያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ካቋረጡ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።

ለሳምንታት ተቋረጦ የቆየው በረራ ወደ አንዳንድ የቀጠናው አካባቢዎች በድጋሚ ማስጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዛሬው ዕለት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ "የመሻሻል ነገሮች በምናይባቸው አካባቢዎች በተወሰነ ደረጃ በረራ እንደገና አስጀምረናል" ብለዋል።

በረራ የጀመረባቸው አካባቢዎች :-

• ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ዱባይ በቀን አንድ በረራ ፣
• አቡዳቢ በቀን አንድ በረራ ፣
• ሻርጃ በቀን አንድ በረራ
• ሳውዲ አረቢያ (ደማም ከተማ) በቀን አንድ በረራ
• ጆርዳን አማን በቀን አንድ በረራ ናቸው።

ይሁን እንጂ አቶ መስፍን ዶሃ (ኳታር)፣ ባህሬን፣ ኩዌት እንዲሁም ቴላቪቭ እና ቤሩት በረራ እንደተቋረጠባቸው መሆኑን አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዝርዝር ምን አሉ ?

" እንደሚታወቀው በገልፍ አካባቢ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ወር አካባቢ ሆኖታል።

ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ገልፍ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚያደርገውን በረራ በተወሰነ ደረጃ ለጊዜው አቋርጧል።

ይህ በመሆኑ ምክንያት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ገልፍ የሚሄዱ መንገደኞች እያጓጓዝን አይደለም፤ ያ በመንገደኛ ቁጥራችን ላይ የተወሰነ ተፅዕኖ ያሳድራል።

ይሁን እንጂ በሌሎች በምንበርባቸው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቻችን ላይ ያለንን በረራ በማጠናከር ከዚህ ከገልፍ እና መካከለኛው ምስራቅ ያጣነውን መንገደኛ ቁጥር ሌላ ቦታ በመብረር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ለማካካስ ሞክረናል።

በዚህ መንገድ እየቀጠልን ነው፤ ሁኔታውን እየተከታተልን ነው የመሻሻል ነገሮች በምናይባቸው አካባቢዎች በተወሰነ ደረጃ በረራ እንደገና አስጀምረናል ያ እየቀጠለ ነው ያለው።

በረራ ተቋርጦ ከነበረባቸው መካከል አሁን መብረር የጀመርንባቸው ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ውስጥ ዱባይ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው፣ አቡዳቢ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው፣ እንዲሁም ሻርጃ በቀን አንድ በረራ እያደረግን ነው።

በተጨማሪም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ደማም የምትባል ከተማ አቋርጠን ነበር እሱን በረራ ቀጥለናል።

ይሁን እንጂ ዶሃ (ኳታር) ፣ ባህሬን ፣ ኩዌት እንዲሁም ቴላቪቭ እና ቤሩት በረራ እንዳቋረጥን ነው።

እንግዲህ በረራ ስናቋርጥ የበረራ ደህንነትን ትክክለኛ ትንተና አካሂደን ያለውን ሁሉ መረጃ አገናዝበን መብረር ሴፍ (safe) ነው የምንል ሲሆን ብቻ እንበራለን።

በተጨማሪም ጆርዳን አማን አቋርጠን ነበር እሱን ሁለት በረራ ነበረ አሁን በአንድ በረራ ጀምረናል " ብለዋል።

tikvahethiopia

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.