#update
" የሟቾች ቁጥር 107 ደርሷል " - የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)
⚫ " ከአንድ ወረዳ ብቻ 102 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የ50 ሰዎችን አስክሬን ማግኘት አልተቻለም። "
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ፣ካምባ እና ቦንኬ ወረዳዎች በደረሰው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 107 መድረሱን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከሟቾቹ መካከል ከጋጮ ባባ ወረዳ ብቻ 102፣ ከካምባ ወረዳ 2 እንዲሁም ከቦንኬ ወረዳ 3 በድምሩ የ107 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል።
ደምሴ (ዶ/ር) እስካሁን በተከናወነው አስቸጋሪ ፍለጋ የ57 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና በጋጮ ባባ ወረዳ የቀሪ 50 ሰዎች አስክሬን እየተፈለገ መሆኑን ገልፀዋል።
የአከባቢው መልካምድር አስቸጋሪ መሆን አስክሬን ፍለጋውን ከባድ ማድረጉን የገለፁት የዞኑ አስተዳዳሪው ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት እርዳት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የምያደርስ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawassa
tikvahethiopia

3 months ago