3 hours ago
በ60 ኮርሶች 47 A+ እና 13 'A' #ruthabate #astu #adamauniversity #electricalengineering #womeninstem #ethiopianexcellence
8 hours ago
ከ60 ኮርሶች 47ቱን 'A+' ያስመዘገበችው ባለብሩህ ተስፋዋ ባለዋንጫ መሃንዲስ ሩት አባተ
#ethiopia | ዛሬ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ካስመረቃቸው 1 ሺህ 387 ተማሪዎች መካከል፣ የአንድ ሴት እጩ የመጪው ዘመን መሃንዲስ ስም በልዩ ክብርና በታላቅ ጭብጨባ አዳራሹን አናውጦታል።
ይህ ስም የሩት አባተ ነው። ሩት በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ያስመዘገበችው እጅግ አስደናቂ ውጤት የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጓታል።
የኤሌክትሪካል ፓወር ኤንድ ኮንትሮል ኢንጅነሪንግ (Electrical Power and Control Engineering) ተማሪዋ ሩት አባተ፣ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 60 ኮርሶች መካከል 47ቱን 'A+' እንዲሁም የቀሩትን 13 ኮርሶች 'A' በማምጣት ሙሉ 4.00 (አራት ነጥብ) ውጤት አምጥታለች።
በዚህም በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ (Very Great Distinction) በመመረቅ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ መሆን ችላለች።
ተወልዳ ባደገችባት አዳማ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቀችው ሩት፣ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት የበቃችው ከቅድመ መደበኛ መሰረቷ ጀምሮ ባደረገችው ተከታታይ ጥረት መሆኑን ትገልጻለች።
“የአዳማ ልጅ ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ነው የተማርኩት፤ ሁሌም የደረጃ ተማሪ ነበርኩ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በትጋት እያጠናሁና እየሰራሁ ስለመጣሁ አቅሜን እያዳበርኩ እዚህ መድረስ ችያለሁ።
ዩኒቨርሲቲ ስገባም ከመጀመሪያ ዓመት ጀምሮ ለትምህርቴ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ራሴን ለፈተናዎች በአግባቡ በማዘጋጀቴ የላቀ ውጤት አምጥቻለሁ፤ ለዚህም ፈጣሪን አመሰግናለሁ” ስትል ሩት የስኬቷን ሚስጥር ታጋራለች።
ይህን ታላቅ ውጤት ስታስመዘግብ ሁሌም አብረዋት የነበሩትን የቤተሰቦቿን ውለታ በኩራት ታነሳለች። ምንም ዓይነት ትኩረቷን የሚሰርቅ ነገር እንዳይገጥማት ቤተሰቦቿ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዳደረጉላት ትናገራለች።
“ቤተሰቦቼ ሁሌም ከጎኔ ሆነው እንድበረታ አድርገውኛል።
ምንም ነገር ከትምህርቴ እንዳያዘናጋኝ በመምከርና በመደገፍ አብረውኝ የስኬቴ ተጋሪ ሆነዋል። እኔም ጥረታቸውን ከንቱ አላደረግኩም፤ አላሳፈርኳቸውም" ስትል በምስጋና ትገልጻለች።
ሴቶች የትኛውንም ማህበራዊና አካባቢያዊ ጫናዎች አልፈው ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ የምትመሰክረው ሩት፣ ይህ ውጤቷ ለሌሎች እህቶቿ ትልቅ ማበረታቻና አርአያ እንደሚሆን ታምናለች።
“እኛ ሴቶች የማንበብና የመማር ዕድል ካገኘን፣ የትኛውንም ዓይነት ማኅበራዊና አካባቢያዊ ጫናዎች አልፈን ለላቀ ስኬት መብቃት እንችላለን።
እኔም በቀጣይ የስኬታማ ሴቶች ህያው ምሳሌ ለመሆን ጠንክሬ እሰራለሁ።” ሩት በዚህ አሸናፊነቷ ብቻ ለመቆም አላሰበችም።
በቀጣይም በትምህርቷ ላይ ይበልጥ በመበርታት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቷን የመቀጠል እቅድ አላት።
ከሁሉም በላይ ግን የተማረችውን ትምህርት ለሀገሯ በተግባር ማዋል ትልቁ ህልሟ መሆኑን ትናገራለች።
"በኢነርጂውና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገሬ ጠቃሚና ችግር ፈቺ ባለሙያ ለመሆን እተጋለሁ" ስትል ጽኑ ምኞቷን ገልጻለች። ወጣቷ ባለዋንጫ መሃንዲስ ለዚህ ማዕረግ እንድትበቃ የረዷትን ፈጣሪዋን፣ ወላጆቿን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራኖቿንና ጓደኞቿን አመስግናለች።
ይህ የሩት ታሪክ የራሷ የትጋት ብቻ ሳይሆን የወላጆች የዕለት ተዕለት ክትትልና የጋራ ጥረት ውጤት ጭምር መሆኑን የእናቷ ምስክርነት ያረጋግጣል።
