" ... በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ያላትን ሚና ማንም በሚሰጣት ችሮታ ሳይሆን በገዛ አቅሟና ጉልበቷ እንደምታረጋግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " ኢትዮጵያ በቀጠናው አንከር (መሰረት) ሀገር ብቻ ሳትሆን፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሁነኛና ወሳኝ ተዋናይ መሆኗን በተግባር የምታሳይበት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች " ብለዋል።
" ኢትዮጵያ በቀጠናችን አንከር ሀገር መሆኗ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ኢትዮጵያ ፎክረው እንደሚገዙ ሳይሆን ተጋድለው ነፃነታቸውን እንደሚያስከብሩ ድንቅዬ ጀግኖች ሀገር ዳግም ፍላጎቶቿን በራሷ መንገድ ታረጋግጣለች " ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎች፣ ዘመቻዎችና ጫናዎች ቢደቀኑባትም ሉዓላዊነቷንና ክብሯን አስጠብቃ መቀጠሏን ጠቁመዋል።
" በግንባርም ፣ በሚዲያም ፣ በሰይፍም ፣ በሰልፍም ፣ በውሸትም ፣ በሐሜትም ፣ በተንኮልም፣ በሸረባም ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም " ሲሉም ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ውድቀቷ ሲናፈቅ ጠንክራ የመውጣት፣ መበተኗ ሲጠበቅ ተሰብስባ የመቆም ትንግርታዊ ማንነት እንዳላት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሉዓላዊ ፍላጎቶቿን፣ የቀጠናዊ ትስስርና የልማት ውጥኖቿን በራሷ መንገድና ብርታት ማሳካት እንደምትችል አረጋግጠዋል።
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዘላቂ ህልውናና ጥንካሬ የሚረጋገጠው በየዘመኑ የሚገጥማትን " የማስቀጠል ፈተና " በማሸነፍ፣ የውስጥ አንድነትን በማጠናከር እና ዘላቂ አዲስ ሥልጣኔን በጋራ ጥረት በመገንባት ብቻ መሆኑን ለምክር ቤቱ አባላትና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር (የባህር በር) እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል። በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው። " ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው…

1 day ago