የሩት እናት ወይዘሮ አዜብ ሻውል፣ የመጀመሪያ ልጃቸው የዋንጫ ተሸላሚ ሆና መመረቋ በቤተሰቡ ውስጥ ልዩ ደስታና ኩራት መፍጠሩን ይናገራሉ።
“ሩት እድገቷ ከንባብ ተለይቶ አያውቅም፤ እጅግ ጥሩ ስነምግባር ያላት ልጅ ናት። ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ሁሌም አንደኛ እየወጣች ነው እዚህ የደረሰችው" በማለት እናቷ የልጃቸውን የልጅነት ትጋት ያስታውሳሉ።
በዩኒቨርሲቲም ቆይታዋ ሁልጊዜ ተሸላሚ መሆኗን በኩራት ያነሳሉ።
እናቷ አያይዘውም፣ የሩት አባት ሁሌም የቅርብ አማካሪና አስጠኝ በመሆን ለዚህ ውጤት ትልቅ እገዛ ማድረጉን ጠቅሰው፤ “ሩት ሀገሯን የምትጠቅም ልጅ ናት፤ ወደፊትም ከዚህ በላይ ትልቅ ደረጃ እንድትደርስ እመኛለሁ” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

8 months ago
እንደ ስሙ ተዓምር እየሠራ ያለው ራጂ አሸናፊ
#ethiopia | 'ራጂ’ የሚለው ቃል የአፋን ኦሮሞ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ተዓምር ማለት ነው። “ስምን መልአክ ያወጣዋል” እንዲሉ ታዲያ በዚህ ቃል የተሰየመው ራጂ አሸናፊ በፊዚክስ ተዓምር እየሠራ ይገኛል።
ራጂ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የቄለም ወለጋዋ ጊዳሚ ነው። የስምንተኛ ክፍል ውጤቱ ከፍተኛ ስለነበር የኦሮሚያ ልማት ማኅበር በሚያስተዳደረው ኦዳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የመማር ዕድል አግኝቷል።
ለቤተሰቡ ዘጠነኛ ልጅ የሆነው ራጂ በቤተሰቡ ውስጥ ትምህርት እንደ ምርጫ ሳይሆን እንደ ሕይወት መመሪያ ስለሆነ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት መማራቸውን ተናግሯል።
ኦዳ ካስፈተናቸው የመጀመሪያዎቹ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የሆነው ራጂ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት (647) በማስመዝገብ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቀለ።
ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) በ‘አፕላይድ ፊዚክስ’ እና በ‘አፕላይድ ሂሳብ’ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በ2014 ዓ.ም በሁለት ዲግሪዎች ተመርቋል።
በዩኒቨርሲቲው ቆይታው በ60 የትምህርት ዓይነቶች A+ ያገኘ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተማሪበመሆን ዕውቅና አግኝቷል።
ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MIT) የድኅረ ምረቃ ትምህርት ዕድል አግኝቷል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን ሲማር ባሳየው ልዩ የአካዳሚክ ብቃት ቀጥታ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ዕድል ያገኘው ራጂ፤ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርቱም ከፍ ያለው ዕውቅናው ቀጥሏል።
ራጂ አሁን በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተማረ ያለው የ‘ኢነርጂ ፊዚክስ’ አካል የሆነውን ‘ቲዎሬቲካል ፊዚክስ’ ሲሆን፤ ለትምህርቱ ልዩ ፍቅር እንዳለው ይገልጻል።
በቲዎሬቲካል ፊዚክስ መስክ የምርምር ጽሑፎችን ከአሜካሪው ፕሮፌሰር ባርተን ዝዊባች ጋር በጋራ አሳትሟል፤ እነዚህም፥ "Type II RR string fields and exotic diffeomorphisms"፣ "Boundary terms in string field theory"፣ እና "Gauge algebra and diffeomorphisms in string field theory" የሚሉ ናቸው።
በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MIT) ትምህርቱን ከመጀመሩ በፊት በጣሊያን፣ ትሪስቴ በሚገኘው አብዱስሰላም ኢንተርናሽናል ቲዎሬቲካል ፊዚክስ ማዕከል (ICTP) የአንድ ዓመት ኮርሶችን ወስዷል።
በ2023 ከዚሁ ተቋም (ICTP) በከፍተኛ ኢነርጂ፣ ኮስሞሎጂ እና አስትሮፓርቲክል ፊዚክስ የተሰጡትን ኮርሶች ሲያጠናቅቅ በዘርፉ ካሉት ከፍተኛ ምሁራን የአንዱን እውቅና ያገኘበትን ውጤት በማስመዝገብ ነበር።
ራጂ የወደፊት ራዕዩን ሲገልጽም፥ የ‘ቲዎሬቲካል ፊዚክስ’ ሊቅ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ማዕከላትን ማቋቋም እና ለተማሪዎች ዕድል መፍጠር መሆኑን ይናገራል።
ወጣቱ ኒውዮርክ በሚገኘው የተመድ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የንድፈ ሃሳባዊ ፊዚክስ መድረክ ላይ ተገኝቶ የወደፊት ራዕዩን አጋርቷል።
ራጂ በመድረኩ ላይ ከትውልድ ሀገሩ ከኢትዮጵያ እስከ ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያደረገውን ጉዞ እና የገጠሙትን ውጣ ውረዶች ዘርዝሯል።
በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ መምህራኑ ቀጣዮቹን የዓለም የሳይንስ ሊቃውንት እንደሚያፈሩ እምነት እንዳለው እና እሱም ይህን ዕድል በማግኘቱ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።
ባደገበት አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሌላው ቀርቶ በቂ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች እንዳልነበሩ የሚጠቅሰው ራጂ፤ ዩኒቨርሲቲ እስከሚገባ ድረስ ኮምፒዩተር አግኝቶ እንደማያውቅ ተናግሯል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ፈጣን ውጤት ስለማያሳይ እና ከባድም ስለሆነ ብዙዎች እንደማይመርጡት ገልጾ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሊያናቀቅ ወደ መጨረሻው ሲደርስ ስለ ‘ኳንተም ፊዚክስ’ ሰምቶ በፍቅሩ መውደቁን ገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ቲዎሬቲካል ፊዚክስ የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎች ስለሌሉ አፕላይድ ፊዝክስ ለመማር መወሰኑን ያወሳው ራጂ፤ በዚያም በርካታ ውጣ ውረዶች ቢኖሩም ዓላማው ላይ አተኩሮ መሥራቱን ተናግሯል።
አሁን ባለበት ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከዓለም ዙሪያ ከመጡ ተማሪዎች ጋር ያለው ፉክክር ከባድ ቢሆንም በትምህርቱ ደስተኛ መሆኑን እና ከሁሉም በላይ መምህራኑ በተማሪዎቻቸው ላይ ያላቸው እምነት ብርታት እንደሆነው አንስቷል።
ባደጉ ሀገራት ያሉ ተማሪዎች መሰረታዊ ሳይንስን ከታች ጀምረው እየተማሩ ስለሚመጡ በኢንስቲትዩቱ ያላቸው ብቃት እና ፉክክርም የላቀ እንደሆነ እና በኢትዮጵያም እንደዚህ ዓይነቱ ባህል መለመድ እንዳለበት ጠቁሟል።
በማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሦስተኛ ዲግሪ እየሠራ ያለ ብቸኛው ጥቁር እንደሆነ የጠቀሰው ራጂ፤ በዓለም ላይ በርካታ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች ስላሉ ዕድሉን ቢያገኙ ዓለም የነገዎቹን ምርጥ ሳይንቲስቶች ልታገኝ እንደምትችል ተናግሯል።
ራጂ በግሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ባደረጋቸው ቃለመጠይቆች ወደኋላ ስለሚጎትቱት ችግሮች ማሰብ እንደማይፈልግ እና ከችግሮች ውስጥ ዕድሎችን ለማግኘት እንደሚጥር ተናግሯል።

9 months ago
#aastu #astu
በ2018 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ማክሰኞ መስከረም 20/2018 ዓ.ም ከጠዋት 2፡00 ሰዓት ጀምሮ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎቹ ገልፀዋል።
ተፈታኞች ለፈተናው ስትሔዱ መመዝገባችሁን የሚገልፅ ከሲስተም ላይ በማውረድ ፕሪንት አድርጋችሁ መያዝ ያስፈልጋችኋል።
በተቀሰው ቀን ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ እና የአድሚሽን ካርዳችሁን በመያዝ በምዝገባ ወቅት በመረጣችሁት የፈተና ማዕከል ከ2:00 ሰዓት ቀደም ብላችሁ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲዎቹ አሳስበዋል።
ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት እና ሌሎች የተከለከሉ ነገሮች ወደ ፈተና ማዕከል ይዞ መግባት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
በአንዳንድ የፈተና ጣቢያዎች የጠዋት እና ከሰዓት በኋላ ፈተና ሊኖር ይችላል ተብሏል።
seledadotio

Comments